እሑድ 19 ጁን 2022

በጠባሴ መድኃኔዓለም ትምህርት ቤት ከሰባት ዓመታት በኋላ - አይ አገሬ!

 

በመዘምር ግርማ

12/10/2014 ዓ.ም.

 

ከሰባት ዓመታት በፊት የማውቀውን ይህን ትምህርት ቤት ከዛሬ ነገ እጎበኘዋለሁ ስል ስንት ጊዜ ሆነኝ፡፡ በዚህ ዓመት የአሜሪካ የሠላም ጓዶችን ስራ መልሶ ለማየትና ለማነቃቃት በማሰብ ሽር ጉድ ስል መጀመሪያ ከመጡልኝ አንዱ ይህ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ስለሆነም ሦስት ሆነን ለመጎብኘት ከተቀጣጠርነው ውስጥ እኔ ሰኔ አንድ ቀን 3፡30 ላይ ቀድሜ ተገኝቻለሁ፡፡ በቅድሚያም ያቀናሁት ወደ ቀድሞ የአሜሪካ የሠላም ጓዷ ወደ ዲሻንታል የመማሪያ ማዕከል ወይም ቢሮ ነው፡፡ ስልጠና ይሰጥበት፣ ተማሪዎች ያነቡበትና ይማሩበት የነበረ ቆንጆ ክፍል ነበር፡፡ እሷ በፊት ቅርጻቅርጽ፣ በልዩ ልዩ የእንግሊዝኛ መጻሕፍት፣ በስልጠና ፖስተሮች ታስውበው ነበር፡፡ ለተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ወይም ሲፒዲ ስልጠና እገዛ ስትሰጥና እንግሊዝኛ ስታሰለጥን ጥቁር አሜሪካዊቷን ወጣት በጎፈቃደኛ አግዣታለሁ - በትርጉምና በመሳሰለው የሙያ ስራ፡፡ አሁን ክፍሉ ዝግ ነው፡፡ በመስኮት ለማየት ሞከርኩ፡፡ በዚያም ቅጽበት ያየሁት ቆሻሻ የተዘጋ ክፍልን እንጂ ያንን ያማረና ግቡ ግቡ ብሎ የሚጋብዘውን የዲሻንታልን ቢሮ አልነበረም፡፡ አሁን ያረጁ ኮምፒውተሮች፣ ካርቶኖች፣ ወረቀቶች፣ ጠርሙሶች ወዘተ በየቦታው እንደ እብድ ቤት ተበታትነው አቆሽሸውታል፡፡ ቆሻሻ፣ የተዘበራረቀ ዕቃ የተቀመጠበት መጋዘን፣ ተስፋ አስቆራጭ ትዕይንት ቀልቤን ገፈፈው፡፡

ከዚህ በኋላ የመምህራን ማዕከል ወደነበረው ስፍራ ስሄድ ሁለት መምህራን ኮምፒውተር ሲነካኩ ደረስኩ፡፡ ወንዶች ናቸው፡፡ ሁለት ሴቶች መምህራን ደግሞ ጥግ ይዘው ለዕለቱ ክፍል ይዘገጃጃሉ፤ ወረቀትም ያርማሉ፡፡ ተዋውቄ የመጣሁበትን ጉዳይ ነገርኳቸው፡፡ መምህራኑ አዳዲስ መሆናቸውን ነገሩኝ፡፡ ርዕሰመምህሩና ምክትሉም ስብሰባ ሄደዋል ተባልኩ፡፡ ሁለት ዕጩ መምህራን ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ መጥተው በቢሮው ውስጥ ከመምህራኑ አጠገብ ተቀምጠው የደወሉን መደወል ይጠባበቃሉ፡፡

አንድ ስለ ትምህርት ጉዳይ ለማውራት ቅርብ የሆነ መምህር አገኘሁ፡፡ በቅርቡ የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ችግር ለመፍታት የሚጠቅም ያለውን ዕቅድ አውጥቶ ማዘጋጀቱን ገልጾ ያንንም ዕቅድ አሳየኝ፡፡ ተማሪዎች ያለባቸውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችግር የተመለከተ ነው፡፡ ያንን ዕቅድ በትምህርት ቤቱ በኩል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማስላክና እገዛ ለማግኘት ከቀናነት ማነስ አለመቻሉን ነገረኝ፡፡  ከእርሱ ጋር ስናወጋ ሌሎች መመህራን ከክፍል ወጥተው እየመጡና በፊትም የማውቃቸው እየተጨመሩ ሲሄዱ ሰላምታ ለመለዋወጥና አንዳንድ ትዝታ ለማውጋት ቻልኩ፡፡ መምህሩ ‹‹ዋናው ችግር ተለባስሶና ተሸፋፍኖ የመሄድ ችግር አለ›› በማለት ከላይ እስከታች ያሉ ችግሮች ለመማር ማስተማሩ ስራ እንቅፋት መሆናቸውን ገለጸልኝ፡፡ በቅርቡ በደብረሲና ትምህርት ቤት ሃምሳኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ አከባበር ወቅት ያገኘኋቸው መምህር እንዳሉኝ ‹‹ትምህርት ቤት ርዕሰመምህሩን ይመስላል፡፡››

