የጉዞ፣ የንባብ፣ የቤተመጻሕፍት ፣ የሕትመትና ስርጭት ወዘተ ጽሑፎችን ያገኙበታል። I share my views and reports of my activities in this blog.
ሰኞ 20 ኤፕሪል 2015
For the Ethiopian Christians Murdered in Libya
I have really been saddened to hear what happened to our fellow country men. We have not yet recovered from the pains the South African murderers inflicted upon us; nonetheless, this inhumane deed of the ISIS terrorists has left a big wound in the hearts of many of us. Sooner or later, death comes to everyone of us including these brutal murderers. When death takes your life with a an unbearable pain as to be burnt alive or slaughtered, your death is indescribable! In a situation where you are not attended to by your loved ones, given water to quench your thirst or bread to satisfy your hunger, and even more than that where you are attacked like a wild animal and when no one is able to avenge your death, there crawls sorrow in the correct sense of the word towards your loved ones! May we never hear such sad stories again! Please stop posting the ISIS photos and videos and show your sympathy to the dead and their family!
ሐሙስ 16 ኤፕሪል 2015
በዓል ባይኖር ኖሮ
የበዓል ሰሞን የሚገርም ግርግር ትታዘባለችሁ፡፡ በብዛት ሰዎች የመጎብኘት ልማድ ባይኖራቸውም በዚህ ወቅት ግን ተጓዡ ይበዛል፡፡ በሚገርም ሁኔታ የምግብ ዝግጅት፣ ሽያጭና ፍጆታ ደግሞ ይጧጧፋል፡፡ ራድዮ ጣቢያዎች የማስታወቂያ ውርጅብኝ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ የሙዚቃ ግብዣ ብሎም የበዓል ዝግጅቶች ያበዛሉ፡፡ ቴሌቪዥን ጣቢዎችም ልክ ሰሞኑን ኢቢኤስ ከቴዲ አፍሮ ቤት የበዓል ዝግጅት እንደጋበዘን ሁሉ ቀደም ብለው የተቀረጹ ዝግጅቶችን እንካችሁ ተቃመሱ ይሏችኋል፡፡ የበዓል ሰሞን መቼም በአቅም ማነስ፣ ከቤተሰብ በመራቅ፣ በህመም፣ በምግብ አለመመቸትና ሌሎችም ምክንያቶች የሚከፋውም አይጠፋም፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑ ደግሞ እነ እከሌ ቤት ይሄ ተበላ ይሄ ተጠጣ የሚለው ማሳበቅ ይረብሽም ይሆናል በተለይ እንዲህ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ በተለያየበት ወቅት፡፡ ምንም ቢሆን ግን ስንትና ስንት በዓል ሲያሳልፉ የታዘቡት ብዙ ለውጥና ሁኔታ ይኖራል፡፡ ምንም እንኳን ማስታወሻ የመያዝ ልማዳችን ደከም ቢልም የማይረሱ ገጠመኞችና ትዝብቶች ስለሚኖሩ አንዳንዶቹን እያነሳን ብናወጋ ለሁላችንም ያስተምርና ያዝናና ይሆናል፡፡ ታዲያ ወረድ ብሎ ባለው የአስተያየት መስጫ ላይ እንድተጽፈልኝ ነው ይህን ማለቴ፡፡ በመጨረሻም የሚከተሉትን የውይይት ሃሳቦች እነሆ ልበላችሁ!
1. በጃንሆይ ጊዜ ትምህርት 15 ቀን ለፋሲካ ይዘጋ ነበር ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ከሞላ ጎደል አሁንም እየተዘጋ ስለሆነ ለምን መንግስት እውቅና አይሰጠውም የሚል ሃሳቤን በትህትና አቀርባለሁ፡፡
2. የህዝቡ ኑሮ ይሻሻል ዘንድ የሚታትሩ ሰዎች ዓላማቸው ይሳከላቸው ስትሉ ጸልዩ፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለበዓል በግ ቢያርድ ደስ ይላል!
3. የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው እንኳን አደረሳችሁ ሲላችሁ ምላሹ ምንድነው?
4. እርጥብ ስጋ መብላት ሳይንስና ባህል ከሚጋጩባቸው ተግባራት አንዱ ነው፤ እርስዎ ከሳይንስ ወይስ ከባህልዎ ጋር ተባበሩ?
5. ብለው አስበው ያውቃሉ?
6. የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች በዓላቸውን ሲያከብሩ እርስዎ ምን ይሰማዎታል?
7. በዓል ሲከበር በሰው አገር ሆነው ያውቃሉ?
8. በ2050 የሚከበረውን አንድ ሃይማታዊ በዓል ስታስቡት ምን ገጽታዎች የሚኖሩት ይመስላችኋል?
9. ዘፈን ለራስዎ ወይንም ለሌላ ሰው ለበዓሉ ጋብዙ ቢባሉ የማንን ዘፈን ይጋብዛሉ? ለምን?
10. መጭውን በዓል በተሻለ ሁኔታ ለማክበር ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ?
በመጨረሻም መልካም የበዓል ሳምንት እመኝልዎታለሁ!!!
