ዓርብ 13 ሜይ 2022

I loved the shiny rain-boots and the blond hair!

 

By Mezemir Girma

A True Story 




One sunny winter morning in my home village, Sasit, I sat on a log with fellow children and adults in front of a small shop. Bare-feet and wearing locally sewn cheap clothes, we were chatting gazing at people passing by. Our backs rested on one of the walls of an iron-roof mud-house. How the rectangular houses are built is a witness to the transforming local architecture. They share one or more of their walls and many of them line up for a considerable distance. There is controllable flooding when it rains heavily because the way is closed for the flood. The dirt-road now has become mud-road. At sloppy places, you walk carefully to avoid slipping. Most people walked barefoot as we did. We went natural almost in every sense of the word. Just out of the blue, a man who wore rain-boots that were really clean and shiny started strutting. The black rain-boots were really unbelievable sight because there was no trace of mud in them. Did he descend from the sky! “How attractive are those rain-boots!” I exclaimed. Unexpectedly, the countryman pranced straight towards me and grabbed my ear. He squeezed and pinched my ear until it was very painful and got red. I didn’t understand the wrong I did if any. I didn't cry either. I remained seated my eyes wide open towards the man going along the way! Adding insult to injury, after the furious man left, one of those who sat beside me exclaimed, “You deserve it, don’t you!” This could be one of the mornings I was basking in the sun before having food, a typical morning. I was 13. When I see it in hindsight, the man didn’t come from the countryside wearing those boots as I expected. He walked to town barefoot, bought the boots from the shop next door and wore them. There was a misunderstanding among us. And very recently one of the guys who sat with me then, met me on the way and told me that that man had a marriage linkage with a wealthy family in the area. He added he died recently. I rather told him that I feel sorry about his death. Would I feel happy by the death of a man who pinched me after I said something he thought was bad seconds after he wore his new boots and started celebrating the success! 

At the the big hall of the Old Class Room Building, Institute of Language Studies, Addis Ababa University, we undergrads sat awaiting a movie to start. We were celebrating the European week with 27 embassies erecting tents on campus grounds and introducing their cultures. The film festival was a part of that and we had to go to cinemas throughout the town to watch European movies free of charge. This one was a Spanish movie. A tall beautiful Spanish woman came to officially open the movie show. She stood on the stage and started speaking in English with a Spanish accent. Her speech was on their culture and the context of the movie. I saw how she presented her point impeccably. More than anything, something attracted my attention. Unlike my German teacher, Moiken Jessen, this one cut her hair short. The slender woman’s hair looked beautiful to me.When these words left my mouth, I was almost made unconscious by her beauty: “How beautiful is she!” A boy sitting next to me was astounded and started to pour his appreciation to me for my remark. “Our people are not like this. We hide our feelings!” he whispered and kept telling me that I was an exception. He tried to explain his point further with examples, but there was no witness to this than myself owing to my experience five years before that. I felt proud and happy to be appreciated back for speaking the truth. This time, my feelings were accepted than questioned. No one took them to be sarcastic. I was 18. The difference between the rewards for expressing your appreciation in a village and a city is like that between sky and earth. 

 


 

ሐሙስ 5 ሜይ 2022

የጉዞ ማስታወሻ

 


ሚያዝያ 27፣ 2014

በመዘምር ግርማ

 


የዛሬው የጉዞ ማስታወሻ በጎበኘናቸው ስፍራዎች ሳይሆን ከእስከዛሬው ለየት ባሉና የሁላችንንም ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ይሆናል፡፡ የጽሑፉም ሁኔታ እኔ እጀማምረውና ሌሎች ተጓዦች የሚጨምሩበትና እናንተም አንባቢያን የምታስፋፉት ይሆናል፡፡ ከዚያም በተለይ መደረግ ባላባቸው ነገሮች ላይ ተግባራዊ ስራ ብንሰራ ደስተኛ ነኝ፡፡ እናንተም ደስተኛ የምትሆኑ ይመስለኛል፡፡

