2017 ዲሴምበር 29, ዓርብ

የመጽሐፍ ዳሠሣ



 ደቂቀ እስጢፋኖስ፣ በሕግ አምላክ
ትርጉም (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ)
አአዩ ፕሬስ 2007
የገጽ ብዛት - 331
ዋጋ - 97 ብር
ይህ መጽሐፍ በሌላኛው እትሙ ሰውን ማሰቃየትን እኛ የፈጠርነው እንዲመስላቸው እንዳረገና የሃሳብ ብዙህነትንና የአማራጭ ሃሳብ መንሸራሸርን እስካሁን አለመቀበላችን ታሪካዊ ሥር እንዳለው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የጻፉለት ነው፡፡ አራት ገድሎችን፣ ማለትም ገድለ አባ እስጢፋኖስን፣ ገድለ አበው ወአኀውን፣ ገድለ አባ አበክረዙን እና ገድለ አባ እዝራን ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተርጉመው ለአንባቢያን ያደረሱት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ-መንግሥት (1426-1460) በዚህ አስተምህሮ ተከታዮች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ በአማርኛ ያስነብቡናል፡፡ ለአብ፣ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ በቀር (ለወላዲተ አምላክ) ሥዕል፣ ለመስቀል፣ ለንጉሥ አንሰግድም የሚሉት የመስራቹ የአባ እስጢፋኖስ ተከታዮች ከቤተክርስቲያን ቀደምት ታዋቂ ሰነዶች ዉጪ የሆኑትን መጻሕፍት አይቀበሉም፡፡ እነዚህ እስጢፋኖሳውያን በንጉሡ ችሎት ቀርበው ከካህናተ ደብተራ ጋር በግልጽ ክርክር ያደርጉና ይፈረድባቸው ጀመር፡፡ የእንቅስቃሴው ተመልካቾች አልፎ አልፎ የፖለቲካ ገጽታ የሚሰጡት ይህ እርምጃ ከአንዳንድ ወገኖች የንጉሡን ፍትሐዊነት ማሳያ አድርጎ ይወሰዳል፡፡
የስቃዮቹ ዓይነት በርካታ ሲሆን የሠውነት ክፍልን መቁረጥ፣ ጅማት መምዘዝ፣ ግርፋትና፣ ድብደባን ሁሉ ያጠቃለለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ ሃያኛው ክፍለዘመን ድረስ እነዚህን የመሳሰሉ በአካላዊ ጉዳቶች እንደሚፈጽም ‹‹ተፈሪ መኮንን›› በሚለው መጽሐፍ ሳይቀር ተጠቅሷል፡፡ ይህም ቅጣቱ የባህላችን አካል የሆነ ከሆነ በነዚህ የሃይማኖት ተቃዋሚዎች ላይ የተጋነነ ቅጣት ተፈጽሟል የሚሉትን ሰዎች መከራከሪያ ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡  
ከንጉሡ በኩል ያሉ ምክንያቶችን ያየን እንደሆነ፤ በብዛት አከራክረው ውሣኔ ይሰጣሉ እንጂ በግብታዊነት ግፍ አይፈጽሙም፡፡ በደብረ ብርሃን የብርሃን መውረድን አስመልክቶ ሁለቱም አካላት፣ ከዘርዓያዕቆብም ሆነ ከእስጢፋኖስ በኩል ያሉት፣ ለኛ ከአምላክ የተላከ መልዕክት ነው ይላሉ፡፡ ይህን ነገር ከሳይንሳዊ አተያይ የሚያዩት ደግሞ በደብረብርሃን ያለፈችው ሃሊስ ኮሜት ነች፤ ይህም ምንም ዓይነት ተዓምር ሳይሆን የተለመደ ሂደት ነው ይላሉ፡፡
እንቅስቃሴው ሴቶችም አሉበት፡፡ ‹‹ትወጋ እንደሆነ እንደወንድ ውጋ›› ብላ አንድን ሰውነት በስለት የሚወጋ የአጼ ዘርዓያዕቆብ ወታደር የተናገረችውን ሴት ደቂቀ እስጢፋኖሳዊ ማየት ይቻላል፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ራሳቸው የጻፏቸው የብራና ሰነዶች ናቸው ተተርጉመው ለአማርኛ አንባቢያን የደረሱት፡፡

