2021 ዲሴምበር 1, ረቡዕ

ለሁለት ሳምንታት በጦርነት ወላፈን ዳር - መዘምር ግርማ - ከደብረ ብርሃን

 ለሁለት ሳምንታት በጦርነት ወላፈን ዳር

መዘምር ግርማ

ከደብረ ብርሃን

ህዳር 22፣ 2014 ዓ.ም.

ከጀመረ አንድ ዓመት ያለፈው ጦርነት ብዙም ትኩረት ሳልሰጠው ወደምኖርበት ደብረ ብርሃን ከተማ እየቀረበ እየቀረበ መጣ፡፡ ስራ ስራዬን ስል ብዙም ክስተቶቹን አልተከታተልኳቸውም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የህወሃት ወራሪዎች ወደ ደቡብ ወሎ ሲገቡ ተነቃቃሁ፡፡ ሰሜን ሸዋን ሲወጉ የበለጠ ንቁ ሆንኩ፡፡ መረጃዎችን ከወዳጅ ዘመድ መቀያየር፣ ከሚዲያ መከታተልና ሁኔታዎችን ማጥናት ግድ አለኝ፡፡ የማገኘውን መረጃም ወገንን ለማንቃትና ለማስጠንቀቅ ተጠቀምኩበት፡፡ የኔን መረጃዎች ጠቀሜታ አስመልክቶ አራጋው አሰፋ  ‹‹ስለደብረ ብርሃን ሁኔታ ለማወቅ ያንተን ፌስቡክ ነው የምከታተለው፤ እውነተኛ መረጃ ስለምታቀርብ። በዚህ ወቅት እውነተኛ መረጃ ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ስለምታቀርበው እውነተኛ መረጃ አመሰግናለሁ›› ያሉት አጠቃላይ ሁኔታውን ይገልጸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

ሰሞኑን ዛሬን ጨምሮ ወገን በድል ላይ ድል እያጣጣመ ስለሆነ የነገሩ መጨረሻ ደርሷል ለማለት ያስደፍረኛል፡፡ ስለሆነም ያለፉትን ሁለት ሳምንታት አድራጎቴንና ሁኔታዬን ሙሉ በሙሉ ማስቃኘት ባልችልም ዋነኛው የመታገያ መንገዴ በነበረው በፌስቡክ Mezemir Girma የለቀኳቸውን ጽሑፎች ሰብስቤ ከዚህ መግቢያ ቀጥሎ አጋርቻለሁ፡፡ የትዊተሩም ቢኖርም ከቦታና ጊዜ አኳያ ትቼዋለሁ፡፡ የምትፈልጉ @authenthiopia ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡ መረጃዎቹን ያስቀመጥኩት ከቅርቡ ቀን ጀምሬ ወደኋላ ነው፡፡

በእነዚህ ሳምንታት ስጽፍና ወገንን ሳሳስብ፣ ሳተጋ መረጃዎቹን ያቀበሉኝን፣ ስሳሳት ያረሙኝንና መረጃዎቹን ተጠቅመው መልካም ስራዎችን የሰሩትን አመሰግናለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በትግሉ ውስጥ የተሳተፈውን ህዝብ፣ ሚሊሻዎች፣ ልዩ ኃይሎች፣ ፋኖና መከላከያ ሰራዊትን አመሰግናለሁ፡፡ የወገን ጦር ሲዋጋ በልዩልዩ መንገዶች ያገዘውን በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖረውን ህዝብም እንዲሁ፡፡ አጋር መንግስታትም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡

ያጋራኋቸው ጽሑፎች የተሟላ መረጃ ላይሰጡ ይችላሉ፡፡ የወደዷቸው፣ አስተያየት የሰጡና ያጋሩ ሰዎችን ሃሳብም ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡ የተወሰኑ በየዕለቱ የተከታተሉ ሰዎችም ይህን ስብስብ ስታገኙ በትዝታ ክስተቶቹን ታስታውሱ ይሆናል፡፡

መለስ ብዬ ሳየው የመጠቃት ስጋት በነበራት ከተማ መቆየቴ በተወሰነ መልኩ ራስን አደጋ ላይ መጣል ቢሆንም መንግስት እዚህ ድረስ መጥተው እስኪያጠቁ አለመጠበቁ ህይወታችንንም ሆነ ከተማችንን ታድጓል፡፡ ደብረብርሃን ግንባር ሳትባል ክፉ ቀንን አልፋዋች፡፡ ይህ ወቅት የሕይወቴ አስፈሪና አስጊው ወቅት ሊባል ይችላል፡፡ በቀን አንድ መቶ ስልክ የተደወለልኝ ቀን ነበር፡፡ የአዲስ አበባም ሆነ ሌላው ህዝብ በወያኔ ፕሮፓጋንዳና በሁኔታው መካረር ሰግቶ ነበር፡፡ የኔን ጽሑፎች በፌስቡክና በትዊተር የሚከታተልበትም ምክንያት ይገባኛል፡፡

እንግዲህ ጊዜው ይህን ዘመቻ አጠናቆ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋሚያና አገርን መገንቢያ ነው፡፡ ለዚህም ሁላችንም በኢትዮጵያዊ አንድነት መረባረብ አለብን፡፡ የዘረኝነትን ሰንኮፍ ካልነቀልን ምን ያህል አደጋ ላይ እንደሆንን ከዚህ ወቅት በላይ አስተማሪ የለም፡፡ ይህ ጽሑፍ ጦርነቱን አስመልክቶ የመጨረሻዬ ቢሆን ደስተኛ ነኝ፡፡

 

‹‹Gashena has been freed by ENDF! Congratulations to all Ethiopians!›› ዲሴምበር 1

‹‹የዛሬው የወያኔ ፍርጠጣ የፋሺስት ወታደሮች ከኢትዮጵያ የወጡበትን ሁኔታ ያስታውሳል፡፡ ተስፋ የቆረጡትም ‹‹አዲዮ ሮማ›› እያሉ ሽጉጣቸውን መጠጣታቸውን ያስታውሷል፡፡›› ዲሴምበር 1

‹‹አቤት ሌሊቱን የነበረው የጁንታው የሽሽት ሩጫ! የት ነው የምትሸሸው 360 ዲግሪ ተከበህ! ከሰሞኑ ገበሬው መሬታችንን አረከሱት ሲል ነበር የከረመው፡፡ አሁንም ብዙ አስከሬን ተጨምሯልና እያነሳህ ወደ ድንበሩ ላይ ከምር አርሶአደር ሆይ! ባገር የመጣውን ምን ታደርገዋለህ! የትና እንዴት የሚለውን የሚመለከተው ክፍል ይነግረናል፡፡›› ዲሴምበር 1

‹‹ኧረ ምንድነው ነገሩ? ደብረብርሃን ሕዝቡ እየጨፈረ ነው መከላከያ ደግሞ ከኦራል ላይ ኮቸሮ ያድላል። ሦስት ደረሰኝ። ጠዋት ዘግይቼ እንደተረዳሁት የድል ዜና ሰምተው ነው።›› ኖቬምበር 30

‹‹የወሎ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያመሰግናል!