እሑድ 29 ማርች 2015
ከመንዝ ጓሳ እስከ እንግድዋሻ
የጉዞ ማስታወሻ
ከመንዝ ጓሳ እስከ
እንግድዋሻ
መዘምር ግርማ እንደተረከው
መንደርደሪያ
ከአንድ
ወር በላይ ዝግጅት የተደረገበት እና ከየካቲት 27 እስከ 29፣ 2007 ዓ.ም. በመንዝ ጌራ ምድር፣ በደብረሲና እና በሞጃ እና
ወደራ ሊካሄድ የታሰበው ጉዞ በተለመደው የሰዓት መሸራረፍ ምክንያት መነሻው ከጠዋቱ 12፡00 ተብሎ የነበረው 2፡00 ላይ ይጀመራል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሽንጠ - ረጃጅም ‹‹ፈረሶች›› የአባይን ውሃ ቀምሰው ለመምጣት ወንዝ በመውረዳቸው በኪራይ ‹‹በቅሎ›› ይህን የባህል
ማዕከል ተቀጥላ ጉዞ ጸሐይ ሞቅ ስትል ‹‹በቅሎዬ ስገሪ አርጊው ነሃ ነሃ፣ ወደ ሰላድንጋይ ወደ ሞፈር ውሃ›› እያልን በተውሶ ግጥም
ጀመርንው፡፡
የጉዟችንን
መርሃ-ግብር በየመገናኛ አውታሩ፣ ፊት-ገጽን ጨምሮ፣ በትነን፣ ተጓዡን ቀስቅሰን፣ የየወረዳዎቹን አመራሮች አነጋግረን እና አስደግሰን
ስናበቃ የአባይ ጉዞ የእኛን ጉዞ ልናደርግ ባሰብንው ቀን ይደረጋል ሲባል የራስ ምታታችን ሆነ፡፡ አንድም ተጓዡ አባይን መርጦ የግቢው
ዘፈን ‹‹እንጉርጉሮ ይብቃ›› ሲሆን፣ ሁለትም ‹‹ምን መንዝ ለቅሶ ተከትለን ብንሄድስ እናየው የለም?›› የሚሉት ገሸሽ ሲሉ፣ ሶስትም
‹‹ጉዞው አርብ ስለሆነ አይፈቀድልንም የሚለው ሰራተኛ ሲበረክት››፣ አራትም የባህል ማዕከሉ ሃላፊ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የጥበብ ድግስ
ሊሳተፍ ሄዶ ያለ ሃሙስ ሳይመጣ ሲቀር እኔ ይህ ጉዞ እንዲደረግ ለማዕከሉ አባላት በስብሰባችን ያሳመንኩት፣ የየወረዳዎቹን አመራሮች
ስፍራቸውድረስ ሄጄ ያነጋገርኩት እና የክተት አዋጅ ያወጅኩት ሰውዬ ሆዬ ‹‹እሸሸግበት ጥግ አጣሁ›› ፡፡
የዕለቱ
ለት ያስረፈደን ተጓዦች በቡድን በየምንሄድበት ስፍራ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መማሪያ ክፍሎች ውስጥ ለማደር የምንተኛበትን ፍራሽ
መኪና ላይ መጫኑ ነበር፡፡ ፍራሽ ሰጭው ያርፍድ፣ ወይንስ የኛ ችግር ይሁን አልተገለጠልኝም፡፡ ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ሰላም ጓድ
በዩኒቨርሲቲያችን ከተለያዩ በሶስት ክልል ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለመጡ 64 ሴቶች ልጆች ባዘጋጀው የአንድ ሳምንት መርሃ-ግብር
ስሳተፍ አንድን ዝግጅት እንከን-አልባ ማድረግ እንዴት እንደሚቻል ካየሁበት ጋር ያሁኑን ሳነጻጽረው ምድርና ሰማይ ነው፡፡
በሰዓቱ
ራሴ ብየው የነበረው ለጥቅስ የሚበቃ ቃሌ ‹‹ሁለት ሰዓት እኮ ማራቶን የሚገባበት ሰዓት ነው›› የሚል ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ሰሜን
ሸዋ አንድ ወረዳ ላይ ሁለት ሚሊዮን ችግኞችን ሊተክል ላይ ታች ከሚለው ከአድህኖ የተቀናጀ የገጠር ልማት የመጣው አበበ ግሩም በብስጩ
ድምጽ ‹‹የቅንጅት ችግር አለ - የተባለው ሰዓትና የተነሳንበት የሁለት ሰዓት ክፍተት አለው፡፡ እኔ በሰዓቱ ነው የመጣሁት፡፡ ሌላ
ነገር ደግሞ፣ ፍራሽ ለመጫን እና ከመናኸሪያ መውጫ ለማምጣት ሲባል መኪናው በተባለው ሰዓት ዝግጁ አልነበረም›› ሲል አማሯል፡፡
በጉዞው
ዋዜማ በፊት ገጽ ያማረርኩት ምሬት አሁንም የመስሪያ ቤቴን ክቡራን ሃላፊዎች ምላሽ ይፈልጋል፡፡ ምሬቱን ቃል በቃል እርስዎም አንብበው ይፍረዱ፡፡ ‹‹በዩኒቨርሲቲያችን ወደ አባይ ግድብ ለሚሄዱ ተጓዦች ውሎ አበል ተከፍሎ ለባህል ማዕከል ተጓዦች ግን ያልተከፈለው ለምንድነው? ሁሉም ዩኒቨርሲቲው በሚሰጣቸው ምንዳ የሚተዳደሩ አይደሉምን? የዩኒቨርሲቲው አመራር አምኖባቸው የፈቀዳቸው ጉዞዎች ሆነው ሳለ ለአንዱ እንደ ልጅ ለሌላው እንደ እንጀራ ልጅ ለምን ይደረጋል? አባይ ግድብ ጋ የሚሄዱትም ጉብኝት፣
ይሄም ጉብኝት!›› የሚል ነበር፡፡
አርብ የካቲት 27፣ የምንሊክ መስኮት
‹‹የምንሊክ መስኮት በጣም ነው
የሚያስፈራው፤ በህልሜ ነው የሚመጣው፡፡ ደስታ ነው የተሰማኝ፡፡ ንጹህ አየር ነው ያገኘሁት፡፡ ›› በማለት በአጫጭር አረፍተ ነገሮች ጣርማበር አቅራቢያ ባለው ገደላማ ስፍራ ጫፍ ወጥተን
ቆላውን በአጉሊ መነጽር እያየን የተሰማትን ሁኔታ የገለጸችው እኔን አባቷን ተከትላ የሄደችው የሶስተኛ ክፍል ተማሪዋ ልጄ ሳትሆን
የስራ ባልደረባዬ ተዋበች አብዱ ነች፡፡ ውብ ሃሳብ በተቆጠቡ ቃላት!