የእንቅስቃሴው መስፋፋት የሚያሳስብና ሥርዓትንና ሐይማኖትን ወደተለየ አቅጣጫ የሚወስድ እንደነበረ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ሃሳባችንን አንቀይርም እያሉ ለእርድ የቀረቡት እስጢፋኖሳውያን ዓላማቸው ምን እንደሆነ የሚያሳስብ ሲሆን ምናልባት የፖለቲካ ዓላማ ይኖራቸው ይሆን ያስብላል፡፡ 15ኛው ክፍለዘመን ላይ የነበረው ይህ እንቅስቃሴ በአውሮፓ የመጣውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ የሚቀድምና የሃገሪቱን ታሪክ የሚቀይር እንደነበረ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአንጻሩ ሲታይ የንጉሡ ሰራተኞችና ሹሞች በትግራይም የእንቅስቃሴውን ተከታዮች ይቀጡ ስለነበር የፖለቲካ አይመስለኝም፡፡ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ክፍላተሃገራትና አውራጃዎች ተከታዮች አፍርተዋል፡፡ ይህም የአንድ አካባቢ እንቅስቃሴ ሳይሆን የአገሪቱ ምዕመናንን ያካተተ ብልጭ ብሎ የጠፋ ክስተት ያደርገዋል፡፡

2017 ዲሴምበር 19, ማክሰኞ

I almost experienced what Stephens's son experienced in his childhood



“A few years ago, my wife Sandra and I were struggling with this (deep-rooted problem) kind of concern. One of our sons was having a very difficult time in school. He was doing poorly academically; he didn't even know how to follow the instructions on the tests, let alone do well on them. Socially he was immature, often embarrassing those closest to him. Athletically, he was small, skinny, and uncoordinated -- swinging his baseball bat, for example, almost before the ball was even pitched. Others would laugh at him.

Sandra and I were consumed with a desire to help him. We felt that if "success" were important in any area of life, it was supremely important in our role as parents. So we worked on our attitudes and behavior toward him and we tried to work on his. We attempted to psych him up using positive mental attitude techniques. "Come on, son! You can do it! We know you can. Put your hands a little higher on the bat and keep your eye on the ball. Don't swing till it gets close to you." And if he did a little better, we would go to great lengths to reinforce him. "That's good, son, keep it up."

When others laughed, we reprimanded them. "Leave him alone. Get off his back. He's just learning." And our son would cry and insist that he'd never be any good and that he didn't like baseball anyway.

Nothing we did seemed to help, and we were really worried. We could see the effect this was having on his self-esteem. We tried to be encouraging and helpful and positive, but after repeated failure, we finally drew back and tried to look at the situation on a different level.

At this time in my professional role I was involved in leadership development work with various clients throughout the country. In that capacity I was preparing bimonthly programs on the subject of communication and perception for IBM's Executive Development Program participants.
As I researched and prepared these presentations, I became particularly interested in how perceptions are formed, how they govern the way we see, and how the way we see governs how we behave. This led me to a study of expectancy theory and self-fulfilling prophecies or the "Pygmalion effect," and to a realization of how deeply imbedded our perceptions are. It taught me that we must look at the lens through which we see the world, as well as at the world we see, and that the lens itself shapes how we interpret the world.

As Sandra and I talked about the concepts I was teaching at IBM and about our own situation, we began to realize that what we were doing to help our son was not in harmony with the way we really saw him. When we honestly examined our deepest feelings, we realized that our perception was that he was basically inadequate, somehow "behind." No matter how much we worked on our attitude and behavior, our efforts were ineffective because, despite our actions and our words, what we really communicated to him was, "You aren't capable. You have to be protected."
We began to realize that if we wanted to change the situation, we first had to change ourselves. And to change ourselves effectively, we first had to change our perceptions.”
Stephen Covey, the 7 Habits of Highly Effective People
I feel that his son’s childhood story was mine. I felt this way as a child.