የመጀመሪያው የጉዞ ሰዓት መዘግየት ነው፡፡ ማለዳ 12፡30 ከአዲስ አበባ ለመነሳት ያሰቡት ተጓዦች 1፡00 መነሳታቸው ደብረ ብርሃን መድረሳቸው በመዳረሻ ቦታችን የነበረው ዝግጅት ከጀመረ በኋላ እንድንደርስ አድርጎናል፡፡ ለወደፊቱ የዝግጅቱ ዝርዝር መርሐግብር ተሰርቶ ሁሉንም ዝግጅቶች በሰዓታቸው ብናደርግ የሚል ዕይታ አለኝ፡፡ በእርግጥ እነ ጋሽ ጥላሁን ጣሰው አዲ አበባ ብሔራዊ ቲያትር ለሚካሄደው ‹ተከፍልናል› ለተባለው የሜላት ዳዊት ዘጋቢ ፊልም ምርቃት ተመልሰው መሄዳቸው፣ እኛ የቤተመጻሕፍቱ ሰዎች ለሳምንታዊው የሐሙስ ምሽት ዝግጅት ደብረብርሃን መድረሳችንና ማህደረ ሸዋዎች አዲስ አበባ ገብተው ማደራቸው የውሎገባ ዝግጅት መሆኑ ድንቅ ነው፡፡ ለወደፊቱ ብዙ ሰው በዚህ መልኩ ሊሳተፍና የፈለገም በዋዜማው ሊሄድ ወይም በማግስቱ ሊመጣ ይችላል፡፡ ጨምሩበት፡፡

በመኪና ውስጥ ያለውን ጊዜ ለማንበብና ለውይይት መጠቀማችንን ወድጄዋለሁ፡፡ ሁሉም ተጓዥ የተመደበለትን ክፍል አንብቦ ለጥንድ ውይይትም ሆነ ለሁሉም ተሳታፉ ማቅረቡ አንድን መጽሐፍ በአጭር ጊዜ ለመወያየት ሁነኛ መንገድ ነበር፡፡ ስንመለስ የተካሄደውንም ጥሩ ውይይት እመለስበታለሁ፡፡

ለበዓሉ ከማህደረሸዋ፣ ከራስ አበበ አረጋይም ሆነ ከወረዳው የተደረገው ዝግጅት ቆንጆ ነበር፡፡ ከራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት እንደ እስከዛሬ አባላትን መዝግበን በርከት ብለን መኪና ተከራይተን አለመምጣታችን አንድ ጉድለት ነው፡፡ ማህደረ ሸዋ ከጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ጋር ተነጋግሮ መኪና ስላስመደበ በዚያ ስምንት ሰዎች ልንሄድ ችለናል፡፡ ከወረዳውም በኩል ሰራተኞችን በሁለት መኪናዎች ማጓጓዛቸውና ማሳተፋቸው፣ የዕለቱን ዝግጅት በባለቤትነት መምራታቸው፣ የምሳ ግብዣ ማድረጋቸው ከብዙ በጥቂቱ የሚያስመሰግን ነው፡፡  ጥቃቅንና ለወደፊቱ ልናሻሸሽላቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የማይክራፎን ጉዳይ፡፡ ሌላ ደግሞ ቦታውን በጥሩ ሁኔታ ተጠቅሞ ሁሉም ሰው ጥግ ላይ ተቀምጦ፣ አንድ መድረክ አዘጋጅቶ ለቀረጻም አመቺ ስፍራ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

