2017 ኤፕሪል 7, ዓርብ

የሳምንቱ ግብዣዬ




እጅግ የተከበሩ ማስተር አርቲስት የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ በኮንግረስ ቤተመጻሕፍት፣ አሜሪካ፣ ያደረጉት ንግግር
ዶክተር ፔጊ ተርልስቲን፣ በቤተመጻሕፍቱ የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ ክፍል የሂብሩ ክፍል ኃላፊ የመክፈቻ ንግግር አደረጉ፡፡ የኢትዮጵያን አምባሳደር ዶክተር ሳሙኤል አሰፋንም ለዝግጅቱ ስላደረጉላቸው ትብብር አመሰገኑ፡፡
የቤተመጻሕፍቱ ሰራተኛ አቶ ፋንታሁን ጥሩነህ አርቲስቱን አስተዋወቀ፡፡
እርሳቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ማግኘቱ እንዳስደሰተው ገልጾ  በእርሱ እድሜ ላሉ ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ መሆናቸውን አስረዳ፡፡  ‹‹የዚህም ምክንያቱ አርቲስቱ የልዕልና፣ የታማኝነት፣ የስራና የሀገር ፍቅርን ችቦ በማውለብለብ የተነሳሽነት ምንጭ መሆናቸው መሆኑን አከለበት፡፡ ፈንታሁን ሲቀጥል ‹‹ለዚህም ሁሉ ከአርቲስቱ ሕይወት በላይ ምስክር የለም፡፡ በተወለደበት አገር ያልተወሰነው ህይወቱ በዓለም ዙሪያ ባሉ የመገናኛ ብዙሃን የተነገረና የዓለም ሎሬት ያስባለው ነው፡፡ ቀጥሎ አጭር ግን የማይመጥነውን የሕይወቱን መግቢያ አቀርባለሁ›› ሲል ቀጠለ፡፡
‹‹አፈወርቅ በአንኮበር፣ ኢትዮጵያ፣ በ1932 ተወልዶ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኢጣሊያ አገዛዝ ስር አደገ፡፡  ከነጻነት በኋላ በ1947 የማዕድን ማውጣት ምህንድስና ለማጥናት ወደ እንግሊዝ አገር ተጓዘ፡፡ ይሁን እንጂ ለጥበብ በነበረው መሰጠት ምክንያት በለንደን ያለውን የጥበብና ቀረጻ ትምህርት ቤት ተቀላቀለ፡፡ ስዕል፣ ቅርጻቅርጽና አርክቴክቸር የተማረበትን የስሌይድ ትምህርት ቤት ሲቀላቀል የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተማሪ ነበር፡፡ ወደ አገሩ ከተመለሰም በኋላ የአገሩን ባህልና ጥበብ ለማጥናትና በጥበብ ስራዎቹ ለማንጸባረቅ የትውልድ አገሩን ክፍላተ-ሀገራት ዞረ፡፡ በ1954 በአዲስ አበባ የብቻውን ትዕይንት አሳይቶ ሲያበቃ አውሮፓን ለሁለት ዓመታትተዟዙሮ የመስታወት ላይ ስዕል አሰራርን ለማጥናት የሚያስችለውን ገንዘብ አገኘ፡፡ በእንግሊዙ ብሪቲሽ ቤተመጻሕፍት፣ በፈረንሳዩ ቢብሎቴክ ናትሲዮናልና በጣሊያኑ ቫቲካን አብያተመጻሕፍት ስለኢትዮጵያ የድርሳን ውስጥ ስዕሎች ላይ ጥናት አደረገ፡፡ በ1958 አፈወርቅ በአፍሪካ አዳራሽ (በአፍሪካ የምጣኔሃብት ኮሚሽን) ያለውን የመስኮት ላይ ድንቅ የመስታወት ስዕል ሰራ፡፡ ሦስቱ መስታወቶች 150 ስኩየር ሜትር ሲሸፍኑ፣ አፍሪካ ያሳለፈችውን ሰቆቃ፣ የወቅቱን የነጻነት ትግልና የወደፊቱን ተስፋ ያሳያሉ፡፡ በ1964 አፈወርቅ የኃይለስላሴ ሽልማት የስዕልና ቅርጻቅርጽ የመጀመሪያው ሎሬት ሆነ፡፡ በውጭ አገራት ዝናው እየናኘ ሲመጣ በሞስኮ አውደ-ርዕይ አሳይቶ፣ ስለስዕል ገለጻም እያደረገ፣ ሶቭየት ህብረትን ለመጎብኘት ቻለ፡፡ በዩናይትድ ስቴትስም በዋሺንግተንና ኒውዮርክ የብቻው ኤግዚቢሽን እንዲያሳይ ተጋብዞ ነበር፡፡ በአሜሪካን ዩኒቨርሲዎችም ስለስዕል ገለጻ አድርጓል፡፡ በሴኔጋል፣ ቱርክ፣ ዛየር፣ ዩናይትድ አረብ ሪፓብሊክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሙኒክ፣ ኬንያና አልጀሪያም ተመሳሳይ ዓለም አቀፍ ትዕይንቶን አቅርቧል፡፡ በ1980 አፈወርቅ በሶቪየት ዩኒየን (በሞስኮው የፑሽኪን ሙዚየምና በራሽያ ብሔራዊ ሙዚየም በሌኒንግራድ) የብቻውን ትዕይንት አቀረበ፡፡ ከሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎችም በርካታ የጥበብ አድናቂዎችንና ሐያስያንን ስቦ ነበር፡፡ ከአፍሪካ አህጉር እጅግ የተከበረና ድንቅ የ20ኛው ክፍለዘመን አርቲስት በመባል እውቅና ሲሰጠው እጅግ ከፍተኛውን የሰላምና የወዳጅነት ጀግንነት ሸልማትም ተሸልሟል፡፡…..››
ማስተዋወቁ ረጅም ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የዕውቅናው ሂደት ቀጥሎ ነበር፡፡ አፈወርቅ በንግግሩ ድንቅ ገጠመኞችን፣ወደ ሃገሩ የመመለስን ፍላጎት፣ የምቀኝነትን መሰናክል፣ የኢትዮጵያን ጥበብ ሁኔታና ሌሎችንም ስለዳሰሰ ዩቲዩብ ላይ ገብታችሁ ሙሉውን እንድታነቡትና እንድትደመሙ፣ እንደሱም እንድትተጉ ይሁን፡፡ The State of Art in Ethiopia

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት

  በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት ረቡዕ፣ የካቲት 20፣ 2016 ዓ.ም. መዘምር ግርማ ደብረብርሃን   ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ ላምበረ...