My Take Away from the Great Book of Leadership



“There is no real excellence in all this world
which can be separated from right living.
David Starr Jordan

In more than 25 years of working with people in business, university, and marriage and family settings, I have come in contact with many individuals who have achieved an incredible degree of outward success, but have found themselves struggling with an inner hunger, a deep need for personal congruency and effectiveness and for healthy, growing relationships with other people.

I suspect some of the problems they have shared with me may be familiar to you.

I've set and met my career goals and I'm having tremendous professional success. But it's cost me my personal and family life. I don't know my wife and children any more. I'm not even sure I know myself and what's really important to me. I've had to ask myself -- is it worth it?

I've started a new diet -- for the fifth time this year. I know I'm overweight, and I really want to change. I read all the new information, I set goals, I get myself all psyched up with a positive mental attitude and tell myself I can do it. But I don't. After a few weeks, I fizzle. I just can't seem to keep a promise I make to myself.

I've taken course after course on effective management training. I expect a lot out of my employees and I work hard to be friendly toward them and to treat them right. But I don't feel any loyalty from them. I think if I were home sick for a day, they'd spend most of their time gabbing at the water fountain. Why can't I train them to be independent and responsible -- or find employees who can be?

My teenage son is rebellious and on drugs. No matter what I try, he won't listen to me. What can I do?

There's so much to do. And there's never enough time. I feel pressured and hassled all day, every day, seven days a week. I've attended time management seminars and I've tried half a dozen different planning systems. They've helped some, but I still don't feel I'm living the happy, productive, peaceful life I want to live.

I want to teach my children the value of work. But to get them to do anything, I have to supervise every move...and put up with complaining every step of the way. It's so much easier to do it myself. Why can't children do their work cheerfully and without being reminded?

I'm busy -- really busy. But sometimes I wonder if what I'm doing will make any difference in the long run. I'd really like to think there was meaning in my life, that somehow things were different because I was here.
I see my friends or relatives achieve some degree of success or receive some recognition, and I smile and congratulate them enthusiastically. But inside, I'm eating my heart out. Why do I feel this way?

I have a forceful personality. I know, in almost any interaction, I can control the outcome. Most of the time, I can even do it by influencing others to come up with the solution I want. I think through each situation and I really feel the ideas I come up with are usually the best for everyone. But I feel uneasy. I always wonder what other people really think of me and my ideas.

My marriage has gone fiat. We don't fight or anything; we just don't love each other anymore. We've gone to counseling; we've tried a number of things, but we just can't seem to rekindle the feeling we used to have.
These are deep problems, painful problems -- problems that quick fix approaches can't solve.” Stephen Covey, the 7 Habits of Highly Effective People
If you suffer from problems like the ones stated above, feel free to contact me at mezemirgirma@gmail.com or 0970381070