ያናገርኩት መምህር በትምህርት አስተዳደር ረገድ ያለ ችግር የፈጠረውን ፈተና ለመገንዘብ ችሏል፡፡ ‹‹ወላጅ ለመጥራት ደብዳቤ ጻፉልኝ ስል አድበሰበሱ›› አለኝ፡፡ ‹‹አመራሩ ወላጅን ማግኘት አይፈልግም፡፡›› የኮምፒውተርን ጉዳይ አንስቶ ሲነግረኝ ሲጠቀሙበት ያየሁትን ኮምቲውተር በስንት ግፊት ከመጋዘን አስወጥቶ እንደሚጠቀም አነሳልኝ፡፡ በዚያም ምክንያት ሌሎቹም መምህራን ለመጠቀም ችለዋል፡፡ በአገሪቱ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶየኮምፒተር ትምህርት ለመስጠት መታቀዱን ገልፆ ከተማው ላይ ሳይቀር መብራትና መሰረተልማት በሌለበት ገጠር እንዴት ሊሆን ይችላል ሲል ይሞግታል፡፡ ‹‹ፈተና በሰሌዳ ጽፈን ነው፡፡ ኮፒ ራሱ እዚህ ጽፈህ ነው ሌላ ቦታ ፕሪንት የምታደርገው፡፡ ያላቸውን የጥቅም ትስስር አታውቅም፡፡ መግዛት አቅቷቸው አይደለም፡፡ የግል ትምህርት ቤት ላይ ያለው እዚህ የለም፡፡ የመንግስት ተቋም ከግል ለምን ያንሳል?›› ይላል በቁጭት፡፡ መምህሩ እሮሮውን ማንም ሊሰማው የማይችልና ቢሰማውም ‹‹እስኪ እስኪሰለቸው ይጩህ›› የሚባል ትጉህ ዜጋ ነው፡፡ ትውልድ የሚለውን ቃል በየንግግሩ መሃል ይጠቀማል፡፡

ቤተመጻሕፍቱን አስመልክቶ ሲገልጽ የሌለ መጽሐፍ የለም ይላል፡፡ የሚጠቀም ሰው አለመኖሩ ግን ያናድደዋል - መምህራን ጭምር፡፡ ‹‹የዱሮ የኢትዮጵያ ካርታ ያለበት መጽሐፍ ለመወገድ ተዘጋጅቶ አገኘሁት፡፡ የቤተመጻሕፍት ሰራተኛው ያንን ካርታና መጽሐፉ የያዛቸውን ቁምነገሮች ሳሳየው አላነበበውም ነበር፡፡ እንዴት ሽፋኑ ስለተገነጠለ ብቻ ይወገዳል! በርካታና ልዩ ልዩ መጻሕፍት ናቸው እኮ›› ብሎኛል በንዴት፡፡ የንባብ ፍቅር ያለው ሰው ለቤተመጻሕፍቱ ቢመደብለት ጥሩ መሆኑን ገልጾልኛል፡፡ ኢንተርኔት ኮኔክሽን የለም፤ ኮምፒውተር ላቡ በተሟላ ሁኔታ አገልግሎት አይሰጥም፤ ላይብረሪው ከግርማ ሞገስ በላይ ጥቅም አልሰጠም የምሬት ቃላት ጎርፍ!

‹‹እዚህ ሰዓት ጠብቆ የሚጠፋ መምህር የራሱን ልጅ በግል ትምህርት ቤት ያስተምራል፡፡ ምናለ የራሳቸውንም ልጆች እዚህ አስመዝግበው በጥራት ቢያስተምሩ!›› አለኝ፡፡ ‹‹መምህሩ ጠቃሚ ስልጠና አበል ከሌለ አይሰለጥንም፡፡ መምህር ግን የዕውቀት አባት ነው፡፡ መምህሩ ገብቶ መውጣቱን ነው የሚያየው፡፡ ዩኒቨርሲቲ በየትምህርቱ ያለውን የማስተማር ስራ ቢከታተልልን ጥሩ ነው፡፡ ትምህርት እየተሰጠ ነው ለማለት እቸገራለሁ፡፡ ትውልድ መግደል ነው፡፡›› ችግሩ በዚህ ትምህርት ቤት ብቻ ሳይገደብ በገጠር ትምህርት ቤት በሳምንት ሁለት ቀንም አያስተምሩም ብሎኛል፡፡ ገጠር ላይ ከሚማሩበት የማይማሩበት ቀን ይበልጣል ብሎ ያምናል፡፡ እንደእርሱ ከወረዳ ከተማ በራቁ ቁጥር ቁጥጥሩ ስለሚላላ ነው፡፡