‹‹ስለ
መስኮቱ ምንም አልነገራችሁን እኮ›› ያለው ኪሩቤል ሮሬሳ እንደመሃንዲስነቱ እቅጩን ይፈልጋል፡፡ እኛ የቋንቋ አስተማሪዎቹ አስተባባሪዎች
ግን ቋንቋ አጥሮን ይሁን ቅንጅት ይችን ጉዳይ ረስተናት ኖሯል፡፡ ስፍራው የስጋ ደዌ በሽተኞች ይጣሉበታል እንዲሁም አርበኞች ይሸሸጉበታል
መባሉን ብንነግረው ጥሩ ምስል ይኖረው ነበር ኪሩቤል፡፡
ጃንሆይ
አጼ ኃይለ ስላሤ አንድ ወቅት በጣርማበር ወይንም በሌላ ስሟ በጫሬ ሲያልፉ በመስኮት ወጣ ብለው ለነዋሪው ‹‹እኛ እምንለው! እዚህ
እምትኖሩት ወዳችሁ ነው ወይንስ ተገዳችሁ? ቆፈኑን እንዴት ቻላችሁት ልጆቼ? ተዉ ሰፈራ እንውሰዳችሁ!›› ቢሏቸው ‹‹አይ ጃንሆይ
ይችን የመሰለች ወርቅ አገር የት ያገኙልናል?›› ብለው መልሰውላቸዋል እየተባለ በሚተረትላት ትንሽዬ የሰው-ሰራሽ ዋሻ ዳር ከተማ
ትኩስ አንባሻ በሻይ ግሩም ቁርስ በላን፡፡ ያንን ዋሻ ሲቆፍር ሰዉ እንዴት እንደተሰቃየ ማን ያውቃል? የዳኛቸው ወርቁን የእንግሊዝኛ
ልብ ወለድ ‹‹ማሚቴን›› አስታወስኩ፡፡ ፍራሽ ጭነው፣ እኛን ተሸክመው ዳገታማውን የኮረኮንች ጎዳና የጀመሩት በቅሎዎቻችን ምስጋና
ይግባቸውና የመንዝን የጉዞ ጠፍር እንሰበስብ ገባን፡፡
አርባሃራ መድሃኔዓለም
መዘዞን
እና ባሽን አልፈን ይገም ከተማ ስንደርስ አንዱ ከዕቅዳችን ውጭ በስነ- ትምህርቱ መምህር በመኮንን ጌታቸው ምክር ያካተትንው ዘንድሮ
ሰዎች አርባሃራ መድሃኔዓለም ሲሉት ወደሰማሁት ገዳም አጭር የእግር መንገድ ጀመርን፡፡ አፋፍ ስንደርስ ሹል ጉልላቱ ብቅ ብሎ ሲታየን
በውበቱ ተማርከን ሹሌን አልን፡፡
ከቤተክርስቲያኑ
ጉዞ መልስ አንድ ሃይለኛው ወልደሃኔ ሙሉነህ የሚባል የ11 ዓመት ልጅና የይገም ትምህርት ቤት የ5ኛ መ ክፍል ተማሪ ውጤቱን የሚያሳይ
መግለጫ ይዞ አይቼው ወዳረፍንበት ሻይ ቤት ጠርቼ ሳይለት አማርኛ 42 ከመቶ እና ሌላውንም በአብዛኛው ከዚያ ያልተሻለ አምጥቶ ሳይ አዘንኩ፡፡ አማካይ ውጤቱ 53.7 ሆኖ ከ48 ተማሪ 31ኛ የወጣውን ይህን ተማሪ መምህርት በስንትወርቅ
ታደሰ ‹‹የተማሪው ውጤት ጥሩ ቢሆንም ከዚህ የበለጠ እንዲሻሻል የወላጅ ድጋፍና ክትትል አይለየው›› ሲሉ የውጤት መግለጫው ላይ
በጻፉት ማስታወሻ አሞካሽተውታል፡፡ እርሱንና ሌሎች ልጆችን አስቤ የያዝኳቸውን ብዕሮች፣ እርሳሶች፣ ከረሜላዎች፣ ቸኮሌቶችና ሌሎችም
ዕቃዎች በመስጠት በአስርት ብሮች በሚሆን ወጭ እነርሱን አስደስቼ እኔም ተደሰትኩ፡፡ መከርኳቸውም፡፡
አንተ ጎዳና
መንዝ
ተኮር አመራሮችና የምርጫ ተወዳዳሪዎች አንዲት የቤት ስራ ልስጣችሁ፡፡ ከጣርማበር ጀምሮ እስከ መሃል ሜዳ ያለው መንገድ ጭራሽ የሚገርም
ነው፡፡ ከ1955-58 ባሉት አመታት የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ መንገዱን ያሰራው በህይወት የሌለው ዶክተር ኢንጂኔር
ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህም ሆነ ራሱን አደራጅቶ አውቶቡስ ገዝቶ መናኸሪያ ሰርቶ እና ጮካ ጮካ መኪና አስተዳዳሪዎች መርጦ ክቤ የተመታው
የመንዝና ግሼ ህዝብ ሞተውም ሆነ ቆመው ያዝናሉ፡፡ የጌራ ምድር ወረዳ አስተዳዳሪው አቶ ሙሉጌታ ‹‹መንዝ አምስት ወይንም ስድስት ወረዳዎችን ይይዛል›› ብለውኝ
ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ህዝብ ከብሄራዊው ዳቦ ትንሽ ይገምጥ ዘንድ ለምን አትሯሯጡለትም? እነዚህ ወረዳዎች ውስጥ ድንቅ ስራ እንኳን
ብትሰሩ እንግዳ በየት መጥቶ ያመሰግናችኋል? በመሃል ሜዳ - መርሃቤቴው የአስፋልት መንገድ ጥሩ ጅማሮነት ግን እንስማማለን፡፡ ‹‹መንዝ የተረሳና ልማት የጠማው አካባቢ ነው›› የሚለው የአቶ ሙሉጌታ ቃል
በጆሯችሁ ሊያቃጭል ይገባል፡፡ በጄ?