2017 ኖቬምበር 29, ረቡዕ

የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት






የአንድ ገጽ የመጽሐፍ ማጠቃለያዎቼ
መዘምር ግርማ
የመጽሐፉ ርዕስ - የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት(1923 – 1948 ዓ.ም)፤ ደራሲ - አምባሳደር ዘውዴ ረታ፤  አሳታሚ - ሻማ ቡክስ፤ በድጋሚ የታተመበት ዘመን - 2005፤ የገጽ ብዛት - 809፤ ዋጋ - 400 ብር፤ 
ማሳሰቢያ፡- ይህን መጽሐፍ ለማንበብ ለሚነሣ ሰው የማሳስበው ነገር ቢኖር ከዚህ መጽሐፍ በፊት ያለውን ታሪክ የያዘውን በእኚሁ ደራሲ የተጻፈውን ‹‹ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የስልጣን ጉዞ›› የተባለውን መጽሐፍ እንዲያነብ ነው፡፡
በቀደመው መጽሐፍ የተነሡትን የተፈሪ መኮንንን በሥልጣን የመደላደል ጥረት ወደጎን ትተን (ማጠቃለያውን ስለጻፍኩ ሊያነቡትም ይችላሉ) ጥቅምት 23፣ 1923 ዓ.ም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተብለው የነገሱትን መሪ የመጀመሪያዎቹን 25 ዓመታት የንግሥና ጉዞ የሚያሳየውን ይህን መጽሐፍ እንመልከት፡፡
ኢትዮጵያን ከዓለም መንግስታት ማህበር ለማስገባትና አገሪቱም በአጼ ምኒልክ ዘመን የጀመረችውን የዘመናዊነት ጉዞ ለማጠናከር ቆርጠው የተነሱት ንጉሠ ነገሥቱ መሳፍንቱ ቢቃወሟቸውም ከፍጹም ፋውዳላዊ ወደ ሕጋዊ አስተዳደር አገሪቱን የሚያራምደውን ሕገመንግሰታቸውን ለማጽደቅና አንዳንድ ሌሎች ለውጦችን ለማስተዋወቅ በቅተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከአልጋ ወራሽነታቸው ጀምሮ አገሪቱን ለ58 ዓመታት የመሩት ኃይለሥላሴ ለስራቸው የሚያግዟቸውን ሰዎች ለማስተማር ጥረታቸው በከፈቷቸው ትምህርት ቤቶች ህልውና ብቻ ሳይሆን ለትምህርት ጉዳይ በሚያደርጉትም የቅርብ ክትትል ይስተዋላል፡፡ ከታናናሾች፣ ማለትም ከደሆችና የባላባት ዘር ካልሆኑት ወገን፣ የሚያስተምሯቸው ልጆች ከሚማሩበት አንዱ የነበረው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ያፈራቸው ልጆች አድገው የሚያመጡት ዓይነተኛ ለውጥ በታሪካችን ይታወሳል፡፡
‹‹ከመንደር ወሮበላነት›› እንዴት ወደ ኢጣሊያ ገዥነት እንደደረሰ ታሪኩ በዝርዝር የቀረበው ቤኒቶ ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን ለህልውናዋ የሚያሰጋት መሆኑ ከአድዋ ታሪክም ጋር ስለሚያያዝ የአንባቢን ፍላጎት የሚይዝ ነው፡፡ ኃይለሥላሴ ኢጣሊያን እንደጎበኙ ያስተናገዳቸው ሙሶሊኒ ለኢትዮያ የደገሰላትን ነገር በግልጽ አላሳየም ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ላይ ያጠላውን ‹‹ጥቁር ዳመና›› ለመቆስቆስ የተነሣው የወልወል ግጭት ‹‹አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ›› ዓይነት ነው፡፡ ይህች ዙሪያዋን በሦስት ቅኘ ገዥዎች የተከበበችው አገራችን ራሷን ለመከላከል የጦር መሳሪያ እንኳን እንዳታስገባ ተደርጋ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ላይ በተፈጸመው ወረራ ጉዳይ በቫቲካን አቋም ላይ በቀረበው ጥልቅ ምርምር እንደተመለከተው መንበረ ጴጥሮስ የፋሽስት ወረራ ተቃዋሚ እንደነበረችና ሊቀ ጳጳሱ ፓፓ ፒዮስም ኢትዮጵያን የሚወዱና ነጻነቷን የሚፈልጉ መሆናቸው ተገልጧል፡፡ እንዲያውም ተቃውሞ ሲያሰሙ ሙሶሊኒ ማስጠንቀቂያ አድርሷቸዋል፡፡ የተወሰኑት ጳጳሳት ግን ለፋሺስት ጦር ባደረጉት ድጋፍ ታሪክ ይወቅሳቸዋል፡፡ ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ ትጠይቅ የሚባለውም ይህን አስመልክቶ ሳይሆን አይቀርም፡፡
መሪዎቻቸውንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን በየጊዜው የሚለዋውጡት የፈረንሳይና የእንግሊዝ መንግስታት ለኢትዮጵያም ነጻነት በተደረጉት ንግግሮችና ውይይቶች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የፖለቲካ ጥቅማቸውንና አቋማቸውን በሚጠቅም መልኩ ሲያዩት ቆይተዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ በኢጣሊያ በ1928 በተወረረችበት ጊዜ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ (የመንግሥታቱ ማህበር) ተጠቂዋ አገር ባቀረበቻቸው አቤቱታዎች ተንጸባርቋል፡፡ ፈረንጆቹ አገራችንን መስዋዕት አድርገው ማቅረባቸው ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ ሶስቱ መንግስታት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ቀድሞ የተፈራረሙትን የምስጢር ውል እስከዚህ ጊዜ ድረስ እንደሚጠቀሙት ይታወቃል፡፡ የማህበሩ አባል አገራት በማዕቀብ ሊያስፈራሩት የሞከሩትን ሞሶሊኒን አንዳንዶቹ አገሮች በምስጢር ሲደግፉት ቆይተው በመጨረሻም ኢትዮጵያን መያዙ ግድ ሆነ፡፡ በዚህ በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በሰሜን ግንባሮች በነበረው ውጊያ የኢትዮጵያ ጦር የድርጅት፣ የአመራርና የመሳሪያ ማዕቀብ ችግር ቢኖርበትም፤ በተቻለው አቅም ለመከላከል ሞክሮ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ፋሺስቶች የተጠቀሙት በዓለም የተከለከለው የመርዝ ጋዝ የኢትዮያን ጦር ወደ መፈታት፣ ንጉሠ ነገሥቱን ወደ ስደት፣ የአርበኞንም እንቅስቃሴ ወደ መጀመር አደረሰው፡፡
የተፈራው ደርሶ ሙሶሊኒ ፊቱን ወደ ሂትለር በማዞር ወዳጅነቱን አጥብቆ እንግሊዝና ፈረንሳይን በማጥቃቱ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሊጀመር ቻለ፡፡ እንግሊዞች ኢትዮጵያን ለመርዳትና ፋሺስትን ከአገሪቱ ለማስወጣት በመወሰናቸው ከስደት ተመላሹ ንጉሠ ነገሥትና አርበኞችም በተሳተፉበት ዘመቻ ጣሊያን ከአገሪቱ ተባረረች፡፡ እንግሊዞችም ጣሊያንን ካስወጡ በኋላ የቅኝ አገዛዝ ዓይነት አስተዳደር ለመመስረት አስበው አስቸገሩ፡፡ ከብዙ ዲፕሎማሲያዊ ትግል በኋላም ከኦጋዴን በስተቀር ያሉትን ክፍሎች ለቀቁ፡፡ ‹‹የኤርትራን ጉዳይ›› የሚለው የዘውዴ ረታ ሌላኛው መጽሐፍ በኤርትራ በኩል ያለውን ሁኔታ ስለሚያትት በሱም ላይ የጻፍኩትን ማጠቃለያ ያንብቡ፡፡ የኢትዮጵያንና የእንግሊዝን ግንኙነት ለማስተካከል የቻሉት የአሜሪካ መሪዎች የአገራችን አዲሶቹ ደጋፊዎችና አጋሮች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