You are my heroes

This afternoon I felt so elated to see the mattresses and food you sent to the IDPs in Debre Birhan. Our brothers and sisters from Wollo need this very much since they are sleeping on the cold concrete floors of the schools and organizations that sheltered them.›› ኖቬምበር 30

 

‹‹ወያኔ ተጉለት ላይ አስወርቶት የነበረው ፕሮፓጋንዳ

1. ፈጣሪ እዚህ ድረስ ካመጣቸው እኛ እንዴት እናስቆማቸዋለን!

2. ጥይት አይመታቸውም!

3. እዚህ የደረሱት በጥንቆላቸው ነው!

4. ንግር አለ፡፡ አባቶች ትንቢት አለ ብለዋል፡፡ 2014/2015

ወሬው አልሰራም! ሁለቴ አልተታለልንም፡፡ እኛም ቀድመን ጠርጥረን ተዘጋጅተንበት ነበር፡፡

እናንተስ ምን አስወሩ?››  ኖቬምበር 30

 

‹‹በዕድሜ ዘመኔ ሰምቻቸው የማላውቅ፣ እንዲሁም ከህዝብ የተደበቁ የሚመስሉ ስለኢትዮጵያ የተዜሙ ዘፈኖች፣ የአገራችን ታሪኮች፣ የጦር ሜዳ ውሎዎች፣ የጀግኖች ገጠመኞችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሰሞኑን በመገናኛ ብዙኃን እየተላለፉ ነው፡፡ ይህ ተግባር ወደፊትም ቢኖር የአገር አንድነት ይመጣል፡፡›› ኖቬምበር 30

‹‹ጠላት እየገሰገሰ ሲመጣ ሊያስቆመው የፈለገ አካል ያለ አይመስልም ነበር፡፡ የመንግሥት የማጥቃት ውሳኔ ግን ነገሩን ሁሉ ቀየረው፡፡ ከገቡበት ወጥመድ መውጣት አልተቻላቸውም፡፡ ቀድመው ያዘጋጁትን የድል ድርሰት መልቀቅን ግን አሁንም ተያይዘውታል፡፡ ቅዠታቸው በሌላ ቦታዎች ያሉትን ሲያስደነግጥ እኛን ግን ፈገግ ያስብለናል!›› ኖቬምበር 30

‹‹ማክሰኞ ሕዳር 21 2014

ከደብረብርሃን ሠላምታችን ይድረሳችሁ። ወደ ከተማችን የመጡ ተፈናቃዮችን እናግዝ። ጦሩን እንደግፍ። ኢትዮጵያ እያሸነፈች ነው!›› ኖቬምበር 30

‹‹ዛሬ ሰኞ ደግሞ የወሬ ቋቱ በከባድ ስራ ላይ ነው የዋለው። ስለ ደብረብርሃን በየፌስቡክና ትዊተሩ ሲሞነጫጭሩ ስለዋሉ ሰው ሁሉ ይደውልልኛል። ይጽፍልኛል። ለማናቸውም ደብረብርሃን ምንም የተለየ ነገር የለም። ሁሉም ስራውን ሲሰራ ሰላማዊ ቀን ነው ያሳለፈው። አሁን ወሬው ደሴና ወልድያ እንዴት አመሹ ነው።›› ኖቬምበር 29

‹‹አንድ ወቅት ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ባቀረበው ምርምር የአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ድርሰት እኔ ለአገሬ፣ የደርግ ዘመን እኔ ለአብዮቱ፣ የኢህአዴግ ደግሞ እኔ ለኪሴ የሚል አስተሳሰብ እንደሚንጸባረቅበት መናገሩ ይታወሰኛል።

ሰሞኑን ወገን ለአገራችን ህልውና የሚያደርገውን ርብርብ ሳይ የእኔ ለአገሬ ጊዜ እየተመለሰ መሆኑን እገምታለሁ። የጠላትን እንቅስቃሴ ወገን ሊያውቅ የሚችለው በሁላችንም ከገጠር እስከ ከተማ ባለነው ንቃትና የመረጃ ፍሰት ነው። ከእረኛ እስከ ምሁር ያለንን ጥረት ታዘብኩ። ቀን ከሌሊት በየሙያችን፣ ዕውቀትና አመለካከታችን የምናደርገውን እገዛ ማየቴ በአገሬ የበለጠ ተስፋ እንዳደርግ አድርጎኛል።›› ኖቬምበር 28

 

‹‹በሰላማዊቷ ከተማዬ ደብረብርሃን የተለመደውን የጠዋት የእግር ጉዞ ሳደርግ የተወሰኑ ፎቶዎችን አንስቻለሁ። ሰንበትና የቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ ዕለት በመገጣጠማቸው ከጠባሴ ገብርኤል የሚመለሰው ምዕመን መንገዱ ላይ በዝቶ ይታያል።

መልካም ቀን ኢትዮጵያዬ!›› ኖቬምበር 28

 

‹‹ለጓደኞቼ

የደብረብርሃንን ውበት እያደነቃችሁ አንድ ወይም ሁለት ቀን ለመዝናናት ጊዜና ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖቼ ብቅ በሉ። አስጎበኛችኋለሁ። ተማሪም ስለሌለና ትምህርት ስላልተጀመረ እረፍት ላይ ነኝ። አድራሻዬን በውስጥ መስመር ጠይቁኝ።›› ኖቬምበር 27

‹‹ጥንቃቄ

መንዝ ላይ እንደነበረው ሁሉ በሌሎችም የሰሜን ሸዋ ወረዳዎች በመንገድ ሥራ ሰበብ ወያኔ በስልጣን ሳለ የቀበራቸው ከባድ መሳሪያዎች ካሉ በአስቸኳይ በመሳሪያ ተመርምረው ይውጡና የወገን ጦር ይጠቀምባቸው።›› ኖቬምበር 27

 

‹‹የደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ 09 የዩኒቨርስቲ መምህራን ኮንዶሚኒየም ማህበረሰብ ለወገኖቻችን ስላደረግነው ድጋፍ አጭር መግለጫ

በዚህ ወቅት ከተለያዩ የክልላችን ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖቻችን አቅም በፈቀደ ድጋፍ አድርገናል። ይህም ድጋፍ የወር ደምወዛችንን ለመከላከያ ከሰጠነው፣ በየቦታው ለልዩ ልዩ ድጋፍ ከምናዋጣው፣ በመስሪያ ቤታችን በስንቅ ማደራጀትና በቁስለኞች ህክምና ከምናደርገውና በየተጠየቅንበት በጉልበት ከምንሰራው በተጨማሪ እንደ መኖሪያ ግቢ ማህበረሰቡን በማስተባበር የተደረገ የበጎፈቃድ ስራ ነው። ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይቀርባል።