መንዝ ጓሳ
ጓሳ የማህበረሰብ
ጥብቅ ስፍራ ደርሰን ገና ሳንጎበኝ ምሳ በልተን ለመመለስ ወደ መሃል ሜዳ ስንጓዝ በስተግራ ባለው ሜዳ የዝንጀሮ መንጋ ፈሶበት አየን፡፡
ረጅም መንገድ እያየናቸው ሄድን፡፡ ያው ግን አብዛኛው የኛ ሰው ግድም የሰጠው አልመሰለኝ - ለእንስሳ ያለው ፍቅር ዝቅ በማለቱ
ሳይሆን አይቀርም፡፡ ‹‹ምግቡ ጥሩ ነው፤ ርካሽ ነው፤ በዚህ ዋጋ ይህ ምግብ እዚህ ቦታ መገኘቱ አሪፍ ነው›› ያለኝን ጎብኝ ከእንስሶቹ
ይልቅ ምግቡ አስደስቶት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ኢንስፔክተር ይሁን ሽፈራው ከአብዛኛው ሰው በተለየ ሁኔታ ‹‹ሰሜን ሸዋ ውስጥ ያለሁም አልመሰለኝ፤ በአረንጓዴ ወቅት ብንመጣ እንዴት ያምራል! የዝንጀሮ መንጋው ያስደስታል፤ የምንሊክ መስኮት
ላይ ሆነህ የኅብረተሰቡን አሰፋፈር ስታይ ያስደንቅሃል›› ሲል ያልጠበቀው ነገር እዚህ ስፍራ በመኖሩ አደነቀ፡፡
ማማ፣
ጌራ እና ላሎ የሚባሉ ሶስት ከጎንደር የመጡ ወንድማማቾች ከ400 ዓመታት በፊት ያቋቋሙት ነው በተባለው መንዝ ጓሳ የማህበረሰብ
ጥብቅ ስፍራ ከምሳ በኋላ 25 ኪሎሜትሩን መንገድ ከመሃል ሜዳ ተመልሰን ደረስን፡፡ አስጎብኛችን አቶ አበበ ጥሩ ማብራሪያ ካደረገልን
በኋላ ጥያቄዎችንም ጠያይቀንና የእንግዶቹን ማረፊያዎች ቃኝተን በእግር የተለያዩ የስፍራውን አካባቢዎች ለማየት እንቅስቃሴ ጀመርን፡፡
ስፋቱ ከ72 እስከ 100 ስኩየር ኪሎሜትር ይሆናል የሚባለውን ስፍራ ለመጎብኘት የሶስት ቀናትና የአራት ሌሊት ቆይታ ያስፈልጋል፡፡
የኛ ጉብኝት ግን መጠነኛ ቅኝት ነው የሚሆነው፡፡ በጽድ ጫካ ውስጥ አልፈን የአስታና የጓሳ ምድሩን በሚገባ ከቃኘን በኋላ ይፋትን
የምናይበት ስፍራ ላይ ደረስን፡፡ ከዚያ ደጋማ ስፍራ ቁልቁል ወደ አጣዬ ማማተር ልብን ይሰውራል፡፡ የጦስኙ ሽታ፣ በስፍራው መሆን
የሚሰጠው የአዕምሮ ሰላም፣ የንፋሱ ሽውታ እና የመልከዓምድሩ አይነ ግቡነት እዚሁ ዋሉ እደሩ ብሎ አንቆ ይይዛል፡፡ አሜሪካውያኑ
ተመራማሪዎች እዚያ መኖሪያ ሰርተው የሚኖሩት መች በደህና ነው! አንዱ
ግን የሚኖርበት ቤት የድንጋይ ካቡ ተንዶበት ሞቷል ሲሉኝ አንጀቴን በላው፤ እናቱ ውሃ ግተው ሳያስታምሙት ማረፉ ያሳዝናል! ለጉብኝታችን
ይረዳ ዘንድ የያዝንው የእግር ኳስ ስለነበር እየተጫወትን ትንሽ ጊዜ ካሳለፍን በኋላ ቀይ ቀበሮ ትገኝበታለች ወደተባለው ስፍራ ሄድን፡፡