ቀጣዩን የመጽሐፉን ሰፊ ክፍል ይዞ የምናገኘው የአቶ መኮንን ሀብተወልድና የጸሐፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ የስልጣን ዘመን ነው፡፡ ሁለቱም የመንዝና የቡልጋ ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸው ህልም አይተውላቸው ወደ ቤተመንግስት እንዲጠጉ ያደረጓቸውና ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል የመጡ ነበሩ፡፡ ሁለቱም የቅርብ ጓደኝነት ያላቸውና ከአንድም በላይ ድርብ ሚኒስትርነት የተሰጣቸው ሰዎች በተራማጅነታቸው በንጉሳውያን ቤተሰብና በመሳፍንቱ ሊወደዱ አልቻሉም፡፡ ጸሐፌ ትዕዛዙ የንጉሡን ሥልጣን ሳይቀር እያሰጉ ሲመጡ ሲሻሩ፤ ሦስቱ የሀብተወልድ ወንድማማቾች በስልጣን ኮርቻ ላይ ቆይተዋል ማለት ይቻላል፡፡ የመኮንንና የወልደጊዮርጊስ መቃቃርም ተዳሷል፡፡ መኮንን ሀብተወልድ የሀገር ፍቅር ማህበርን የመሰረቱ ትጉህ ሰው ሲሆኑ ዓረብ ቤት የሚባለውን ዓረቦች በሃገሪቱ የተንሰራፉበትን የሱቅ ዘርፍ ለጉራጌ ተወላጆች ያስተላለፉ አገር ወዳድም ናቸው፡፡ ከምንም በላይ መኮንንን የሚያሳስባቸውና ለሃገር ፍቅር ቲአትር ታዳሚያን ይናገሩት የነበረው የሃገራችን አንድነት እንዳይናጋ ነበር፡፡
ጸሐፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስና የአቶ መኮንን ሀብተወልድ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግስትን የማዘመን ስራቸውን ለማጠናከር እንዲረዳቸው በማሰብ ከባላባቶች አንጻር በጀመሩት ስራ ምስለኔዎችንና ጭቃሹሞችን ሰብስበው ሲናገሩ የገለጹት ነጥብ ለአሁንም ስሜት ስለሚሰጥ አነሆ፡- ‹‹ኢትዮጵያ በአሥራ ሁለት ጠቅላይ ግዛቶች አንድትከፈል የተደረገው፤ ዘመናዊውን አስተዳደር ለመከተል የሚያመች እንዲሆን በማሰብ ስለሆነ፤ በዚህ አሠራር ሕዝቡ በጎሳና በዘር ልዩነት ተጠንቶ የተደረገ መስሎ እንዳይታየው በሚገባ ማስረዳት›› (611) እንዳለባቸው አሳስበዋቸዋል፡፡ አገራችን በጎሳ እንዳትከፋፈል፣ የግዛት አንድነቷ እንዳይነካና ዘመናዊነት እንዲገባ የሚጥሩት መኮንን ሀብተወልድ ከክቡር ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ጋር እንዳይሳሳቱብን ያስፈልጋል፡፡ ምክንየቱም እርሳቸውም በነሱ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ስለነበሩ ነው፡፡
በጣሊያን አገር ሰላሳ ዓመት የኖሩት ዘውዴ ረታ በንጉሠ ነገሥቱ መንግስት ወቅት የቤተመንግሥት ጋዜጠኛ ስለነበሩ፤ ያዩት የነበረውን የከፍተኛ ባለስልጣኖችንና የሃገሪቱን ፖለቲካ ሁኔታ የመመርመር ፍላጎት ስላደረባቸው በአውሮፓና በአሜሪካ እየተዘዋወሩ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የተጻፉትን ብርቅዬ ሰነዶች አንብበዋል፤ መርምረዋል፡፡ ከዚህም በላይ የታሪኩን ዋነኛ ተሳታፊዎች ወዳጆቻቸውን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ብዙ መረጃ ሰብስበዋል፡፡ ይህን መጽሐፍም ልዩና ጠለቅ ያለ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ይህ ነው፡፡
የዚህን መጽሐፍ ቀጣይ ክፍል፣ ማለትም ከ1948 እስከ 1967 የነበረውን የንጉሠ ነገሥቱን ታሪክ ደራሲው እያጻፉ ባለበት ሁኔታ ሕይወታቸው በማለፉ እስካሁን ባለን መረጃ ስለመጽሐፉ መውጣት ምንም የተሰማ ነገር ስለሌለ በልባዊ ሐዘን ለአምባሰደር ዘውዴ ምስጋናችንን ልናቀርብ ይገባናል፡፡