አንድነት ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተፈናቃዮች

8 ከረጢት ሩዝ (እያንዳንዱ 25 ኪግ የሚይዝ) በድምሩ 2 ኩንታል ዋጋው 6800 ብር የሆነ፣

9 ከረጢት መኮረኒ (እያንዳንዱ 25 ኪግ የሚይዝ) 2.25 ኩንታል ዋጋው 9675 ብር የሆነ፣

10 ኩንታል ልዩ ልዩና በተለያዩ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ወገኖች የሚሆኑ አልባሳት፣

3 ፍራሾች፣

1000 ሰዎች ቁርስ ዳቦ በሻይ አብልተናል። ዋጋው 4250 ብር የሆነ፣

ምሳ 1300 ሰዎች አብልተናል። አንድነት ትቤት ላሉትና

ሰን ዱቄት ፊትለፊት ካለው አዳራሽ ለሚገኙ 300 ተፈናቃይ ወጣቶች መሆኑ ነው። ዋጋው 16,290 የሆነ፣

ከዚህም በተጨማሪ ከቀበሌ 09 ማህበረሰብ ጋር በመተባበር 6045 ብር ከእኛ እና ከህብረተሰቡ 4200 ብር ተዋጥቶ ከቀበሌያችን ማለትም ከቀበሌ 09 ወደ ግንባር ለዘመቱ ሚሊሻዎች 26 ፎጣ፣ 2 ካርቶን ቫዝሊን ብዛቱ 288 500 ምላጭ፣ 500 መርፌና ክር ልከናል። ይህም አስፈላጊ የሆነና ዘማቾቹ ሊቀርብልን ይገባል ያሉትን አንገብጋቢ ነገር ጠይቀን ነው።

ያደረግነው እገዛ የአቅማችንን ያህል አስተዋጽኦ ለማድረግ፣ ለወገናችን አለኝታነታችንን ለማሳየት እንዲሁም ችግራቸው የሚሰማን መሆኑን ለማሳየት ነው።

ከዚህ በዘለለ ለወደፊቱም በዕውቀት፣ ክህሎትና ጉልበታችን ወገናችን እስኪቋቋምና በቤቱ እስኪገባ ድረስ ለማገልገል ዝግጁ ስለሆንን በዩኒቨርስቲውም ሆነ በቀበሌያችን ጥሪ ቢደረግልን በደስታ እንተባበራለን። በከተማችን፣ በክልላችን፣ በሌሎች ከተሞችና አካባቢዎች፣ እንዲሁም በዉጪ አገራት የምትገኙ ወገኖች የአቅማችሁን እንድትደግፉ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ወገኖቻችን ከቤታቸው ወጥተው ብዙ ነገር ባልተሟላበት ሁኔታ ለመኖር እንደተገደዱ ልብ እንበል።

በቀበሌ 09 የዩኒቨርስቲው ኮንዶሚኒየም የምንኖር መምህራን ወገኖቻችሁ።›› ኖቬምበር 27

 

‹‹የቃፊር ስርዓት

የቃፊርን አሰራር መጀመር ያስፈልገናል። ይህም ጠላት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲዘዋወር ስናይ ለወገን የምናሳውቅበት የግንኙነት ሰንሰለት ነው። አሰራሩም ለጠላት በቅርብ እርቀት ላይ ያለ ሰው በርቀት ያለ ወገን እንዲዘጋጅ የሚነግርበት ነው። ያለ ስልክ ይነገርበት የነበረው ስርዓት ጮሆ በመናገር ወይም በተኩስ በማሳወቅ ይከናወናል። ይህን የማስጠንቀቂያ መልዕክት የሰማ ወገን ለቀጣዩ እየነገረ ሁሉም ይዘጋጃል። እነ ራስ አበበ በአርበኝነት ዘመን ከጦር ሰፈራቸው በየተወሰነ እርቀት ቃፊሮችን ያቆሙ ነበር። ጠላት ሲመጣም አንዱ ለሌላው ሲያሳውቅ የጦር ሰፈሩ በአጭር ጊዜ ለመከላከል ወይም ለማጥቃት ይዘጋጃል። አሁንም ስልክ ባይኖር፣ ባይሰራ ወይም በአንዳች ምክንያት ግንኙነት ቢቋረጥ የቃፊር ስርዓት ጥሩ አማራጭ ነው። ይህን ስርዓት ብንጠቀም ኖሮ ብዙ መንደሮች በጠላት እየተወረሩ ወጣቶች ለጥይት ማብረጃ በግዳጅ አይመለመሉም ነበር። ሌሎቹም ጥፋቶች ይቀሩ ነበር። እንነጋገርበት። ላልሰማ እናሰማ።›› ኖቬምበር 27

‹‹በየአካባቢያችን አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ነቅተን መጠበቅና መመርመር እንደሚያስፈልገን ይበልጥ የምንገነዘበው በመንዝ ወያኔ በስልጣን ላይ እንደነበረ መንገድ ሲሰራ የቀበረውን ታንክና ከባድ መሳሪያ ሰሞኑን ቆፍሮ ማውጣቱን ስንሰማ ነው።

ሰዎቹ ከጣሊያን የተማሩት ብዙ ነው።›› ኖቬምበር 27

‹‹ቶሎ ፈርመን ከውጤት እናድርሰው።›› ዶክተር እሌኒ ከኃላፊነቷ እንድትነሳ የሚጠይቀውን የፊርማ ማሰባሰቢያ ገጽ ሳጋራኖቬምበር 27

‹‹ትናንት የሳሲቱ ቆራጥ ወታደር ሻምበል Betselot Sasit Hilemichael በወታደራዊ መኪና ሊጠይቀኝ ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ መጥቶ ነበር። እሱና ጓደኛው በመኪናቸው ይዘውኝ ሄዱ። ወታደራዊ መኪና ውስጥ ስገባ የመጀመሪያዬ ነበር። ትንሽ ያስፈራል። መኪናው ቦቴ ነው። የጫኑት ነዳጅ እንደሆነ ጠየኳቸው። ነዳጅ ሳይሆን ዉኃ መሆኑን ነገሩኝ። ለምን እንደሚጠቀሙት ስጠይቃቸው ለወታደሩ ለመጠጥ በየግንባሩ የሚደርስ መሆኑን ነገሩኝ። በየቦታው ዉኃ ላይኖር ስለሚችል ይህን ማድረግ ግድ ይላል። ጦሩ ምን ያህል መስዋዕትነት እየከፈለ እንደሚያኖረን አስቤ ተገረምኩ። አከበርኳቸው። ጦስኝ አምባ ሆቴል ሻይ ቡና ጋብዘውኝ ተለያየን። ወደ ግዳጅ ሄዱ።