ከእስካዛሬው ለየት ያለው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ያሳየው የባለቤትነት ስሜት ነው፡፡ የዚህም አንዱ ማሳያ የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ አባሉ ደራሲ ጥላሁን ጣሰው በራሳቸው መኪና ቤተሰባቸውን ይዘው በዝግጅቱ መሳተፋቸው ነው፡፡ በስፍራውም ስለታሪካችን ትምህርት ከሰጡን በኋላ በስፍራው ማህበሩ ስላሰበው ልማት ገለጻ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ለወደፊቱ የኛም አስተዋሽነት አስፈላጊ ነው፡፡ ደራሲ ጥላሁን በአዲስ አበባ መሳተፍ ሲጠበቅባቸው ከእኛ ጋር በአንዲት ግራር ማክበራቸው ማህበሩ ለተመሰረተበት ቦታ ያለውን አክብሮትና ውለታ ያሳያል፡፡ ሌላም የማህበሩ አባል እኛ በነበርንበት መኪና ነበሩ፡፡ ብዙ ታሪክም ነግረውናል፡፡ ስለ ወደፊት ስራዎችም አውግተናል፡፡ ማህበሩ መኪና መመደቡም ትልቅ ውለታና አስተዋሽነት ስለሆነ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ይህም ለሌሎች አርአያ ነው፡፡ ለምሳሌ ከዓመታት በፊት ምኒልክ ዘኢትዮጵያ የጉዞ ማህበር፣ ደብረብርሃን ከቤተመሕፍቱ ለምንሄድ 30 ሰዎች የጉዞ ወጪ ሸፍኖልን ነበር፡፡  

ሌላው በስፍራው በበዓሉ አከባበር ላይ የታየው የፋኖና የአካባቢው ህዝብ ተሳትፎ ያላቸውን የአገር ፍቅር የሚያሳይ ነው፡፡ በዛሬው ዕለት ግማሹ የወረዳው አመራር የአራት ሚሊሻዎችን ቀብር ለማስፈጸም ስለሄደ እንዳልተገኘ ተነግሮናል፡፡ ስለዚህ አሁንም ያልተረጋጋ ሁኔታ እንዳለ ማየትና ከታሪክ አስተዋሽነት በላይ ማሰብ አለብን፡፡ ምናልባት የተጎዱትን ሚሊሻዎች ቤተሰብ እንዲሁም የቆሰሉትንም ለመደገፍ ሃሳብ ያለው ካለ የወረዳውን ኃላፊዎች አድራሻ እሰጣለሁ፡፡

በሰላድንጋይ ከተማ ከተካሄደው ውይይት የያዝናቸው ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም በወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት የቤተመጻሕፍት አገልግሎት እየጀመሩ ስለሆነ መጽሐፍ እንድንለግስ የጠየቁን ነው፡፡ በመልስ ጉዟችን በመኪና ውስጥ

ስንወያይ ተጓዦች ለመለገስ የሚችሉትን መጽሐፍ ቃል ገብተዋል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በየግላቸው ከሚያውቋቸው ሰዎችም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እንዲየሰባስቡ ተነጋግረዋል፡፡ ስለዚህ እኔም ያንኑ ጥሪ ተቀብዬ ከግሌ ሰላሳ መጽሐፍ ለመስጠት ቃል ገብቻለሁ፡፡ ይህም ዛሬ ለትምህርት ቤቶቹ ከሰጠኋቸው ሰላሳ መጻሕፍት በተጨማሪ ነው፡፡ ከዚያ በዘለለ እናንተ አንባብያን እንድትሰጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ ለዚህም ጉዳይ ብትጠይቁኝ ዝርዝር ሃሳቡን ለማጋራት ዝግጁ ነኝ፡፡

 መዘምር ግርማ

ደብረብርሃን

እንኳን ለድል ቀን አደረሰን!