ዘበኛውም ጨዋታችንን ተቀላቅለው ‹‹ይህ ትልቅ ተቋም ስብሰባ የለ፣ ቤተሰብ አይጠራ፣ ልጆቹ ጠባይ የላቸው፣ ደሞዝ አይጨመር›› ሲሉ አማረዋል፡፡ የትምህርት ቤት ጥበቃ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአካባቢው ማህበረሰብ ይሸፈን ስሚባል ህብረተሰቡ ደምወዝ እንደሚከፍል ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡

‹‹ተማሪው ፍላጎቱ ደካማ ሆነ፡፡ የአማርኛና እንግሊዝኛ የፊደል ገበታ 7 ክፍል በየክፍሉ ለጥፌያለሁ፡፡ የማስተምረው ከዚህ ነው የሚወጣው እላቸዋለሁ፡፡ አያነቡም፤ የተወሰነ ተማሪ ነው የሚሰራው፡፡ ቤተሰብ አምጡ ስል አያመጡም፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ በድህነት ነው የሚኖረው፡፡ ልጆቹ ምግብ ሳይበሉ ሊመጡ ይችላሉ፡፡ 22 ተማሪ ውጪ በሚኖሩ በጎፈቃደኞች ድጋፍ የትምህርት ቤት ምገባ ይደረግለታል፡፡ ቤተሰቦቻችሁ የት ይሰራሉ ስላቸው ዳሸን፣ ሐበሻ፣ ዩኒቨርሲቲ፣ ጽዳት፣ እንጀራ ጋገራ፣ ይላሉ፡፡ ለምን ጎበዝ አትሆኑም ታዲያ የነሱ ልጆች ከሆናችሁ ስል የሚያለቅሱም አሉ፡፡››

በትምህርት ቤቱ ያገኘሁት ሌላ መምህር ስለአመጣጤ ስነግረው በፊት አጣዬ ሲያስተምር ክፍል ገብታ እንግሊዝኛ የምታስተምር አሜሪካዊት እንደነበረች አወጋልኝ፡፡ ስለሷም ልዩ ልዩ የሚያስታውሰው ነገር አለው፡፡ ብቻዋን ገጠር ሄዳ ዋሻ ውስጥ ገብታ ገበሬዎች ይዘዋት እንደመጡና በጥርጣሬ እንደሚያያት ነገረኝ፡፡ አንዷ ደግሞ ውሻዋን ትታ መሄድ ከብዷት እንደነበርና ሃዘን እንደተሰማት አወጋልኝ፡፡ ‹‹እርጉሞች ናቸው›› የሚል ንግግርም ጨመረ፡፡ ከተጠቃሚ አገር ዜጎች በኩል በባህል ብረዛና በፖለቲካ ጥርጣሬ አሜሪካውያኑ በሚሰሩት ስራ ሁሉ ጣልቃ እንደሚገባባቸው ከበፊቱም ያስተዋልኩት ስለሆነ አልደነቀኝም፡፡ ‹‹በየዋህነት ለማገዝ አዝነው ነወይ የመጡት?›› ይላል መምህሩ፡፡ ጥሩ ነገሮች የጀመራቸው ሃላፊ ወይም ሰው ሲሄድ ይቆማሉ በሚለው ላይ ግን አሜሪካውያኑ ሲሄዱ የጀመሩት ስራ አለመቀጠሉን አስመልቶ አንዳንድ ምልከታን አውስቶልኛል፡፡ ተስማምተንማል፡፡ የዘላቂነት ችግር አለ፡፡ አሜሪካውያኑ የኛን ስራ ለዘላለም ሊሰሩልን አልመጡም - መንገድ ሊያሳዩን እንጂ!