በዚያም በየቀበሮ ጉድጓዱ ብንዟዟር ቀበሮ የገባችበት ይጠፋል፡፡ አበበ እንደተጨነቀ ያስታውቃል፡፡ ‹‹እዚህ ጋ በዚህ ሰዓት ብዙ ቀን ትታይ ነበር፤ ትናንትም አይቻታለሁ››
በማለት ተቆጨ፡፡ በዚህ ስፍራ የማታ ጸሐይ እየሞቅንና እያወራን ፎቶ ስንነሳ፣ በአጉሊ መነጽርም ቀበሮ ስናፈላልግ ቆየን፡፡ ከአንድ
እስከ ሁለት ሰዓት ከሚሆን ቆይታ በኋላ ተሳፍረን ወደ መሃል ሜዳ እየጨፈርን ሄድን፡፡
በተያዘልን
በነጻነት ቡና ቤት ራት እየበላን እና መጠጥ እየጠጣን ከወረዳው አመራሮች ጋር ስለ መንዝ ጓሳ ውይይት አደረግን፡፡ በውይይቱ ላይ
ከኛ ከጎብኝዎች ወገን የተነሳው የመጀመሪያው ነገር ‹‹የመንዝ ህዝብ ራሱ ስፍራውን ማየት አለበት፤ ሰርግን የመሳሰሉ በዓላትን እዚያ
እያከበረ አውቆ ማሳወቅ አለበት፡፡ ከሌላ ፓርክ ለምን ብርቅዬ እንስሳትን አታመጡም?›› የሚል ሲሆን ሃላፊዎቹም አምነውበት ማስተዋወቅ
እንደሚያስፈልግ ተግባብተናል፡፡ ከሌላ ፓርክ እንስሳት አምጡ ለሚለው ሃሳብ ተመራመሩበት የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በጣም አንገብጋቢ
የነበረው ጥያቄያቸው ግን ‹‹በጓሳው ምድር ላይ እንደ አረም እየበቀለ ጓሳውን ሊያጠፋው በደረሰው አረም በ‹‹ነጭሎ›› ላይ እንድትመራመሩልን
የድረሱልን ጥሪ እናስተላልፋለን!›› የሚል ነው፡፡ ‹‹ጓሳ ልብሴ፣ ጓሳ ጉርሴ›› እያለ በጓሳው ክልል ውስጥ የቤት እንስሳት ለሚያስገቡ
ሰዎች እንስሳቶቻቸውን እስከማረድ የሚከብድ ቅጣት እየጣለ ስፍራውን ጠብቆ ላኖረው ኅብረተሰብ የጓሳ አደጋ ላይ መውደቅ የአስቸኳይ
ጊዜ አዋጅ የሚያሳውጅ ነው፡፡ ‹‹ጓሳ እንዴት ቆየ ተብሎ ቢጠናልን እና የአካባቢ ጥበቃው ወደፊትም በዘመናዊ መንገድ እንዲካሄድ
ያግዘን ነበር›› ሲሉ የወረዳው ሃላፊዎች ሌላ ጥያቄን ለዩኒቨርሲቲው ልዑካን አቅርበዋል፡፡ ‹‹የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ደብረብርሃን
ዩኒቨርሲቲ ላይ ቢከፈት ለእኛ ያግዘን ነበር›› ብለው መንዞች ባቀረቡት ሃሳብ ግን አልስማማም፡፡ ዩኒቨርሲቲው ደቡብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ
እና ምዕራብ ኢትዮጵያን ማን ሊጎበኝለት ነው መንዝ የሚሄደው? የትኛው ትምህርት ክፍል ነው በሰሜን ሸዋ ላይ እዚህ ግባ የሚባል
የመስክ ጉብኝት ተማሪዎቹን ይዞ የሚወጣው? ቱሪዝምስ ቢከፈት መንዝና ሌሎች የሰሜን ሸዋን ስፍራዎች በአይኑ ሙሉ ያያቸዋል ወይ?
ሰሜን ሸዋ መች ለሽርሽር ያመቻል?