ዓርብ 29 ኤፕሪል 2022

‹‹መጥፎ ትውልድ ስለሚመጣ ለክፋት እንዳይጠቀማቸው ከመጻሕፍቴ ጋር ቅበሩኝ››

 

መቶ አለቃ ላቀው ተሰማ

 



በቅርቡ በአገራችን በአገር በቀል ዕውቀት ላይ ያተኮሩ መጻሕፍት፣ የቴሌቭዥን ዝግጅቶችና ልዩ ልዩ ሁነቶች ስለበዙ በራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት፣ ደብረብርሃን፣ ሳምንታዊ የሐሙስ ምሽት (11፡30-1፡00) ውይይት ላይ በተለይም በሳምንቱ ምን አነበባችሁ በሚለው በመጀመሪያዎቹ ሃያ ደቂቃዎች ምዕራፍ ላይ ሃሳቦች ይነሳሉ፡፡ ተሳታፊዎች ያነበቡትን ከስሜታቸው፣ ዕውቀትና ልምዳቸው ጋር እያዋሃዱ ያጋሩናል፡፡ ከማንበብ በዘለለም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጥ ዘንድ እንግዳ እንዲጋበዝ በተጠየቀው መሰረት መቶ አለቃ ላቀው ተሰማ ተጋበዙ፡፡ ትናንት ሐሙስ 20/08/2014 ዓ.ም ዝግጅቱ ከመጀመሩ ግማሽ ሰዓት ቀድመው ከዕለቱ አዘጋጅ ጋር በቤተመጻሕፍቱ ተገኙ፡፡ እኔም ቤተመጻሕፍቱን የማስጎብኘት ተግባሬን ፈጽሜ ለዕለቱ ዝግጅት የሚጠቅም ወግ ጀማመርን፡፡

ከውይይቱ በፊት ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉ የተለመደ ነው፡፡ በእርግጥ የዕለቱ አዘጋጅና እንግዳው ያደረጉ ቢሆንም በጋራ አንዳንድ ነገሮችን ስናነሳሳ ቆየን፡፡ ስለ ንባብ ስንነጋገር በቤተመጻሕፍቱ ውስጥ ከማይነበቡ መጻሕፍት አንደኞቹ የታሪክ መጻሕፍት መሆናቸውን ገለጽኩ፡፡ ይህንንም እንድናርም መቶ አለቃ ላቀው አሳስበውናል፡፡ ይኸውም መጻሕፍቱን በማንበብና ለአባላት የተረዳነውን በማቅረብ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመውናል፡፡ የንባብ ልምዳቸውን፣ የሕይወት ገጠመኞቻቸውንና ጊዜው የፈቀደውን ሲያወጉን ቆይተው የዕለቱ ዝግጅት 1፡30 ላይ ተጀመረ፡፡ እርሳቸውም በሰዓቱ ለሁሉም ተሳታፊ ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በቤተክህነት፣ በወታደር ቤትና በፖለቲካ ያላቸውን ተሳትፎ ጨምረው ነበር፡፡ ‹‹የኔ ትውልድ አገሪቱን ችግር ውስጥ የከተተም ቢሆን ያዳናትም ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ችግር ቢኖርም በሶማሌ ጦርነት ብዙ ዋጋ ከፍለናል›› ብለውናል፡፡ በነበረው የእንግዳ ክፍለጊዜም ያነሷቸው ነጥቦች ሰፊ ቢሆኑም የተወሰኑትን አንኳር ነጥቦች በማስታወሻዬ ስለያዝኳቸው እነሆ፡፡

ከአሁን በፊት የግእዝ ዕውቀት ያለውና በዘመናዊውም ቴክኖሎጂ በዲግሪ ተመርቆ የሚሰራው ንጋቱ ግርማ በቤተመጻሕፍታችን እንዳቀረበልን ያለ ትምህርት ነው የመቶ አለቃም፡፡ የኢትዮጵያውን ዕውቀት ባላቸው ንባብና ግንዛቤ መጠን ከዉጪው ዓለም ጋር ያስተሳስሩታል፡፡ በአጠቃላይ ስንመዝነው አቀራረባቸው መንፈሳዊ አስተሳሰባቸውንና ያሉበት የንባብ ደረጃ ያሳየናል፡፡  በታሪክ፣ በአገርበቀል ዕውቀትና በኃይማኖት ላይ ያተኮረ ንባብ አላቸው ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