በትምህርት ቤቱ እንደዱሮው ሁሉ ውኃና የረባ መጻዳጃ  የለም፡፡ ፈረንሳዮች በተለይም የእህት ከተማችን የብሉምኒል ከተማ ሰዎች ያሰሩት ሁለት ብሎክ ደረጃውን የጠበቀ መጸዳጃ አሁንም ጥቅም ሳይሰጥ አስር ዓመት አልፎታል፡፡ አጠቃላይ የዘመናዊ መጸዳጃው ስራ ባዮጋዝም ስለነበረውና የሱ ማሰሪያ ገንዘብ ስለተበላ ፕሮጀክቱ መቆሙንና ተማሪውና መምህሩ ደረጃዋን ባልጠበቀች አነስተኛ መጸዳጃ እየተሰቃየ አንደሚገኝ ታዝቤያለሁ፡፡

ከቆይታ በኋላ ዲሻንታልን የምታውቅ ተማሪ አገኘሁ፡፡ ተማሪዋ የ11ኛ ክፍል ተማሪና ስለትምህርት ቤቱ ታሪክ አሳይመንት ለመስራት የመጣች ነች፡፡ የዲሻንታልን ስራዎች አስታወሰች፡፡ ከአንዳንድ መምህራን ‹‹እሷ ምን ያልሰራችው አለ!›› የሚል በድፍን የመግለጥ ዘዴ የተሻለ ማብራሪያ ሰጥታኛለች፡፡ በፊት ዲሻንታል ላሰልጥን ስትል የሚመጣው መምህር በጣት የሚቆጠር መሆኑን ታዝቤ ነበር፡፡ መምህራኑ ምንም ባያስታውሱም አይገርመኝም፡፡

የእንግሊዝኛ መምህሯ ቀለም መጥተው ተዋውቃኝ ከሒሳብ መምህሩ ሙሉጌታ  ጋር ተነጋግረው በስድስተኛና ሰባተኛ ክፍል ባሉ ስድስት ክፍሎች ያሉ በእንግሊዝኛ ዝቅተኛ ውጤት ያላቸውን አምስት አምስት ተማሪዎች መረጡልኝ፡፡ ዓላማዬ በፊት ዲሻንታል እንደሰራችው አንድ ፕሮጀክት ዓይነት መስራት ነው፡፡ እነዚህን ተማሪዎች በእንግሊዝኛ ጎበዝ ማድረግ፡፡ ወደ ትምህርት ቤቱ ከሄድኩበት ሰኔ 1 ቀን 2014 ጀምሮ እስከዛሬ ሰኔ 12 2014 ድረስ ለአምስት ክፍለጊዜያት በግል ቤተመጻሕፍቴ በራስ አበበ አረጋይ ተማሪዎቹ እየመጡ እንግሊዝኛ በተለይ አጠናኑ ላይ በማተኮር አስተምሬያለሁ፡፡ ማስተማር ብቻም ሳይሆን የመሐልሜዳው በጎፈቃደኛ ማይክ ‹ማይክ ፊድ› በሚል ያካሂደው የነበረውን የምገባ አሰራር ከዲሸንታል የማስተማር ሞዴል ጋር በማቀናጀት እያስተማርኩና እየመገብኩ ነው፡፡ ስመግብም በራሴ ወጪ ነው፡፡ ለወደፊቱም የምሰራው የአማራ የሠላም ጓድ ስራ እርዳታ ሳይቀበል በአካበባቢያችን ባለው ሀብት በመጠቀም የበጎፈቃድ ስራን እንዲሰራ እፈልጋለሁ፡፡ ገና በጥናትና ዕቅድ ላይ ያለ ቢሆንም፡፡

በዕለቱ ሁለቱ ጓደኞቼ መጥተው ትምህርት ቤቱን ጎበኘን፡፡ ቤተመጻሕፍቱ እጅግ ያመማረና ግዙፍ መሆኑን አየን፡፡ አስነባቢውን አቶ ዓለማየሁን ከአሁን በፊት በቤተመጻሕፍታችን ከሪጊስ ዩኒቨርሲቲ ላይብረሪ ዲን ከጃኔት ሊ ጋር በሰጠነው ስልጠናም ስለማስታውሳቸው ለመግባባትና ስለ ስራ ሁኔታ ለመጠየቅ ጊዜ አልወሰደብኝም፡፡ የበፊቶቹ የዲሻንታልን ስራዎችም አየን፡፡ ለማርች 8 የሴቶች ቀን ጄፍ ከተባለው በጎፈቃደኛና ከተማሪዎች ጋር የሰሩት ስዕልና የአንዳንድ ሰዎች እየጠፋ ያለ ትዝታ ብቻ ቀርቷል፡፡ ሕግ አጥንታ በአሜሪካ አየር ኃይል በመስራት ላይ የምትገኘው ዲሻንታል መንፈሷ እንዲደሰትና ‹‹ትምህርት ቤቴን እይልኝ›› የሚለው ጥያቄዋ እንዲመለስ እሰራለሁ፡፡ በብዛት አሜሪካውያኑ ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ለጥያቄዎቻችን መልስ ስለማይሰጡን የሰራሁትን ለመንገር እቸገር ይሆናል፡፡