መከላከያን፣ ልዩ ኃይሉን፣ ፋኖንና ሚሊሻን እንደግፍ!›› ኖቬምበር 27

‹‹We thank the numerous groups of patriots coming to Debre Birhan to donate food and clothes to the IDPs and the army. Even if the fighting is going far north, we should assist from peaceful areas like Debre Birhan. Donate directly to the army, IDPs, not me or somebody else.›› ኖቬምበር 26

‹‹ጤና ይስጥልኝ

ደብረብርሃን የተለመደ ሰላማዊ ቀን አሳልፋለች።

በደህና እደሩ።›› ኖቬምበር 26

 

‹‹በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰበር ዜና ተላልፏል። ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጦር ግንባር የድል ዜና አስተላልፈዋል።

Breaking News on ETV

PM Dr Abiy Ahmed has declared the victories achieved so far from the frontlines.›› ኖቬምበር 26

‹‹አርብ ሕዳር 17 ከሰዓት በኋላ

እንዴት ናችሁ?

ለመከላከያ፣ ለልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ ማድረግ ስላለብን ድጋፍ አስተያየት ለመስጠት ያህል የምንሰጠው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሮች፣ በቀበሌ ገበሬ ማህበራት፣ በድርጅቶች ወዘተ የተደራጀና ብዛት ያለው ቢሆን የተሻለ ነው። ይህም አንድ መኪና እህል፣ ልብስ፣ በርከት ያለ ትኩስ ምግብ ወዘተ መሆኑ ነው።

እዚህ ሱቆች፣ ቡቲኮች፣ ባንኮች፣ ግሮሰሪዎች፣ ሆቴሎች ወዘተ ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ነው።

መዘምር ግርማ

ከደብረብርሃን›› ኖቬምበር 26

 

‹‹አርብ ሕዳር 17 2014

ሠላም እንዴት አደራችሁ? እኛ ደህና ነን። የወገን ጦር ከፍተኛ ቁጥር ያለው በመሆኑ በርከት ያለ የምግብና የዕለት መገልገያ ቁሳቁስ እገዛ እንደሚያስፈልግ አንድ እገዛ ለማድረስ ሄዶ የነበረ ወዳጄ ነግሮኛል። ስለሆነም በዚህ የድላችን የመጨረሻው ምዕራፍ ለእርዳታ እንረባረብ። ድል በድል እየተንበሻበሽን መሆኑን ከየቦታው እየተረዳሁ ነው። የወያኔ ወታደሮች በጥቂት ቁጥሮች ተቆራርጠው በቀሩባቸው ቦታዎች ወደ ትግራይ የመመለሻ ዕድላቸው ተሟጦ ማለቁን ለህብረተሰቡ እየተናገሩ መሆኑን ሰምቻለሁ። ለማናቸውም መንግስት መሐሪ ስለሆነ እጅ ቢሰጡ እንደሚሻላቸው እንመክራለን።

መዘምር ግርማ

ከደብረብርሃን›› ረቡዕ ህዳር 15

‹‹በሉ በደህና እደሩ።

ለሰዓታት ሳትለጥፍ ስትቀርና ስትጠፋ እንጨነቃለን ላላችሁኝ ነገ አርብ ጠዋት 3:00 በኋላ እንደምመለስ በመግለጽ ልሰናበት። ምክንያቱም ዋይፋይ እንጂ ሞባይል ዳታ ስለሌለ ነው። እስከዚያው ጦራችን ከደሴ የሚልክልንን የድል ዜና እንጠብቅ።›› ረቡዕ ህዳር 15

 

‹‹የምስራች

የወገን ጦር የጠላትን ወታደር እየቀጠቀጠ ከአዲስ አበባ 376 ኪሎሜትር ላይ ደርሷል።

እያጋራን

Congratulations

ENDF and our popular forces have driven the terrorists as far as Kombolcha, 376 kms from Addis.

Share›› ረቡዕ ህዳር 15

‹‹ስለ ደብረብርሃን ለምትጠይቁ ኮምቦልቻ ደርሰውላችኋል።›› ረቡዕ ህዳር 15

‹‹ደብረብርሃን ዛሬ ከሰዓት በኋላ

ትናንት በተላለፈው መመሪያ መሰረት በየጎዳናው ለመተላለፍ የከተማዋን መታወቂያ መያዝ ግድ ሆኗል። በግምት በየ100 ሜትሩ መታወቂያ እንድናሳይ እየተጠየቅን ነው። ይህም ጥሩ ነው። ሰላም ነን። ለወገን ጦር ስንቅ እየተደራጀና እየተላከ ሲሆን፤ በድልም እየተንበሻበሽን ነው።›› ኖቬምበር 25

‹‹እነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ከፈረንጆቹ ጋር የዶለቱበት የቪዲዮ ውይይት መሉ ቃል›› ሐሙስ ህዳር 16

 

‹‹ዛሬ ሐሙስ ህዳር 16 2014 ..

ደብረብርሃን ከተማ እንደተለመደው ሰላም ነች፡፡ መከላከያን፣ ልዩ ኃይሎችን፣ ፋኖና ሚሊሻን እንደግፍ፡፡ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!

Today, Thursday, November 25, 2021 Debre Birhan is peaceful. Addis Ababa is also peaceful. Ethiopia prevails!›› ሐሙስ ህዳር 16

‹‹ማስታወቂያ

ከዛሬ ሐሙስ ህዳር 16 2014 ቀን ጀምሮ በደብረብርሃን ከተማ መንቀሳቀስ የሚችለው የከተማው መታወቂያ ያለው ግለሰብ ብቻ እንደሆነ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የቤት ለቤት ፍተሻም ቢካሄድ ጥሩ ነው፡፡›› ኖቬምበር 24

‹‹ከእስራኤል የኢትዮጵያውያን ቴሌቪዥን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት ረቡዕ ከደብረብርሃን ካደረኩት ውይይት በአጭሩ›› ኖቬምበር 24

 

‹‹ሞላሌ ላይ ያለው የጠላት ጦር በእግረኛና ከሰላድንጋይ በመድፍ እየታጨደ ነው። ሞፈር ዉኃ ጅረትን አልተሻገረም።›› ኖቬምበር 24

‹‹ለወገን ጦር የሚጠቅም መረጃ ስናሰራጭ ከማህበራዊ ሚዲያ ይልቅ በስልክና በአካል ቢሆን ይመረጣል። እኔም የእናንተን ምክር ሰምቼ የጠላትን አሰፋፈር፣ ብዛት፣ እንቅስቃሴና የትጥቅ ይዞታ መረጃ ሲደርሰኝ ለወገን እያደረስኩ ነው።›› ኖቬምበር 24

 

‹‹አልጀዚራ አረብኛ ደብረፅዮን ሞተ ብሎእየዘገበ መሆኑን አንድ ሰው ነገረኝ። የሰማ አለ?›› ኖቬምበር 24

 

‹‹ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!

