ሰኞ 26 ኦገስት 2019

የሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴን ‹ይቻላል› እኔ እንደምረዳው





ከሰሞኑ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴን የሚያስታውሱኝ አንዳንድ ነገሮችን አየሁ፡፡ በትምህርት ቤት ግንባታ እያደረገ ያለውን ጉልህ ሚና ሁላችንም እያደነቅነው ነው፡፡ አንድ ቆየት ያለ የአማርኛ ጋዜጣ ከአንዲት ኢትዮጵያ ውስጥ ከቆየች የቢቢሲ ዘጋቢ ጋር ባደረገው ቆይታ ዘጋቢዋ ከኢትዮጵያውያን ኃይሌን በአርዓያት እንድንጠቀምበት ጠይቃለች፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት በተለያዩ ቦታዎች በተዘዋወርኩበት ጊዜ ሁለት የኃይሌ ሳይሆኑ የማይቀሩ የእጅ ጽሑፎችን ለማየት ችያለሁ፡፡ እነዚህም አንደኛው ኃይሌ ሪዞርት የሚለው ጽሁፍ ላይ ያለው የእንግሊዝኛ ጽሑፍ፣ ይኸውም ኃይሌ (Haile) የሚለው ነው፡፡ ሌላውና ቆየት ያለው ይቻላል የሚለው ነው፡፡ ንግድ ምክር ቤትም ሳይጠቀምበት አይቀርም፡፡ 
የሆነው ሆኖ፣ ይቻላል ምን ማለት ነው ብዬ ራሴን ጠየቅሁ፡፡ በትምህርት ቤትም ይቻላል ይባላል፡፡ ታላቅም ታናሹን ሲያበረታታ ይቻላል ይላል፡፡ መምህርም ተማሪውን እንዲሁ፡፡ ሻለቃ ኃይሌ እየተጠቀሰ እሱ እንዳለው  እየተባለ ይቻላል ይባላል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም - አሉ ብቻ አንዳንድ አገላለጾች - ዘወትር የምንሰማቸው፣ ግን ምን ማለት ናቸው የሚለውን የማናውቀቸው ወይንም ያላሰላሰልናቸው፡፡ ‹‹አርስቶትል ‹እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው› አለ›› ይባላል፡፡ ምን ማለቱ ነው የሚለው ብዙም አይብራራም፡፡ ወይም አውዱ ለማብራራት የመያመች የጨዋታ ማድመቂያ ይሆናል፡፡
ጀግናው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ብዙ ተብሎለታል፡፡ የኃይሌ ማሸነፍ ዜና አይደለም እንዲል ደምሴ ዳምጤ፡፡ ሃያ ሰባት የዓለም ሪኮርዶችን በጣጥሷል፡፡ በዓይናችን እያየነው ከስኬት ማማ የወጣ፣ ቀን በቀን እየጠነከረ የመጣ፣ ትልቅ አርአያ ነው፡፡ ስለ ኃይሌ ለእርስዎ መንገር ለቀባሪው ማርዳት እንዳይሆን ወደ ዋናው ጉዳዬ ልግባ፡፡
ይቻላል ምንድነው?
ለእኔ ይቻላል ዝም ብሎ ቃል አይደለም፡፡ በተለይ ኃይሌ ይህን ቃል ሲጠቀምበት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ለስኬታችን ቀን ከቀን ያለማሰለስ ከሰራን ያን ድል መቀዳጀት ይቻለናል ማለቱ ነው፡፡ ስኬት ለኃይሌ የዓለም ሪኮርዶችን መሰባበርና በተሰማራበት ሙያ ትልቁ ሰው መሆን ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ አድርጎታል፤ ሆኗል፡፡ አንድ ወቅት ላይ የደረሰኝ የጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው ሪከርድ የሚሰብሩ ወይም በዓለም ላይ ካሉ አትሌቶች ከፍተኛውን ቦታ የሚይዙ ከአይኪዋቸው ብዙ ተጠቅመዋል፡፡ አዎን! በዓለም ላይ ሚሊየን ዶላሮችን የማይፈልግ የለም፡፡ ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ፡፡ ከዚህ የዓለም ህዝብ ነጥሮ መውጣት አእምሮን በትክክል መጠቀምን ይጠይቃል፡፡ አካልንና አእምሮን አጣምሮ ከስኬት ማማ የደረሰውና ዓለም ያጨበጨበለት ኃይሌ ‹‹ፕሬዚዳንት ልሁን›› አለ ተብሎ የተቀለደው እዚህ ጋ ፉርሽ ይሆናል፡፡ ኃይሌ በአካልም በአእምሮም የበለጸገ ስለሆነ!
 ኃይሌ ስለ ዕለት ውሎው ብዙ ተናግሯል፡፡ ልምምዶችን ያለማሰለስ ያደርጋል፡፡ ሃሳቡ ከውድድሮቹና ከዓላማው ላይ ነው፡፡ የአንዲት ቀን ልምምድ መታጎል ቀጣዩን ድል ያሳጣዋል፡፡ ስለሆነም ይተጋል፡፡ በዚህም ምክንያት ይተጋል፡፡ ስለሚተጋም ይቻላል፡፡ በተሰማራበት ዘርፍ የተቻለውን ጥረት አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ስፖርት ብዙ ይቻላል የሚያስብሉ ገጠመኞችን አሳይቶናል፡፡ ይድነቃቸው ተሰማ፣ አበበ ቢቂላ፣ ፍቅሩ ኪዳኔ እንደሚቻል ያሳዩ ናቸው፡፡ ፍቅሩ ኪዳኔ ብዙ ስላልተነገረለት እንጥቀሰው፡፡ ከሃረር መምህራን ማሰልጠኛ በስፖርት መምህረነት በሰርተፊኬት የተመረቀ ነው፡፡ የእርሱ ፍላጎት ወደ ጋዜጠኝነት የመዝ ነበረና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዘጋቢ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስፖርተ ጋዜጠኛ ሆነ፡፡ እነ ክቡር አቶ ይድነቃቸውን እየተከተለ ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም መድረክ  መወከል ጀመረ፡፡ አሁን ፊፋን፣ አይኤኤኤፍንና ሌሎችንም የስፖርት ተቋማት ያማክራል፡፡ በዘርፉ ብቸኛው ጥቁር እስከመሆን መድረሱን ከሳቢው የህይወት ታሪኩ ከፒያሳ ልጅ መማር እንችላለን፡፡ አንዲትን ዘርፍ መርጠን ከተሰማራንና ከበረታን እንደሚቻል ከኢትዮጵያ ስፖርት ብዙ መማር እንችላለን፡፡ ይቻላል! አዎ ይቻላል! የሚቻለው ግን በትጋት፣ በጽናት፣ ጊዜን በመጠቀም ነው፡፡