በትምህርት ቤቱ ያገኘኋቸውና ተማሪዎችን በሳምንት ሦስት ቀን ራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት እየያዙ የሚመጡት ትጉህ መምህር በደብረ ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የኮምፒውተር ስልጠና ዕድል ተሰጥቶ ብዙ መምህራን አንፈልግም ብለው እርሳቸው እየሰለጠኑ መሆኑን ነገሩኝ፡፡ እኔም ከእርሳቸው ጋር ኮሌጅ ሄጄ የስልጠናውን አሰጣጥ አየሁ፡፡ ከየትምህርት ቤቱ የተሰባሰቡ 16 መምህራን እየሰለጠኑ ነው፡፡ የኮምውተሩ ስልጠና ስላለቀ ከሰልጣኞቹ ጋር በመነጋገርም የስድስት ቀናት የእንግሊዝኛ አጠናን ስልጠና መስጠት ጀምሬያለሁ፡፡ ነገ ሰኞም ሁለተኛውን ክፍለጊዜ ይቀጥላሉ፡፡ አንዱ በር ሌላውን ይከፍታል፡፡

ከጠባሴ መድኃኔዓም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቆይታዬ ብዙ ተምሬያለሁ፡፡ ይህን ሁሉ ችግር የምፈታው ግን የትኛውን ቦታ ብይዝ እንደሆነ አልገባኝም! ከወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት እስከ ከንቲባ፣ ከዞን አስተዳዳሪ እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይህን ሁሉ ችግር እያዩ ዝም ብለዋል፡፡ መምህሩ በደንብ እንዲያስተምር፣ ርዕሰመምህሩ በደንብ እንዲመራ፣ ተማሪው እንዲተጋ፣ ወላጅ ምግብ እንዲያቀርብ፣ ለወላጅ የስራ ዕድልና የገቢ ምንጭ እንዲመጣ!

 


ሰኞ 6 ጁን 2022

በትምህርት ጉዳይ - ተማሪ ለምን ‹ሰነፍ› ይሆናል?

 

በመዘምር ግርማ

 


ሰነፍ ተማሪ ማነው ብለን ብንጠይቅ የተለያዩ መልሶችን ልናገኝ እንችላለን፡፡ ብዙ ሰው ሰነፍ የመባል ዕድል ገጥሞት ያውቃል ለማለት እደፍራለሁ፡፡ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ ትምህርት ሰነፍ ትባላላችሁ፡፡ ለዚህ ማስረጃም ከመቶው ያላችሁ ነጥብ ዝቅተኛ መሆኑ ይሆናል፡፡ በፈተና መውደቃችሁ ለስንፍናችሁ ማስረጃ ይሆናል፡፡ የቤት ስራና የክፍል ስራ አለመስራታችሁም እንዲሁ፡፡ ሌላው ሰነፍ ትምህርቱ እየገባው ለመስራት የማይሻና ጊዜውን በሌላ አልባሌ ነገር ላይ የሚያሳልፍ ሊሆን ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ዓይነት ሰነፍ ላይ ያተኮረ ሃሳብ ለማጋራት ይህን ጽሑፍ ጫር ጫር (ወይም በኪቦርድ ስለሆነ ጠቅ ጠቅ) አድርጌያለሁ፡፡

ተማሪዎች አንድን ትምህርት ለመቀበል ያላቸው ሁኔታ የተለያየ ይሆናል፡፡ ፈጣን፣ መካከለኛና ዝቅተኛም ይሆናል፡፡ ለዚህም ልዩ ልዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የልጆቹ የትምህርት አቀባበል፣ የመማሪያ ስልታቸውና መምህሩ የሚያስተምሩበር መንገድ አለመጣጣም፣ ከቀደሙ ክፍሎች ለዚያ ትምህርት አስፈላጊውን የቀደመ ዕውቀትና ክህሎት አለማግኘት ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሰነፍ የተባለው ተማሪ የሚገጥመውንና በአንድ የክፍል ደረጃ ለሚሰጥ ትምህርት የቀደመ አስፈላጊ ዕውቀት ይዞ አለመገኘቱ የሚያስከትለውን ችግር በተለይ ቀጥሎ እንመልከት፡፡