ከመከላከያ፣ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ ጎን ነን›› ኖቬምበር 24

‹‹ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች

ረቡዕ ሕዳር 15 2014 ..

ወደ ከተማችሁ እየመጣ ያለ ምንም ጦር የለም። እየመጣ የነበረው በመንዝ፣ በደብረሲና፣ በሸዋሮቢት ወዘተ ተቀብሯል። ቦታዎቹን ለማታውቋቸው ጠላት ለአዲስ አበባ 190 ኪሎሜትር ቀርቦ ነበር። ይህም ደብረሲና ድረስ ማለት ነው። ደብረብርሃን ከአዲስ አበባ 130 ኪሎሜትር ትርቃለች። ፈጽሞ ጠላት አልተጠጋትም። ዘመቻውን በቻላችሁት መጠን ደግፉ። ብዙ ከተሞች ነፃ እየወጡ ነው። በፕሮፓጋንዳ እንዳትሸበሩ።

መዘምር ግርማ

ከደብረብርሃን›› ኖቬምበር 24

‹‹Jerusalem Post has published Fasil Legesse's meticulously written article on the situation in Ethiopia. Please read and share it. የእስራኤል ቴሌቪዥኑ ጋዜጠኛ ወዳጄ ፋሲል ለገሰ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በጀሩሳሌም ፖስት ላይ የጻፈውን ቆንጆ ጽሑፍ እነሆ። ያንብቡት። ያጋሩት።›› ኖቬምበር 24

‹‹ደብረብርሃን ዛሬ ረቡዕ

ደብረብርሃን ፍጹም ሰላማዊ ነች። ብዙ የንግድ ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች ተከፍተዋል። ሰውም ይንቀሳቀሳል። Debre Birhan is peaceful today.›› ኖቬምበር 24

‹‹ጠላት ወደ ደብረብርሃን ሲጠጋ አስግተውኝ የነበሩ ክስተቶች

(አሁን ነገሩ በማለፉና ኢትዮጵያ በማሸነፏ ለትውስታ የተለጠፈ)

1. ጠባሴ፣ ደብረብርሃን ላይ ሄሊኮፕተር አረፈ። ለመውረድ ሲያንዣብብ አይቻለሁ። ምን ሊሰራ መጣ በማለት የጠየኳቸው "ወታደራዊ ቦርሳ ሊወስድ ነበር። መኪኖች አቀበሉት። ሄደ።" የሚል መረጃ ሰማሁ። ይህን ካሁን በፊት ካለኝ የወታደራዊ ጉዳዮች ግንዛቤ አንፃር አገናዘብኩት። ብርጌዱ ሊሸነፍና ሊበተን የሚችልበት አዝማሚያ ካለ ምስጢራዊ ሰነዶች የተሻለ ሰላም ወዳለበት ቦታ ይላካሉ። ይህ ትዝ ብሎኝ ሰጋሁ። ደነገጥኩ።

2. ተቋማት ወሳኝ ዕቃዎቻቸውን አሸሹ። ይህ ደሴም ከመያዟ ሁለት ቀናት በፊት ታይቷል። የቴሌና ሌሎች መስሪያ ቤቶች ዕቃዎች ወደ ሸዋሮቢት መጥተዋል።

3. የተወሰኑም ቢሆኑ እስረኞች ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረዋል።

4. ያየኋቸው የተወሰኑም ቢሆኑ አመራሮች ሸሽተዋል።

5. ባደረኩት ምልከታ እና ጓደኞቼንም ጠይቄ ባረጋገጥኩት መሰረት ከደብረብርሃን ወደ ሌሎች ቦታዎች የሸሹት በብዛት የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸው። ይህም የወያኔን የሸዋ አማራ ጥላቻ በመገንዘብ ዘር ተኮር ጭፍጨፋን በመፍራት ይመስላል።›› ኖቬምበር 23

‹‹ደብረብርሃን ላይ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው

1. ከካምፕ ዉጪ የሚዞሩ ስደተኞችና ለከተማው አዲስ የሆኑ ሰዎች

2. የማናቸውንም የፀጥታ ኃይል የደንብ ልብስ ሳይለብሱ የጦር መሳሪያ አንግተው የሚዞሩ ሲቪሎች

3. ሐሳብ ለመስጠትም ሆነ ስራ ለማገዝ ሲፈለጉ በስራ ቦታቸው የማይገኙ ኃላፊዎች

4. ለፀጥታ አስጊ ናቸው ተብለው ተጠርጥረው ታስረው የተፈቱ ሰዎች ይመስሉኛል።

ትኩረት! ትኩረት!›› ኖቬምበር 23

‹‹መረጃ

በደብረሲና ስር በወፍዋሻ አድርገው ጣርማበር ያለውን የወገን ጦር ለመቁረጥ እየሄዱ እንደሆነ መልዕክት ደርሶኛል። ስለሆነም ጥንቃቄ ይደረግ። ይሁን እንጂ የዚህን መረጃም ትክክለኛነት ለማጣራት ይሞከር።›› ኖቬምበር 23

‹‹የጠባሴ ወጣቶች ደብረብርሃን ላይ ለወገን ጦር የገቢ ማሰባሰቢያ እያደረጉና እኛም እያገዝን ነው።

Fundraising for the army on the road in Debre Birhan›› ኖቬምበር 23

‹‹አዎ! የአማራ ሕዝብ ትጥቁን አይፈታም! የማረከውንም ያስቀምጥ! መደራጀቱና ለክፉ ቀን መዘጋጀቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። በክፉ ቀን የደረሰብንን አይተናል።›› ኖቬምበር 23

‹‹ግብፅ ቱርክን ለኢትዮጵያ አትሽጪብኝ ያለቻቸው ድሮኖች በዚህ የመጨረሻ ሰዓት አድነውናል። ወደ ደብረብርሃን ለመተላለፍ በሰሜን ሸዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች እየተመመ ያለውን የወያኔ ሰራዊት እንደ ቅጠል እያረገፉት ነው። እናመሰግናለን ቱርክ!›› ኖቬምበር 23