ባየው
ነገር መደሰቱን ገልጾ ‹‹ሰዉን የሚያስደስት ነገር ይኖር ይሆን? እያልኩ እየፈራሁ ነው የመጣሁት፤ ሰዉ አንሄድም ሲል ግን ሰብረን
ነው የመጣንው›› ያለው የባህል ማዕከሉ ሃላፊ ዝናወርቅ አሰፋ የገባቸውን ቃሎች ዩኒቨርሲቲው ቢፈጽም አበጀህ ያስብለዋል፡፡
አስታ
እና ጅብራን የሚያካትት የእጽዋት ቅርስ፣ አንኮበር ሶረኔን እና ቅልጥም ሰባሪን ጨምሮ ብርቅዬ አዕዋፍን፣ ቀይ ቀበሮንና ጭላዳ ዝንጀሮን
የመሰሉ በሃገራችን ብቻ የሚገኙ እንስሳትን የሚይዘው ጥብቅ ስፍራ የመንገድ ችግር ብቻ አይደለም ያለበት፡፡ የእንግዶች ማረፊያው
ምድጃ እና ኩሽና ከማከራየት በዘለለ ምግብ ቢያዘጋጅ እና የአገልግሎቱን አድማስ ቢያሰፋ ጥሩ ይሆናል፡፡ ‹‹አንድ እንግዳ ቢመጣ
ለማስተናገድ የተሟላ ነገር የለም›› እንዲል አበበ ግሩም፡፡
ጎንደር
፣ ባሌ፣ አቡነ ዮሴፍ (ወሎ) እና ጓሳ ብቻ ያለችው ቀይ ቀበሮ በሌላው ዓለም እግር እስኪነቃ ቢዞሩ አያገኘኟትም፡፡ በማግስቱ 12፡00
ሰዓት ላይ ወደ ደብረሲና የመልስ ጉዞ ስናደርግ ይህችን ብርቅዬ እንስሳ መንገዳችንን ስታቋርጥ አይተናት ቆመን እና ቀርበን ለማየት
በቃን፡፡ ለአበበም ስልክ ደውዬ እንዳየኋት ነግሬ አስደሰትኩት፡፡
ስንመለስ
አበበ እንዲህ እያለ ያስቀን ገባ -
‹‹ሚስት
ከመዘዞ፣ ምን ተይዞ፤
ሚስት
ከማማ፣ ከሆነማ፤
ሚስት
ከግሼ፣ ይሁን እሺ፡፡››
ቁም ነገርም
አለው አቤ፣ ‹‹የመንዝ ኅብረተሰብ ችግር ውስጥ ያለ ስለሆነ የአካባቢ ጥበቃው ከእርከን ስራ በዘለለ ቢሰራበት›› የሚል፡፡
ከደብረሲና መልስ ይህ አስተያየት ተሰጥቷል - ‹‹ከላልይበላው ጉዟችን ይህኛው በልጦብኛል፤ ሁሉ ነገር
በቅንጅት ተደርጓል፡፡ በቡድን ተበልቷል፤ ታድሯል፤ ቀድሞ እዲዘጋጅ ተደርጓል›› ተዋበች
አብዱ፡፡ ተዋበች ግን የዘነጋሽው ነገር ቢኖር ትምህርት ቤት ውስጥ እንድናድር ወረዳውን አናግረን የነበረው ነገር ሳይፈጸምልን ቀርቶ
ነጻነት ቡና ቤት አድረናል፡፡ በእርግጥ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ‹‹የአንድ አልጋ እየከፈላችሁ ፍራሻችሁን መሬት ላይ እያነጠፋችሁ
አምስትም ስድስትም እየሆችሁ በነጻ ተኙ›› ብለው ባለቤቱ አቶ ካሳዬ ስለፈቀዱልን በሙሉ ተጓዡም በአንድ ቤት ባይሆን የተወሰንን
ሰዎች እየሆንን በትናንሽ ቡድኖች ስናወራ አድረናል፡፡
የመንዝን ጉዳይ ሳንጨርስ በመጨረሻም
ደብረ ብርሃን ከተመለስኩ በኋላ ስለ ጓሳ የሰማሁትን ወግ ላውጋችሁ፡፡ በቀደምት ጊዜያት ጓሳ በጣም ሽፍታ የሚበዛበት ስፍራ ስለነበር
ተማሪን ጨምሮ ማንም ሰው በታጣቂ አጀብ ነበር የሚያልፍበት፡፡ ባለቤታቸው
ሳር እያበላቸው ሳይሆን ወደሌላ ስፍራ ጓሳን አቋርጦ እየሄደ እንደሆነ ለማረጋገጥ ከብቶች አፋቸውን ታስረው የሚሄዱበት የነበረው
ይህ ስፍራ አንድ ሰው ከብቶቹን አስገብቶበት ሳር ሲያበላ ከተገኘ ከብቱ ይታረድበታል፤ እርሱም ይገረፋል፡፡ አንደኛው አስገራፊ አቶ
ወልዴ ሸረሸር ይባሉ እንደነበር መንዜው አቶ ቀማው አጫውተውኛል፡፡ ወደፊት ከአቶ ወልዴ ልጆች ጋር ብራና ቃለ መጠይቅ ለማድረግ
ትሞክራለች፡፡
ቅዳሜ፣ የካቲት 28፣ ደብረሲና
በጣርማበር
ዋሻ እንደደረስን ጠባቂዎቹን አስፈቅደን በዋሻው ውስጥ በእግር መንገዱ የእግር ጉዞ አድርገን ይፋት እና ደብረሲና
በግልጽ በሚታዩበት ስፍራ ላይ ስንደርስ ዝናወርቅ ከዳኛቸው ወርቁ ልብወለድ ከአደፍርስ ላይ ስለነዚህ ስፍራዎች የሚያትተውን የመጀመሪያውን
ገጽ አነበበልን፡፡ ከዚያም ደብረሲና ከተማ ገብተን የደራሲ ዳኛቸው
ወርቁን አደባባይ እና ሐውልት አየን፡፡ የዳኛቸው ወርቁ ሐውልት በአዲስ መልክ ተሰርቶ በማየታችን ባለፈው ዓመት ወደስፍራው በግላችን