በተለያዩ ትምህርት ዓይነቶች መሰረታዊ የሚባለውን ዕውቀትና ክህሎት መጨበጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝኛ ትምህርት ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ፣ መቁጠር አስፈላጊ ነው፡፡ ከኤ አስከ ዜድ ቆጥሮ መጨረስ መሰረታዊ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ቆጥሮ መጨረስ ስንል ድምጻቸውን ማወቅ፣ ድምጻቸውንና ቅርጻቸውን ማዛመድ መቻል እንዲሁም ካፒታልና ስሞል የተባሉትን መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚያም በተለያዩ ቃላት ውስጥ ገብተው ሲነበቡ የሚኖራቸውን ድምጽና አንዳንዴም የሚያመጡትን ልዩነት መማር ያስፈልጋል፡፡ ይህንና ተያያዥ የእንግሊዝኛ ፊደላትን መሰረታዊ ሁኔታ አለማወቅ በቀጣይ ክፍሎችም ሆነ የትምህርት ሂደት የሚያመጣውን ችግር አስቡት፡፡ በላይ ክፍሎች እንግሊዝኛ የማስተማሪያ ቋንቋ ሲሆን የሚኖረውን ድርብርብ ጣጣም ልብ በሉ፡፡ በአንዱ ቀን ትምህርት ላይ የሌላው እየተደራረበ ሲሄድ ብዙ ነገር ይበላሻል፡፡ ያ ሁሉ ችግር የሚቃናበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ያንን የሚያቃናው የተማሪው በዕድሜ ሂደት መብሰል ነው? ወይንስ የጥሩ መምህር መገኘት? የወላጅ ክትትል? የሚቃናበት መንገድ ካልተገኘስ? ልጁ ከልጅነት እስከ ዕውቀት በእንግሊዝኛ እንደተቸገረና ትምህርቱን እንደጠላው ሊዘልቅ ይችላል፡፡ ይህን የእንግሊዝኛን ሁኔታ አነሳሁ እንጂ ነገሩ በሌላም ትምህርት ማጋጠሙ አይቀርም፡፡ በሂሳብም መሰረታዊ የሂሳብ ምልክቶችንና ቁጥሮችን ያላወቀ ተማሪ ለተደራራቢ ችግር መጋለጡ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ያለፈው ቀን ትምህርት የዛሬን የቤት ስራ ወይም የክፍል ስራ ለመስራት አስፈላጊነቱ አሌ አይባልም፡፡ በአማርኛስ ቢሆን! ተመሳሳይ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ እንደተገለጸው ያለ ችግር ይገጥማል፡፡ ይህ ሁኔታ ለሁሉም ትምህርት ይሰራል፡፡ ተማሪዎች በዚያ ችግር ውስጥ ሳሉ የሚከታተላቸው ወይም የስንፍናቸውን ምክንያት የሚረዳላቸው ይኖር ይሆን? ወይንስ እኔ ሰነፍ ነኝ ብለው ችግራቸውን ተቀብለው እንዲኖሩ ይገደዳሉ? በቀጣዩ አንቀጽ እንየው፡፡