ከእለቱ አዘጋጅ ከፋሲል ገዳሙ የቀረበላቸው የመጀመሪያ ጥያቄ ‹‹ጥበብን እንዴት ያዩታል?›› የሚል ሲሆን፤ እርሳቸውም አባቶቻችን የነበራቸውን ጥበብና ዕውቀት ከብዙ በጥቂቱ አካፍለዋል፡፡ ይኸውም በግዕዝ የተጻፉትንና ልዩ ልዩ ይዘትና አጠቃቀም ያላቸውን መጻሕፍት በመጠቃቀስ ነው፡፡ ኦሪትን፣ የአክሱማውያንን፣ የዛግዌን፣ የመካከለኛውን ዘመን፣ የዘመናችንን የዕውቀትና ጥበብ አካሄድ በተለያዩ አብነቶች አነሳስተዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስም ንጉሥ ዳዊትን፣ ንጉሥ ሰለሞንንና ሌሎችንም ለንግግራቸውና ለምሳሌያቸው ማጠናከሪያ አንስተዋል፡፡

ንጋቱ ግርማ በትምህርቱ አንስቶልን የነበረውንና ከአገራችን ጥበቦች አንዱ የሆነውን መሰወርን ከስሪ ዲ፣ ፎር ዲ፣ …ሰቭን ዲ ጋር አያይዞት ነበር፡፡ እርሳቸውም መሰወርን ጨምሮ ዝናብ ማስቆምንና ማዝነብን አንስተዋል፡፡ በቅርቡ በቴሌቪዥን የሰሙትን ቻይናዎች ጎጃም ለመንገድ ስራ ላይ ዝናብ በአገሬው ባለሙያ እንዳስቆሙና አፄ ኃይለሥላሴ ጃማይካ ላይ ዝናብ የሚዘንብበትን ቀን ከደብተራ ጠይቀው መሄዳቸውን ከሌሎች መሰል አብነቶች ጋር ነገሩን፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ‹‹አባቶቻችን በአንድ ቀን ደብረ ብርሃንም ጎንደርም ይቀድሱ ነበር፤ በደመና በመጓዝ›› ይሉናል፡፡ ይህንንም ሊቃውንቱ ጥበባቸው መንፈሳዊነትና እግዚአብሔርን በመቅረብ የሚያደርጉ እንደሆነ ነግረውናል፡፡ ጥንቆላ በአንጻሩ በደንብ ያልተማሩና የማይመራመሩ የሚያደርጉት መሆኑን ጨምረዋል፡፡

‹‹እየሩሳሌም በአጋንንት ተገነባች፡፡ ለሰለሞን ነው አጋንንት የተሰጡት›› የሚለውን ጨምሮ የምሳሌዎቻቸው ማዳበሪያዎች ለእኔ አዳዲስ ነበሩ፡፡