‹‹የጥንቃቄ መልዕክት ለጦሩ

በመንዝ የገቡት የወያኔ ወታደሮች አሁን ወደራ ደርሰዋል። ወጣቱን እያስገደዱ እያሰለፉ ነው። ዓላማቸው ጣርማበር ላይ ያለውን ጦር ከኋላ ለመውጋት ይመስላል። ከታች ከደብረሲና ካለው ጦራቸው ጋር የጦሩን ትኩረት ሳይበትኑት መመታት አለባቸው። አሁን ያሉበት በግምት ከጣርማበር 15-20 ኪሎሜትር ይርቃል። ብዛታቸውን አላወኩም። ተሽከርካሪ እንዳያንቀሳቅሱም መመታት አለባቸው። ምክንያቱም ወደ ደብረብርሃን ለመቅረብ የሚያስችላቸው የሞጃ ጠጠር መንገድ ከደብረብርሃን የአየር ርቀቱ 22 ኪሎሜትር ገደማ ስለሚሆን በመድፍ ጥቃት እንዳይፈጽሙ ነው። ለዚህም መድሐኒቱ ከሞላሌ ሰላድንጋይ ያለውን መንገድ መጠበቅ ነው።›› ኖቬምበር 23

‹‹ከእስራኤል የኢትዮጵያውያን ቴሌቪዥን ጋር እንደወትሮው በዙም ሳይሆን በስልክ ትናንት ቃለመጠይቅ አድርጌ ነበር። እዚህ ስላለው የወገን ጦር የበላይነት ነግሬያቸዋለሁ። የደብረብርሃንንም ሰላም መሆን ተረድተዋል። የህዝቡንም በተጠንቀቅ መቆም እንዲሁ። በእየሩሳሌም ስላካሄዱት የድጋፍ ሰልፍም በኩራት ነገሩኝ። ቃለመጠይቁ ከተጠናቀቀ በኋላ እንደገና ደውለው አንድ ነገር ጠየቁኝ። ለአንዳንድ ነገር እንዲሆንህ ገንዘብ እንላክልህ የሚል ነበር ጥያቄው። በጣም ደስታ ተሰማኝ። በወገኔ ኮራሁ። ይሁን እንጂ ለወገናዊ ተቆርቋሪነታቸው አመስግኜ እዚህ የሃብት ችግር እንደሌለ አስረድቼ ገንዘብ የመላኩን ሃሳብ አስተውኳቸው። ብቸገር ነገ የሚሰጡኝ ገንዘብ ስለሆነ ወገኖቼ እንደሰጡኝ እቆጥረዋለሁ። በውጪ ያላችሁ ወገኖቻችንን ሁሉ ለማይነጥፍ የአገርና የወገን ፍቅራችሁ እናመሰግናለን።›› ኖቬምበር 23

‹‹I just talked to Tom Gardner of The Economist. Thank you for your interest in the situation in Debre Birhan and Shewa.

ከዘኢኮኖሚስት ዘጋቢ ቶም ጋርድነር ጋር በደብረብርሃን ስላለው ሁኔታ በስልክ አውርተናል።›› ኖቬምበር 23

 

‹‹ዳግማዊ አድዋ ድል ተቃርቧል። የዘመናችንም ኢትዮጵያዊ እና መሪው እንደ አፄ ምኒልክና የዘመናቸው ህዝብ ሁሉ በነጮችና ተላላኪዎቻቸው ላይ ድል ይቀዳጃል! ኢትዮጵያ ታሸኔፋለች!›› ኖቬምበር 23

‹‹እንደ ደባርቁ ከንቲባ ማን ይሆናል!

የደባርቁ ከንቲባ የተወሰኑ የከተማው ሰዎች ወያኔ ወረራ ሲፈጽም ሊሸሹ እንደሞከሩ ሰብስቦ አናገራቸው። "አትሂዱ አንላችሁም። መሄድ ትችላላችሁ። በኋላ ግን ደባርቅ ላይ ቤት አለን ብላችሁ ለመመለስ እንዳታስቡ!" አላቸው። ከዚያ ሁሉም ሰጥ ለጥ ብለው ወደ ግንባር ተመሙ። የሆነው እንዲህ ነበር። የተወሰኑ ግለሰቦች ለመሸሽ ቢያስቡም አብዛኛው የደባርቅ ህዝብ የወያኔ ጦር እየገሰገሰ ለከተማዋ አንድ ኪሎሜትር ተቃርቧል መባሉን ሲሰማ ጦር፣ ጎራዴ፣ ቢለዋ፣ ጠመንጃ፣ ያለውን ሁሉ እየያዘ ተመመ። መከላከያ ሰራዊትንም ቀድሞ ሄደ። በዚህ ጊዜ መከላከያና ህዝቡ ወደ ወያኔ እሽቅድድም ያዙ። መሸሽ ሳይሆን ማሯሯጥ ቀጠለ። የደባርቅ ወጣት በአንድ ቀን ብዙ የተሰዋውና የተቀበረው በከፍተኛ ወኔ ከእጁ የገባውን መሳሪያ ይዞ ከወያኔ ወታደሮች ጋር አንገት ለአንገት ሲተናነቅ ነው። ትናንት ከደባርቅና ጎንደር ሁለት ጓደኞቼ ይህንኑ አስታውሰው ደብረብርሃንም ጫጫ ላይ መንገዱን ዘግታ ማናቸውም ነዋሪ እንዳይወጣ አድርጋ ወያኔን መፋለምና ትግሉን ህዝባዊ ማድረግ አለባት ብለውኛል። ልክ ነው። ይህን ማድረግ ያስፈልጋል። ጦርነቱ እየተጠናቀቀ ነው። በእርግጠኝነት እናሸንፋለን!

ታዲያ ጨዋታ ጨዋታን ያነሳዋል እንዲሉ ከደባርቁ ከንቲባ በተቃራኒው ያሉ አመራሮችን ሽሽት ባየን ጊዜ የተሰማን ስሜት ከባድ ነበር። ለጦርነቱ ማገልገል ያለበትን የመንግስት መኪና እየያዙና በስንት ወታደር እየታጀቡ ዕቃቸውን ጭነው የሸሹትን አይተናል። እንኳን ህዝቡን አትሽሽ እያሉ ሊገስፁ! ቀድሞ በተለያዩ መንፈሳዊና ዓለማዊ ማህበራት የተደራጁ ወጣቶች በየከተማው ኬላ አቁመው ሲፈትሹና እየተዟዟሩ ሲያበረታቱና ሰቃኙ ስታዩ በትውልዱ ትበረታታላችሁ።

ሁሉም ህዝብ ለጦርነቱ በድል መጠናቀቅ ይረባረብ። የአመራር ለውጥ ለማምጣትናና የአካባቢን ደህንነት ለማስጠበቅ ሰፊ ስራ መሰራት አለበት።

መዘምር ግርማ

ከደብረብርሃን›› ኖቬምበር 23

‹‹ደብረብርሃን ሕዳር 13

የተወሰኑ ተማሪዎች ትምህርት አለ ብለው ትምህርት ቤት ሄደው ሲመለሱ አይተን አነጋግረናል። እንረጋጋ። ተማሪዎቻችን በለጡን። ሠላም ነን። Students coming back from school in Debre Birhan today›› ኖቬምበር 22

‹‹የሰላድንጋይ ሰው ወደ ከተማው እየተመለሰ መሆኑን እየሰማሁ ነው። ከተማው ላይ ሳትፋለሙ ሽፍትነት ለምን አስፈለገ! ! ወያኔ ተመቷል!›› ኖቬምበር 22

 

‹‹ደብረብርሃን ዛሬ ማለዳ

ደህና ነን። ወያኔ እንቁልልጭ። የኢንዱስትሪ ከተማ ሊዘረፍ!