ይህን ጽሑፍ ልጻፍ ወይንስ ምን ላድርግ የሚለውን ሳልወስን በማስታወሻ ደብተሬ ይዤ የቆየሁት ጉዳይ ‹‹ A plight of plights is studying a lesson or learning something that you really do not understand because you don’t have the necessary background. Worrying Unnecessarily!›› ማለትም ‹‹የስቃዮች ሁሉ ስቃይ የቀደመ ዕውቀቱ የሌላችሁን አንድን በእውነት የማትረዱትን ትምህርት ወይም ነገር መማር ነው፡፡ መጨነቅ ሳያስፈልግ መጨነቅ!›› የሚል ነበር፡፡  አዎን፣ መሰረታዊ ዕውቀቱና ክህሎቱ የሌለንን ትምህርት እንጠላ ይሆናል፡፡ በምንጠላበት ሁኔታ ድጋፍና እንድንወደው የሚያደርግ ነገር ካላገኘን ከዚያ ትምህርት ጋር እየተቆራረጥን መሄዳችን አይቀሬ ነው፡፡  ይህም ትምህርቱን የመጥላት ሁኔታ በተማሪው ላይ አላስፈላጊ ጫና ይፈጥራል፡፡ በትምህርት ወቅት አለመከታተል፣ በመምህራን እንደ ልግመኛ መወሰድ፣ በፈተና ወቅት በግምት መሙላት፣ አሳይመንት በሰው ማሰራት፣ መኮረጅ፣ በዚያ ትምህርት ከሚገኙት ክህሎትና ዕውቀት ምክንያት ተዛማጅ ትምህርቶች ላይም የውጤትና ፍላጎት መጥፋት፣ ከክፍል መውደቅ ወዘተ ሊከተሉ ይችላል፡፡ የቀደመ ዕውቀቱ የሌለንን ትምህርት መማር እንዴት ተደራራቢ ችግርችን እንደሚያስከትል ካየን ዘንዳ ምን ዓይነት መፍትሔ ሊኖር ይችላል የሚለውን እንመልከት፡፡ መፍትሔው ከትምህርት ተቆጣጣሪ አካላት፣ ከመምህራን፣ ከወላጆች፣ ከተማሪዎች፣ ከተመራማሪዎች ወዘተ ሊመጣ ይችላል፡፡ አንድን ትምህርት ለማስቻል ከመዋዕለሕጻናት ጀምሮ አንድ ልጅ ላይ የሚፈሰው ሀብት ከፍተኛ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሀብት በትክክለኛው መንገድ እየፈሰሰና ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን ማረጋገጥ ያሻል፡፡ በትንሽ እገዛ ሊስተካከል የሚችልን ችግር ችላ ማለት ለዘላቂ ችግርና ድርብርብ ጫናዎች ይዳርጋል፡፡ ልጆችም በትምህርት ጎልብተው ሊደርሱ የሚገባቸው ደረጃ ላይ ይደርሱ ዘንድ ይህን ችግር መፍታት ያሻል፡፡ ለመማር ዝግጁ የሆነ አእምሮ ይዞ የተወለደን ልጅ ባልተገባ ሁኔታ ሰነፍ እያሉ ስም ከማውጣት የስንፍናውን መንስኤ አጥንቶ ማገዝ ከምስቅልቅል የትምህርት ህይወት ያድናል፡፡ ስንፍናው ከትምህርት አሰጣጡ ሊሆን ይችላል፡፡ አለያም ለተማሪው የተጋነነ ውጤት በመስጠት በዚያ ትምህርት ጥሩ እንደሆነ በማሳየት ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተማሪውም፣ መምህሩም ሆነ ወላጅ ችግሩን ልብ ሳይሉት ቆይተው ተደብቆ ቆይቶ ሊወጣ ይችላል፡፡ አንዳንድ አስደናቂ ነገሮችም ይኖራሉ፡፡ ለምሳሌ አንደኛው በግል ትምህርት ቤቶች የሒሳብ ትምህርት አሰጣጥን ብናይ ለአንድ ተማሪ ሒሳብን በአማርኛም በእንግሊዝኛም የሚሰጡ አሉ፡፡ በሁለቱም ተምሮ ሒሳብ የማይችለው የግል ትምህርት ቤት ተማሪ ብዙ ነው፡፡ ወላጅን ለማማለል የሚደረገው በሁለቱም ቋንቋዎች ሒሳብንም ሆነ ሌሎቹን የማስተማር ዘዴ የሽወዳ ስራ መሆኑን ያሳብቃል፡፡ የመንግስት ተቆጣጣሪ ሲመጣ በአማርኛ እንደሚማር ይናገራሉ፡፡ የተማሪውን ትኩረት በበርካታ ትምህርቶች ከመበተን ሥርዓተ-ትምህርቱ እንደሚያዘው በአማርኛ አስተምረው ትክክለኛውን ክህሎት ቢስጨብጡት የተሻለ ይመስላል፡፡ የሒሳብ ነገር ከተነሳ አይቀር ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ያነበብኩት በትምህርት ሚኒስቴር የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው በመንግስት ትምህርት ቤቶች ያለው የተማሪ ቁጥር መብዛት፣ ክትትል ያለመኖር፣ የመጻሕፍት እጥረት ወዘተ በሒሳብ ትምህርት አገሪቱ ብዙ እንድትቸገር እንዳደረጋት ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ መሻሻል ያለበት ነገር አለ፡፡ ይህም ለሌሎችም ትምህርቶች ይሰራል፡፡ በተቻለ አቅም ጥረትና ትብብር ማድረግ ያሻል፡፡   

አንድ ተማሪ ከአንድ የክፍል ደረጃ ወደ ሌላኛው ሲሸጋገር አስፈላጊውን የትምህርት ይዘት ማወቁን ማረጋገጫ ሁነኛ መንገዶችን መቀየስ አስፈላጊ ነው፡፡ ይዞ ላልተገኘውም በሰዓቱ እገዛ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እገዛውንም በቤተሰብ፣ በመምህር፣ በአስጠኚ እንዲሁም የኦንላይን የትምህርት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማድረግ ይቻላል፡፡ ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ ሆኖለት በትምህርት ጫፍ የሚደርሰውን ጎበዝ ተማሪ እንደምናደንቀውና እንደምናበረታታው ሁሉ ከታች ያለውንና በብዙ ችግሮች የተተበተበውን ተማሪ ማየት ያሻናል፡፡ ‹‹ስራ ስራ ስራ›› ብለን ብንመክረው ለውጥ ላይመጣ ይችላል፡፡ እንዴት እንደሚሰራ ላያውቅ ስለሚችለማሳየት አለብን፡፡ ለማጠቃለል ያህል ሰፊ ጥናት የሚፈልገውንና ከትምህርት ስርዓታችን ችግሮች አንዱ የሆነውን ይህን ችግር መምህራንና ተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎች፣ ወላጆችም ሆኑ ተማሪዎች ልብ እንዲሉት አሳስባለሁ፡፡