የዕለቱ አዘጋጅ ለጠየቃቸው በርካታ ጥያቄዎች መልሶችን በአጥጋቢ ሁኔታ የመለሱት መቶ አለቃ ከተሳታፊዎችም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልሶችን ሰጥተዋል፡፡ ከሁሉም ያነጋገረውና ቤቱን በአንድ እግሩ ያቆመው ከአንዲት ተሳታፊ የመጣው ጥያቄ ነበር፡፡ ይህችም ለመጀመሪያ ጊዜ በግብዣ የመጣች ልጅ ራሷን ስትገልጽ አባቷ ጥበቡን የሚያውቁ እንደነበሩና እሷ ሳትወለድ አባቷ ለእናቷ ‹‹የሚወለደው ልጅ ወንድ ከሆነ ምንም ችግር አይኖርብንም፤ ሴት ከሆነች ግን አንቺ እንደወተለደች፣ እኔ ደግሞ ከስድስት ወር በኋላ እንሞታለን›› ብለው ለእናትዮዋ መናገራቸውን ነገረችን፡፡ ቃላቸውም እውን ሆኖ ሁለቱም ወላጆቿ ከተወለደች በኋላ መሞተቸውን ገለጸች፡፡ እርሷም አገር ጥላ መሄዷን፣ አባቷ ያወጡላትን ስም መቀየሯን፣ የሕይወት ፈተናዋን ምክንያት ለማወቅ መጽሐፋቸውን ጭምር በማንበብ መጣጣሯን ተናግራ መፍትሔ ጠየቀች፡፡ አሳዘነችን! መቶ አለቃም  ስለ ጉዳዩ ሲያስረዱ ይህን ዓይነት ነገር እንደሚከሰት ገልጸው አንዳንዴ በቤተሰቡ ላይ የሚመጣን መጥፎ ነገር ለማስቀረት ጽንስ እስከማቋረጥ ይደረሳል አሉ፡፡ ‹‹አባትሽ ያወጡልሽን ስም ተጠቀሚበት፤ አባትሽ ላንቺ ሲሉ ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ መመራመርና ማንበብም ከባድ ነው፤ አነበብኩ ያልሽው ፍትሐነገሥቱን ነው›› ብለው ሃሳብ ሰጧት፡፡ ካስፈለገ አባቷን አስነስቶ ማናገር እንደሚቻል ጠቅሰው ሙትን ረፍት መንሳት ስለማያሻ ይህን አንሄድበትም ብለዋል፡፡  አባቶቻችን መጥፎ ትውልድ ስለሚመጣ ለመጥፎ እንዳይጠቀመው ከመጻሕፍቴ ጋር ቅበሩኝ ይላሉም ብለውናል፡፡ የእሷም አባት ውሳኔ ይህ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ መላምት አእርሳቸውም ሆነ ከአባላት ተነሣ! መጯጯህም ሆነ! ከብዙ ምልልስም በኋላ  የቤተመጻሕፍቱ አባላት ይህን ትምህርት ለመማር ስለሚፈልጉ እንዲያግዟቸው ሲጠይቋቸውም ‹‹ምስጢሩ ጥልቅ ነው፤ ያለ ግእዝ ዕውቀት የሚሆን ነገር የለም፡፡ ከሦስቱ ‹ሀ› የቱን እንደምትጠቀሙ ካላወቃችሁ አይሰራም…›› ብለው የጉዳዩን ክብደት አስረድተዋል፡፡ በዚህም ብዙ ማጉረምረም ተከተለ፡፡ ‹‹የካቲት ጥሩ ወር ነው፡፡ አባቶቻችን በየካቲት አድዋ የቀናቸው ለዚያ ነው፡፡ ሰው እንደስሙ ይሆናል፡፡ ስንድር ስም እናያለን፡፡ ጥበቡ ሰፊ ስለሆነ ….››  ነገርን ነገር እያነሣው ብዙ አወጉ፡፡

ጥበብ፣ ጥንቆላ፣ አስማት፣ እርኩስ መንፈስ እያለ ከሚሄደው ወግ ወጣ ያለ ሃሳብ ያስተናገድነው በኔ ጥያቄዎች መሰረት ነው፡፡ እኔም የታሪክ አዋቂው ከመጡ አይቀር ዕድሉን ልጠቀም ብዬ ሦስት ጥያቄዎችን ጠየቅሁ፡፡ ከእነሱም አንዱ ክርስቲያናዊ ስላልሆነው የብሔረሰብ ጥበብ ምን ያስባሉ የሚል ሲሆን በሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አፄ ኃይለሥላሴ ጫምሲቱ ከሚባሉት የዝናብ ማስቆም ችሎታ ካላቸው ባለሙያዎች አንዱን ጋብዘው መጠቀማቸውን አነሳሁ፡፡ እርሳቸውም ይህንን አምነው ሐረርም ዝናብ ሲጠፋ ሴቶቹ እርጥብ ቅጠል ተሸክመው ከተማውን ሲዞሩ እንደሚዘንብ ገልጸውልናል፡፡ እንዳዩት በአመዛኙ የብሔረሰብ ጥበብ በቅጠላቅጠል መሆኑን ነገሩን፡፡ ሌላው ጥያቄ ስለተጉለት ነበር፡፡ እርሳቸውም የተጉለትን የሺዎች ዓመታት ታሪክ፣ እንዲሁም ከአፋር ጋር ስለሚዋሰን በቅድመታሪክም ያለውን ቦታ አስረድተውናል፡፡ ተጉለትን ስናነብ ግን ‹ጉ›ን አጥብቀን መሆን እንዳለበት አስረድተውናል፡፡ እንደዚያ ሲነበብም ትርጉሙ ላገሩ እድገት ተጣጣሩለት እንደሚሆን ነግረውናል፡፡  በራስ አበበ አረጋይ ስም ቤተመጻሕፍቱን መሰየሜንም ከተጉለት ጋር አያይዘውታል፡፡