ረቡዕ 21 ኦገስት 2019

ሁቱትሲ፣ የሩዋንዳዊቷ ወጣት ከዘር ማጥፋት የመትረፍ ታሪክ።
የአዲስ ዓመት ስጦታ ለአንባቢያን
ያንብቡ፤ አስተያየት ይስጡ፤ ያጋሩ።
ቴሌግራም የሌላችሁ ኢሜላችሁን ጻፉልኝ።
https://t.me/hututsi1/2

ሰኞ 12 ኦገስት 2019

Ras Abebe Aregay Library: in Retrospect and Prospect


Mezemir Girma (mezemirgirma@gmail.com)



Sometime in 2015, for a moment before class I availed myself in the English Language Improvement Center (ELIC) of Debre Birhan University, Ethiopia. I think the center was founded by Katryn, an African-American Volunteer Service Officer (VSO). As you enter the ELIC you see a small bookshelf. To the right, there are computers which are connected to the internet. Students who were at the center at that time were absorbed in the internet. There was no one who wanted the books. As a result, they looked deserted, disorganized, and unattractive.


This initiated me to arrange the books and I started the task right away. In the arrangement, I arranged the fiction in one row, the academic in the other and the periodicals below them. There was one book I didn’t know where to put. It was entitled, “Left to Tell, Discovering God Amidst the Rwandan Holocaust.” After I finished arranging the books, I borrowed the book and left. For teachers, borrowing was done by writing one’s name in a register.  
I read the book. It was a saddening read. I knew that the issue of managing one country’s diverse ethnic groups was a challenge everywhere in Africa. Ethiopia is one of these countries. As a result, I started to translate the book into Amharic, the language of Ethiopia. The translation project was finalized in my summer break. Then I headed to editors and people who could give me their comments. Many lent me a hand including Dr Yacob Hailemariam, who was a prosecutor for Rwandese genocide victims of 1994. He wrote me the foreword of my book in translation. I’m really indebted to all of them. Self-publishing the book in 2016 costed me around 2500 USD. The book got a wider acceptance and it opened my eyes to the world outside of teaching.
 For three years in row since then, I kept trying to find out who brought the book on Rwanda to the ELIC. Katryn, who I asked via email responded after a long silence and she said she was not the one. Anyhow, whosoever brought the book to our place was a very thoughtful person. Ethiopia needs more of such books to prevent the genocide pandemic.



A great idea came to me after my friends and family members told me that mine was the first book they read in their entire lives. I opened a library in Debre Birhan City Administration. Alongside my teaching job, I managed this library. There were four librarians at one time when the library had two branches. We are really changing the situation in this city where there are only two public libraries that do not have library programs other than giving a reading space and access to books.   
Ras Abebe Aregay Library has been giving various services to the public over the last three and a half years. For the future, we have projects that are awaiting donors’ attention. Once they get donors, we can keep making history in central Ethiopia.

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...