ደራሲውን ለማሰብ ተጉዘን የነበርንው ጓደኛሞች ተደሰትን፡፡ ከዚህ በኋላ ቁርሳችንን በልተንና ፍራፍሬ ገዝተን ወደ ሰላድንጋይ ከተማ
ጉዟችንን ጀመርን፡፡
በሰሜን
ሸዋ የታወቀ መስህብ አንኮበርና መንዝ ጌራ ነው፡፡ ከነዚህ ስፍራዎች ሌላ ያልታወቀ ስፍራ ልናይ ነው የሄድንው በቀጣዩ ቀን፡፡ ሰላድንጋይ
ከተማ ሳንደርስ ተጓዡ ደብረምጥማቅ ማርያም ላይ ወርዶ በእግር ወደ ጻድቃኔ ማርያም ሄዶ ተሳልሞ ሰላድንጋይ ከተማ ሊገባ ቻለ፡፡
ከዚያም ከአንድ አለት ወደተፈለፈለው ወደ ዳግማዊ ላሊበላ ምስካበ ሃዙናን መድሃኔዓለም ገዳም አቀናን፡፡ 41 የሱባዔ ክፍሎች ያሉትና
ሶስት አብያተ ክርስቲናትን በአንድ በር ገብተው የሚያዩበት ገዳም በጥቂት ሰዎች ለመሰራት ሁለት ዓመትም አልፈጀበት፡፡ በዋነኝነት
ፍልፍል አብያተክርስቲያኑን የሰሩት፣ ያሰሩት እና አሁንም እያስተዳደሩት ያሉት አባት ናቸው እኛን ያስገበኙን፡፡
ቀጥሎ
ሰላድንጋይን ሰላድንጋይ ያስባላትን ግዙፍ ድንጋይ ጎብኝተን እላዩ ላይ ቆመን ፎቶ ተነስተን ወደ አጼ ምንሊክ ቅድም አያት ወደ ልዕልት
ዘነበወርቅ ሰገነት አቅንተን ጉብኝታችንን ጀመርን፡፡ ይህን ስፍራ በቅርቡ በስፍራው የተተከለውና እየተገነባ ያለው የቅዱስ ገብርኤል
ቤተክርስቲያን ግዛቱን ተሻምቶታል፡፡ ከሰገነቱም ቤተክርስቲያኑ ጎልቶ ይታያል፡፡ ምን ይሻል ይሆን?
ሳሲት - እንግድዋሻ
ከዚህ
በኋላ ጉዞ ከሰላድንጋይ በስተምዕራብ 20 ኪሎሜትር ወደምትርቀው ወደ ሳሲት ከተማ የተደረገ ሲሆን ራት ተበልቶ ሜንሽን ፊዩር ሜንሽን
ባሰራው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እረፍት ልናደርግ ስንሄድ ህዝቡ በሆታ ነበር የተቀበለን፡፡ ህዝባችን የተማረ ሰውን እንዴት
እንደሚያከብር ልብ በሉ፡፡ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፣ የዘጋቢ ፊልም ትዕይንት፣ የስነ-ጽሁፍ ምሽት
እና ምክክር ተደርጎ በሁለት መማሪያ ክፍሎች እያወራን እንድናድር ተደረገ፡፡
በማግስቱ
እንግዱ በተባሉ የአገሩ አቅኝ ስም የተሰየመውን አንድ ግዙፍ ታሪካዊ ዋሻ ለማየት ጠዋት 1፡00 ላይ የእግር ጉዟችንን ሳሲት ከተማን
ለቀን ወደ ሰሜን አቅጣጫ የጠዋት ጸሐይ እየሞቅን፣ እዚያው ያስጋገርንውን ሁለት ዳቦ በሞሰብ ይዘን ጉዞ ጀመርን፡፡ ጥሩ ጫማ አንዲያደርጉ
ለተጓዦች በበተንንው ማሳሰቢያ አስቀድመን ያሳወቅን ቢሆንም በነጠላ ጫማም የመጡ ነበሩ፡፡ አብረውን ካደሩትና ሞቅ ባለ መልኩ ካስተናገዱን
የወረዳው የባህል ቡድን አባላትና ሰራተኞች እንዲሁም ከሳሲት ነዋሪዎች ጋር የምናደርገውን ጉዞ እኔ ከፊት ካለው ተጓዥ ጋር ሆኜ
ነበር የምጓዘው፡፡ ዋሻው በር ጋ ልንደርስ ስንል ያለችውን አስቸጋሪ መንገድ ትተው በቀናው መንገድ እንዲመጡ እኔና ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች ስንነግራቸው የማይሰሙን ሰዎች ነበሩ፡፡ አደጋ ሊደርስባቸው ብሎ የዳኑ ሁለት ሰዎችም
ነበሩ፡፡ ገና እዋሻው ውስጥ ከመግባታችን ከኋላ ከነበረው ቡድን ያሉ ተጓዦች ‹‹እንደዚህ አይነት መንገድ እንደሆነ አልነገርከንም፣
ቁልቁለት አለው አላልክም፣ አሁን ጸሐዩ ሳይበረታ እንመለስ›› ሲሉ አስገረሙኝ፡፡ ገና ዋሻውን ሳያዩት፣ ውስጣውስጡን ሳይጎበኙት፣
እዚያ የተገኘውን በርካታ የአገሬውን ነዋሪ ትተው መሄድ ሳይከብዳቸው፣ ሊመጣ ትንሽ ጊዜ የቀረውን ዳቦና ጠላ ሳይቀምሱት እንዲሁም
ዋሻው ውስጥ ለማድረግ ያሰብናቸውን ብዙ መርሃ-ግብሮች ሳይታደሙ እንሂድ ሲሉ ደነቀኝ፡፡ አንድ አካባቢውን የሚያውቅና እየደጋገፈ