ሕዳር 13 2014

Debre Birhan this morning. All is well. ›› ኖቬምበር 22

‹‹Morning update from Debre Birhan

We are safe. The town is in the government's hands. Enemy advance is blocked. At Tarmaber, 50 kms from here, our army has a huge presence. According to sources enemy troops were being attacked by air in North Shewa all over the night.

Mezemir Girma

Debre Birhan›› ኖቬምበር 22

‹‹ እንዴት አደራችሁ? ደብረብርሃን ሠላም ነች። ጠላት መምጫ የለውም። ሌሊቱን በየገጠሩ ለመምጣት ሲሞክር በአየር ሲደበደብ አድሯል። ቢሆንም ሳንዘናጋ አካባቢያችንን እንጠብቅ። ሰርጎ ገቦችን እናጋልጥ።›› ኖቬምበር 22

‹‹Under the America sponsored genocide

I'm in Debre Birhan. While people I knew flew away to Addis Ababa to save their lives, I'm still at Debre Birhan. I could go to Addis a few days ago, but why? After my people fall victims to a U.S. sponsored genocide by the Tigray People's Liberation Front, what use would being alive have? Currently, the Oromia Regional State is forbidding people of Amhara ethnicity, whose ethnicity could be found out from their identification cards, from entering to the metropolis. It is their capital city. One can see how the Amhara people are cornered! In the photo I posted here you see me posing with my book which is a translation of a book on the Rwandan genocide. This afternoon, I was the attendant at Ras Abebe Aregay Library, a library I opened in town. Readers came to discuss the U.S. sponsored genocide and ways to curb it. After the discussion I asked them to take this photo that you see attached.

My plan is to join the patriots who are fighting in rural areas nearby.

Hopefully, I will come back with another post.  ››  ኖቬምበር 21

‹‹የጦርነት ወቅት ወግ

ዛሬ ሕዳር 12 በጀግኖች አገር ሸዋ፣ ደብረብርሃን

ራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት ከሰዓት በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ተከፍቶ ነበር። ጠዋትም ለተወሰነ ጊዜ ከፍቻለሁ። የጦርነቱን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልኩ ዋይፋይ ወዳለበት እየሄድኩ መረጃ ሳደርስ ውያለሁ። ከሰዓት በኋላ በርከት ያሉ መምህራን በራስ አበበ አረጋይ ቤት ተገኝተው ሲመክሩ ሳይ ጀግናው ራስ አበበ አረጋይ ያኔ ፋሺስት ጣሊያንን ለመመከት በጅሩ ዋዩ ከአርበኞች ጋር የመከሩበት ጊዜ ትዝ አለኝ። ብቻቸውን ነበር ከአዲስ አበባ የወጡት። የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዥ ነበሩ። በመጨረሻም በአስር ሺዎች ሠራዊት አሰባስበው የኢትዮጵያን ባንዲራ ለማውለብለብ በቁ። ጣሊያንም በአምስት ዓመት ከአገራችን በሽንፈት ወጣች። እነሆ በቤተመጻሕፍታችን ከተገኙት አንባብያን ጋር ከመከርን በኋላ አንዲት ፎቶ አንሱኝ አልኳቸው። ይህም ፎቶ 2008 .. የታተመው የትርጉም ስራዬ ሁቱትሲ ነው። የኢማኪዩሌ ማስታወሻ የሆነው ይህ መጽሐፍ ስለ ቱትሲ ዘር ማጥፋት ያወሳል። ትዕይንቶቹ ዓይኔ ላይ አሉ። በዚህ ቀውጢ ወቅት ደብረብርሃንን ትተናት አንሄድም። እንፋለምላታለን እንጂ!

ይህን ስናስብ ወገን በየአጎራባች ወረዳዎች የወያኔን ሠራዊት እየደመሰሰው መሆኑን መስማት ያኮራል። በሰላድንጋይ ተመትተዋል። ድሮኑም እስከ ሞላሌ ጨፍጭፏቸዋል። በሌላ ወሬ እመለሳለሁ።

ደብረብርሃን ሰላም ነች። በየቦታው ያለውን ወገን እንዲፋለም በስልክ እየደወላችሁ ንገሩልን። ሞባይል ዳታ የለም።

መዘምር ግርማ

ደብረብርሃን ›› በራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት የፌስቡክ ቡድን ኖቬምበር 21

‹‹ በመንዝና ተጉለት ግንባሮች ያለ አንድ ወንድማችን የሚሸሸውን "የታባክ ነው የምትሸሸው!" (ያለውን ቃል በቃል) እያለ ወያኔን መውጫ መግቢያ አሳጥቶታል። ተጉለቶችም ሰላድንጋይን አላስደፈሩም። መልሰውታል! ሌሎቻችሁም በየወረዳውና ዞኑ ያለውን ህዝብ እንደዚህ እንዲያጠቃ አድርጉ።

በጥላቻና በዘረኝነት ከሆነ ማንም መሬታችንን አይረግጣትም። ለወደፊቱ ያሰቡ ካሉም ጥሩ ትምህርት ነው። እኔ ጉግል ማፕስ ላይ የቦታ እርቀት እየለካሁ ስሌት በመስራት በስልክ እያስተላለፍኩ ነው። አሁንም ደብረብርሃን ነኝ።

ከእናንተ የሚጠበቀው የሚመስለኝ

ለፍልሚያ መነሳትና ማነሳሳት፣

በየቦታው ህዝቡ እየሸሸ ከሚመታ ወደ አጥቂነት እንዲቀየር መምከር፣

ለትግሉ ድጋፍ ማድረግ፣

ንብረት ዘርፎ ጭኖ የሚሄድ የወያኔ መኪና ካለ ጎማውን መምታት!››  ኖቬምበር 21

‹‹መረጃ ከሰሜን ሸዋ

የወገን ጦር ሠላድንጋይ ላይ በመድፍ እያጠቃ ነው። ከሞላሌም አዛዦቹ የሠላድንጋይ ልጆች ስለሆኑ ጠላት ተቆርጧል። እስካሁን 17 የወያኔ ወታደሮች በኛ ጦር ተደምስሰዋል። ሌሊቱን ሠላድንጋይ ተያዘ የተባለው ስህተት ነው። ሁላችንም ጠንክረን እንፋለማለን። ከከተማ ወጥቶ ማገዝም ካስፈለገ እየተዘጋጀን ነው።