ሐሙስ 2 ጁን 2022

Project X

 

By Mezemir Girma

 



 

“Once in power, the Nazis implemented racial laws and policies that deprived Jews, Black people, and Roma (Gypsies) of their rights,” reads part of an article from the United States Holocaust Memorial Museum. The same model seems to have been copied and implemented on the members of various victim ethnicities in Ethiopia over the last three decades. A phone call or a request to visit their bosses’ offices that is reaching individual government employees these days must be part of a bigger covert program which is cascading from the constitution. People who are increasingly caught by other complicated life and national issues these days almost forgot it as something which is part of their everyday lives. This activity which we are dealing with is the implementation stage of the sinister ethnic-centered policy. How could one ingest this act which is more of like adding gas to burning fire at this time of juncture Ethiopia is in? Such seemingly trivial issues like ethnic profiling of government employees should awaken Ethiopians or humanity at large. 

Citizens of this country suffered immensely for three decades and their plight doesn’t seem to abate to date. Since the obsession with divide and rule is in the mindset of the politicians who were brought up by the TPLF is it could take us a long way to come out of it. Depriving communities of their rights, silently working on minimizing their population, economic deprivation, all type of influence have been experimented in this country. Human rights violations range from individual ones to big scale. Vanity from the world over has been copied and inflicted upon the people.  

“Hello Mr X. A new form that every employee should fill in has come. Please tell us a few pieces of information and let us fill it on your behalf. First, could you tell us your ethnicity?” This is a call that employees of Federal institutions have been receiving these days. None seems to care, they simply comply. That is at least what I noticed. Only a few raise the issue among friends’ circles.  The registration process has not been questioned by serious personalities, journalists or people concerned. No one seems to deter it. So far, they call and ask those who they think don’t resist the scheme. A social media post from Hawassa disclosed that the registration was underway there and a considerable number of university staff responded as Ethiopians. A few other teachers and staff said that they were asked for place of birth. Just like those Kebele officials in Addis Ababa who went to each household and found out the ethnicities of the residents a few years ago, this one is going smoothly. I just treated the issue here only because they are doing it without a little shame. Who knows about other secret works they are doing?

A few months ago, there was a wind of it. Certain people whom I don’t exactly remember for the time being posted on their social media platforms about the issue. Some of them wrote a few lines opposing the scheme, but the rest just posted photos of notices from the noticeboards of their work places. Those notices required employees of agencies in Addis Ababa and Federal institutions to report to the human resource departments and inform the ethnic groups they belong. Now, the silent work has come to every town in the regions. This may not sound like a surprise. Yes, the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia is centered on ethnicities than citizens – “We the Nations, Nationalities and People of Ethiopia … our common destiny can best be served by rectifying historically unjust relationships … Every Nation, Nationality and People in Ethiopia has an unconditional right to self-determination, including the right to secession.” – a time bomb!  The question in my mind is who is the mastermind of the ethnic-profiling underway at this time and for what purpose?

Politicians who ruled the country for 27 years with an iron-grip used ethnic difference as a means of divide and rule. At that time it was common to hear them speak the issue in public. I remember one mentioning the percentage of employees in Addis Ababa and the need for balance. This answer he brought in response to the question on the unfair distribution of power and resources exposes what sort of calculations they were making. At this time that miscalculation seems to be the guiding principle too. That time could be one in which the politicians and local cadres were almost free and calm to table such issues. They were just issues and the actions they made were more of done backstage than now. At this time of war, increasing cost of living, unrest and almost all type of problem in the country, what use could be ethnic profiling of employees? Won’t it be better to seek a means to rally the population to support in the rebuilding of the nation! It is clearly dousing the dying nation with gas. An escalation of the problems we have could be from those who want the nation crumble than a responsible administration that is ruling a country.

Ethnic profiling and any actions related to dividing the people should halt and the mother of all these vice, the constitution, should be revised accordingly. The current action seems to be in line with what the TPLF led system did when they came to power by the name of putting the ethnic group of people on Kebele identification cards which they used to discriminate against those who they labeled unfriendly. For the current system which promised such fancy ideas as it will give a national identification card and focus on nationality than ethnicity, this seems to be a paradox and puts their undelivered promise in question. The racial laws and policies could be meant to deprive employees of their rights and ethnic groups’ representation at government agencies if not introducing a pre-1994 Rwanda like ethnic quota. If an employee reshuffle or any sort of decision follows this, it will result in a mess. That is in the minds of employees since at this time the administrations terminated employment. They could be planning to use ethnic background than merit. Until that nobody knows what the future holds for Ethiopians.  

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...