2017 ኖቬምበር 17, ዓርብ

ስለበይነ-መረብ አጠቃቀማችን




በይነ-መረብ (Internet) መኖሩን ያወኩት በ1996 ሳይሆን አይቀርም፡፡ በመሰናዶ ትምህርት ቤታችን፣ ኃይለማርያም ማሞ፣ ደብረ ብርሃን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ይሰጣል፡፡ በፊት ሒሳብ መምህራን የነበሩት ናቸው ይህን ትምህርት ያስተምሩ የጀመሩት፡፡ አንድ ጃፓናዊ መምህርም መጥቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ አንዳንድ ቀን ላብ ውስጥ ያስተምረን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ኮምፒውተር መኖሩን ሳይቀር ያወኩት ከዚህ ዓመት ብዙም አይቀድምም፡፡ በ1993 በአንዳንድ ቢሮዎች ውስጥ አይቼ ሊሆን ይችላል፡፡ ቴሌቪዥንን የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ያየሁት ሰው ለኮምፒውተር ብዙም አልዘገየሁም ማለት ይቻላል፡፡
በይነመረብን ልተዋወቅ የቻልኩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የኬኔዲ ቤተመጻሕፍት ነው፡፡ የባሌው ልጅ ጓደኛዬ ነው ያስተዋወቀን(ስሙ ባልሳሳት ከማል ይስለኛል - ይህን የምለው ውጤት ስላልሞላለት ትምህርቱን ሳይጨርስ ወደ አገርቤት ስለሄደ ጊዜው ስለረዘመ ነው)፡፡ ቤተመጻሕፍት ውስጥ ከካታሎጉ አጠገብ ብዙ ኮምፒውተሮች ያለምንም ተጠቃሚ ተከፍተዋል፡፡ ይህ ጓደኛዬም ብቻውን ይጠቀማል፡፡ አጠቃቀሙን ስጠይቀው አሳየኝ፡፡ ‹‹የምትፈልገውን ጻፍበት›› ሲለኝም ፍኩበትና ፈልጌ አገኘሁ፡፡ ይህ ቤተመጻሕፍት በቀን እስከ አራት ሰዓት ለሚሞላ ጊዜ ኢንተርኔት እጠቀምበት የነበረ ነው፡፡ አሰራሩ እንደዚህ ነበር፡፡ ጠዋት ከቁርስ በኋላ የኢንተርኔት ወረፋ ለመያዝ መታወቂያችንን ተራ እናስገባለን፡፡ ከዚያም ሰራተኞች ሲገቡ ይከፈትና እንጠቀማለን፡፡ እንዲህ እንዲህ እየተባለ ከትምህርት መልስ ጊዜው በኢንተርኔት ያልፍ ነበር፡፡ ያኔ እንደዛሬው ፌስቡክ የለም፡፡ ግፋ ቢል ፔንፓል ነው ያለው፡፡ አንዳንድ የዲያስፖራ ሚዲያዎን እከፍት እንደነበርና የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናዬ ከፍ ብሎ እንደነበር አስታውሳሁ፡፡ ግን ያኔ ፖለቲካን ያልኮመኮመ  ማን ነበር፡፡ ቦታው ለዚህ ክፍት ነበር፡፡ ጋዜጣው፣ ሬዲዮኑ (በቀን ለብዙ ሰዓታት ሬዲዮ አደምጥ ነበር) ምኑ ቅጡ፡፡ ጊዜው ደግሞ 1997 ነበር፡፡ ‹‹ትምህርቱ መቼ ይጠናል?›› ካላችሁ ልክ ናችሁ፡፡ ያው የእንግሊዝኛ ተማሪ ብዙም አያጠናም ነው መልሱ፡፡
አሁን የኢንተርኔት ሱስ ባመነመነኝ በዚህ ሰዓት-  ኢንተርኔትን ካወቅሁ 13 ዓመት በሆነኝ በአሁኑ ጊዜ - ባወራለት ጥሩ መሰለኝ፡፡ አጠቃቀማችን ላይ ላትኩር፡፡