የመንግሥት ዕቅድ እስካሁን አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው። ኢንተርኔት በዋይፋይ ነው እየተጠቀምኩ ያለሁት። ከዚያ ውጪ ኢንተርኔት ሁልጊዜ ስለማላገኝ እንደዋወል።

ደብረብርሃንን አስመልክቶ

በከተማችን ውስጥ ያለው ሥራ መሰራት አለበት። መጥራት ያለበት ይጥራ። ህግ አስከባሪዎች ቅድመ-መከላከል መስራት ይኖርባቸዋል። አካባቢያችንን እንጠብቅ።

ለመረጃ ያህል- ሠላድንጋይ የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና ከተማ ነች። በመንዝ ትዋሰናለች። አሁን ወደ ሠላድንጋይ የመጡት ሞላሌን አልፈው ነው።

ሞጃና ወደራ ወረዳን አልፎ ባሶና ወራና ወረዳ አለ። ከዚያም ደብረብርሃን። ከደብረብርሃን ወደ ሞጃ በአቋራጭ ለመሄድ የስድስት ወይም ሰባት ሰዓት የእግር መንገድ ነው።

 ›› ኖቬምበር 21

‹‹ደብረብርሃንና ሸዋ ማድረግ ካለበት ውስጥ

አስቸኳይና ድንገተኛ የቤት ለቤት ፍተሻ ይደረግ።

ድርጅቶችና አሳቻ ቦታዎች ይፈተሹ።

በየ100 ሜትሩ ኬላ ይኑር። ፍተሻም መታወቂያ ማሳየትም ግዳጅ ይሁን።

በየሰፈሩ ለእያንዳንዱ ሰው ተከታታይ ይመደብ። ይህም እርስበርስ ማለት ነው።

በአጭሩ እንደ ጎንደር ራሳችንን ለማስከበር እንነሳ።

የማይዘነጋው ጉዳይ ለጦሩ ድጋፍ ማድረግና በዘመቻው መሳተፍ ነው።

እናንተም ጨምሩበት። እንወያይበት።

ይህን ለማስፈጸም የትኛውን የዞኑንና የከተማውን መስሪያ ቤት እንጠይቅ።››  ኖቬምበር 21

‹‹ የአማራ ክልል በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ሐብቱ ወድሞ እንዲህ በኢኮኖሚ እንዲንኮታኮት ከተፈረደበት ከጦርነቱ በኋላ አንድ የዉጪ አገር ከተማ ላይ ዓለምአቀፍ ቴሌቶንና መሰል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ሊደረግለት ይገባል። ሌላም ብዙ ነገር! ›› ኖቬምበር 20

‹‹ወሬ እንዳይፈታን!

በሠሜን ሸዋ በየወረዳው ከመቶ ሺህ በላይ ህዝብ አለ። በአሁኑ ሰዓት በመንዝ የተያዘው ስትራቴጂ አንድ መቶ የማይሞሉ የጠላት ወራሪዎች መጥተው የወረዳውን ከተማ ያሸብራሉ። ነዋሪው ከከተማ ገጠር ወደሚኖር ዘመዱ ስለሄደ ከተማውን ያለ ተኩስ ይይዙታል። አመራሩም የጠፋባቸው ቦታዎች ነበሩ። ከዚያ ስህተት ተምረን አካባቢያችንን መከላከል አለብን። ይህን ለማስተካከል እየተሰራ መሆኑን ተረድቻለሁ። አስር እየሆንን አንዱን መጣል አያቅተንም። ወያኔ በሠሜን ሸዋ እንዲቀበር ሁሉም መስራት አለበት። በስልክ በየአካባቢው ያለ ወገናችንን እናበረታታ። የመረጃ እጥረት እንዳይፈጠር።›› ኖቬምበር 20

 

‹‹በመንዝ የመጡት ወያኔዎች ጥቂቶች ናቸው። በተጉለት፣ በሸሾ፣ በአዳባይ የአካባቢው ጦር ተዘጋጅቷል። ወደ ተጉለት ከመድረሳቸው በፊት የመንዝ ሕዝብ በየገቡበት እንዲመታቸው በስልክ ለምናውቃቸው እየደወልን እናሳስብ። በየገበሬው ቤት እየገቡ እኛ እናንተን አንነካም የሚሉት ውሸታቸው ነው። ይህንንም አስገንዝቡ። መጋፈጥና መፋለም ባለድል ያደርገናል።›› ኖቬምበር 20 

‹‹ጥንቃቄ ይደረግ። መንዝ ውስጥ ያሉት ቁጥራቸው ጥቂት ነው። በየአካባቢው ያለው ሚኒሻና ሕዝብ ባሉበት ሊያስቀራቸው ይችላል።›› ኖቬምበር 20

‹‹ደብረብርሃን ያረፉ የተጎዱ የጦሩ አባላት ክራንች የላቸውም። ባለፉት ሳምንታት በአነስተኛ አጭር እንጨት፣ በተወላገደ እንጨት፣ በፍልጥ ወዘተ ሲመረኮዙ አይቻለሁ። ክራንች ያስፈልጋቸዋል። ይህም ለእርዳታ ከሚመጡ ነገሮች ጋር ቢካተት ጥሩ መሰለኝ። ›› ኖቬምበር 19

‹‹ኢትዮጵያዊ ለሆነ ሁሉ እንደ አፋርና ሶማሌ ክልሎች የአገር ፍቅር ስሜት የሚያስደስተው የለም!  ›› ኖቬምበር 19

‹‹የበፊቱን ማጭበርበሪያ አሁንም እየተጠቀሙበት ነው። ዉኃ ቅዱ፣ እህል አስፈጩ ዓይነት ማስፈራሪያ በወሬኞቻቸው በኩል ያሰራጫሉ። ከዚህም የበላለጠ የሚያሸብር ወሬ ይነዛሉ። በዚህም መሰረት የከተሞችን ሰላም ያውካሉ። ካላስፈላጊ ወሬና ሽብር ፈጠራ እንጠበቅ። ቤተሰብ፣ ጎረቤትና መንደራችንን እናንቃ።›› ኖቬምበር 19

‹‹የቤልጂየም ኢትዮጵያውያን ሰልፍ። ከሃያ በላይ የዓለም ከተሞች ሰልፍ ይወጣባቸዋል።›› ኖቬምበር 19



በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት

  በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት ረቡዕ፣ የካቲት 20፣ 2016 ዓ.ም. መዘምር ግርማ ደብረብርሃን   ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ ላምበረ...