እንደ ከተማው ነዋሪነታቸው የደብረብርሃንን ያለፉትን የሃያ ዓመታት ለውጥና የወደፊት ዕጣፈንታ በእርሳቸው ዕይታ እንዲነግሩንም ጠይቄ ነበር፡፡ ‹‹ደብረብርሃን አቀማመጧ ስለፈቀደላት ነው እዚህ የደረሰችው፡፡ ከዚህ የበለጠ ታድጋለች፡፡ ከአዲስ አበባም ትበልጣለች፡፡ አሁን ዘርዓያዕቆብ ቢመጡ አያውቋትም፡፡ በእናንተ ዕድሜ አንደኛ መዲና ቢቀር ሁለተኛ ትሆናለች፡፡ ከስምጥሸለቆና ከጂቡቲ ጋር ያላት ቅርበት፣ የአማራ ህዝብ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለው ትስስርና በብዝሃነት ደረጃ የኢትዮጵያ መገለጫ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡ በአዲስ አበባ የተፈጠረውን ትንግርት ማረጋጊያ ትሆናለች፡፡ ሙስሊሞችና ልዩ ልዩ ኃይማኖቶች መኖራቸውም የከተማዋን ህዝብ ስብጥር የሚያሳይና ለእድገቷ የሚጠቅም ነው፡፡›› ብለውናል፡፡ ‹‹ይሁን እንጂ በጥሩ ሁኔታ እያደገች አይደለም፡፡ አንድ ፎቅ ወደ ላይ እየወጣ ሌላው ታች ነው፡፡ ይህንን በብዙ ስብሰባዎች ተናግረናል፡፡ ሙስናው አፍኖ ይዟታል፡፡ እዚያ ላይ ምን ይሰራ የሚለው ያወያያል፡፡›› ሲሉም ጨምረውበታል፡፡

እኔ በግሌ ካሁን በፊት በተወሰነ መጠን ስለ መናፍስት መኖር በዩቱብ ቪዲዮ ‹‹ጎስት ሃውንቲንግ›› ላይ በቪዲዮ የሚታዩ መናፍስትንና የማናገር ጥበቦችን አይቼ ነበር፡፡ መቶ አለቃ ይህንን ፈረንጆች ከእኛ እንደወሰዱ ያላቸውን እምነት ሲነግሩን ጉዳዩ ምርምርና ፍተሻ የሚያሻው መሆኑ ታይቶኛል፡፡

በመጨረሻም ለቤተመጻሕፍቱ አባላት ምስጋናና ምክር ሲለግሱ ከመቀመጫቸው ተነስተው ነበር፡፡ ስናነብ እንዳንመርጥ፣ ተሰባስበን መወያየታችን የሚደነቅ መሆኑን፣ ወደፊትም እንደሚመጡና እንደሚሳተፉ በመናገር የዕለሩ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ጻፍኩ እንጂ ያወጉት ብዙና ጥልቅ ነው፡፡

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...