1. ፌስቡክ ብቻ ለምን? የምንጠቀመው ማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ከሆነ ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡ ኢንተርኔት ውቅያኖስ ስለሆነ ወጣ ብለን ማየት አለብን፡፡
2. ጉግል በአማርኛ - ጉግልን እንደ መረጃ መፈለጊያ መጠቀም ትልቅ ብልህነት ነው፡፡ በእርግጥ ለኛ የቋንቋ ገደብ አለብን፡፡ እንግሊዝኛን በምቾት አንጠቀመውም፡፡ ለዚህ አንድ መፍትሔ አለው፡፡ ይኸውም የምንፈልገውን ነገር በአማርኛ ጽፈን ጉግል ላይ መፈለግ፡፡ ብዙ መረጃዎች ስላሉ ፈልጉ፡፡ አንዳንዴ በእንግሊዝኛ ከማገኘው የተሻለ በቋንቋዬ አገኛለሁ፡፡
3. ማንበብ ብቻ ሳይሆን መጻፍም - ማንበብ ብቻ ሳይሆን መጻፍም እንደምንችል የማናውቅ እንኖራለን፡፡ ዳውንሎድ ብቻ ሳይሆን አፕሎድም ማድረግ እንችላለን፡፡ ለዚህም በነጻ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ቦታዎች አሉ፡፡ እኔ የምጠቀምባቸውን ነገሮች ለአብነት እነሆ - http://mezemirethiopia.blogspot.com/
https://authenticethiopia.wordpress.com/
4. ጉግል - ጉግል ብዙ ነገር አለው፡፡ እኛ የምውቀው ጉግል ዌብ ብቻ፣ ምናልባት ምስል ከሆነ ገና ይቀረናል፡፡ ለምሁራን ምሁራዊ የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት ጉግል ስኮላርን እንጠቀም፡፡ ጉግል ኧርዝም አለ፡፡
5. ዩቱብ - ዩቱብ ላይ የተለያዩ ቪዲዮዎች አሉ፡፡ ታዋቂ የዓለማችን ዩኒቨርሲቲዎች ሳይቀሩ የሚያስተምሩትን ትምህርት ቪዲዮ ይለቃሉ፡፡ የኮርሳችንን ወይንም የምዕራፋችንን ስም ጽፈን መሞከር ነው፡፡
6. ኦንላይን መማር - ኦንላይን መማር እንደሚቻል የምናውቅ ስንቶቻችን እንሆን፡፡ በራስ ተነሳሽነት ቋንቋ፣ ኮምፒውተር፣ ሙዚቃ ወዘተ መማር ይቻላል፡፡ በነጻ የሚሰጡ ትምህርቶችን ተከታትለን ኮርሶችን ማጠቃለልም ይቻለናል፡፡ ለመማር open courseware አንዱ ቦታ ነው፡፡
7. ስማርት ፎን ላለው ሰው ደግሞ ሁሉ ነገር ቀና ነው፡፡ በተለይ ዋይፋይ ካለማ ምን ችግር አለ፡፡ እንግሊዝኛ መማሪያ ፖድካስቶችን ማለትም የድምጽ ፋይሎችን አውርዶ ማድመጥ አንዱ ነው፡፡ አፕሊኬሽኖችም እጅግ ጠቃሚ ናቸው፡፡
ተጨማሪ የምታጋሩት ካለ ኢንተርኔትን ብዙም ለማያውቅ ሰው ስለሚጠቅም መድረኩን እነሆ ብያለሁ፡፡

በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት

  በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት ረቡዕ፣ የካቲት 20፣ 2016 ዓ.ም. መዘምር ግርማ ደብረብርሃን   ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ ላምበረ...