የሚወስዳቸው ወጣት ሰጥተናቸው ተመለሱ፡፡ የቀረው ግማሹ ሰው ከአገሬው ጋር ግሩም ጊዜ ማለቂያውን ባላየንው ዋሻ ውስጥ አሳለፈ፡፡
በጠዋት እንደምንመጣ እንዳልተነገራቸው የነገሩን የዋሻው አቅራቢያ ስፍራ ነዋሪዎች የእድራቸውን ስብሰባ ከጠዋቱ አራት ሰዓት በዋሻው
ውስጥ እንደጠሩ ነገሩን፡፡
ዋሻው
ቢያንስ እኛ በዚያን ቀን ያየንው ክፍሉ የአንድ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ የሚያክል ሲሆን ከጣልያን የአምስት አመት ቆይታ ጋር የሚያያዝ
ታሪክ አለው፡፡ ካሳዬ ወንዳፈረው የተባለ አርበኛ የእኔን አያት ዘነበ ድረሴን ጨምሮ የሳሲትና አካባቢውን ህዝብ በሙሉ ከነከብቱ
እዚህ ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እየተዋጋ አድኖበታል ማለትን ሰምቻለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዶክተር ሲቪል መሃንዲስ ኃይለጊዮርጊስ
ወርቅነህም የህይወት ታሪካቸውን በሚተርከው መጽሃፋቸው ላይ ሳሲት አቅራቢያ ባለ ትልቅ ዋሻ እርሳቸው የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ በመጋቢት
1931 ዓ.ም. ቤተሰቦቻቸው የነበሩበት ከ300 በላይ ጠመንጃ የያዘ ጦር የነበረው ህዝብ ተጨፍጭፎ ሴቶችና ህጻናት ስላልተገደሉ
ተርፌ ለዚህ በቃሁ ይላሉ፡፡ ይህ ዋሻ ለእኔ እንግድዋሻ ይመስለኛል መጽሃፋቸው ላይ ካለው ገለጻ አንጻር ሳስተያየው፡፡ ስለዋሻው
ታሪክና የወደፊት ሁኔታ ውይይት ተካሂዶ ሁሉም አካላት የየራሳቸውን የቤት ስራ ወሰዱ፡፡ በተለይ ነዋሪው መንገዱን ለማስተካካል ቁርጠኛ
መሆኑን ገለጸ፡፡ የምሁራንን አትኩሮት ስለሚፈልግ የዩኒቨርሲቲያችን የታሪክና ተዛማጅ ጥናቶች ሊቃውንት ሄደው ቢጎበኙት የሚል ሃሳብ
ዋሻው ውስጥ የተገኘንው ሰዎች ሰንዝረናል፡፡
በዋሻው
መግቢያ ላይ ተቀምጦ የወረዳው የባህል ቡድን አባል የሆነችን ትንሽ ልጅ ያናግር የነበረው መምህር ዘላለም ተሸመ ‹‹ይህች ልጅ የአምስተኛ
ክፍል ተማሪ ስትሆን አንደኛ ነው የምትወጣው፤ አድጋ ሳይንቲስት ሆና በዚህ ዋሻ ላይ መመራመር ትፈልጋለች፤ አስጨብጭብላት›› ብሎኝ
ለህዝቡ ነግሬ አስጨበጨብኩላት፡፡
የወረዳው
የባህል ቡድን የጀመረው ዘፈንና ፉካሮ በአባቶች ፉካሮና ሽላሎ ተተክቶ ከአፍታ በኋላም ሁለቱም ይፈራረቁ ገቡ፡፡
‹‹ጣሊያን
መንገድ ሰሪ እንግሊዝ መሪ ነው፣
የዚህ
ሁሉ ጠቅላይ ኃይለ ስላሤ ነው››
ሲሉ የፎከሩት
አባት ከጃንሆይ ወዲህ የነገሱትን ስድስት አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች ረስተዋቸው ነው መሰለኝ፡፡ ወይንም ከነዚህ ሁሉ እንደ አቶ ቡልቻ
ደመቅሳ ሁሉ ጃንሆይን አስበልጠው ሳይሆን አይቀርም፡፡
‹‹እናንተ
የዋሻውን ታሪክ ማግዘፍ ስለፈለጋችሁ አንደኛው ሰውዬ እኔ ልጅ ሆኜ የማውቀው አባቴ እዚህ ዋሻ ውስጥ ፍየሎች ሲገቡብኝ ለማስወጣት
ስመጣ ይህ ዋሻ እኮ አባቶቻችን ጣሊያንን የተዋጉበት ነው ሲለኝ ነው፤ የማውቀው ይህን ብቻ ነው ሲል ምንም አልሰማችሁትም፡፡ እስኪ ሌላ ሰው ደግሞ ይናገር ብላችሁ እሱን ችላ አላችሁት፤›› አለኝ መምህር
ዘላለም ተሾመ ከጉዞው መልስ፡፡ ይህን ትችት በመጠኑም ቢሆን የምቀበለው
ሰውየውን አቋርጠናቸው ከሆነና ትህትና ነፍገናቸው ከሆነ ነው፡፡ ታሪኩን የተሻለ የሚያውቁት ሰዎች ስላሉ እነሱ ይናገሩ ለማለት አስቤ
ነበር በኔ ቤት፡፡ ‹‹ከመንዝ ይልቅ ለተጉለት ታዳላለህ፤ መሃል ሜዳ ከተማንና ገበያውን ቅዳሜ ጠዋት እንድንጎበኝና እንድንገበይ
የታቀደው ሲሰረዝና በጠዋት ወደ ደብረሲና እንሂድ ሲባል እያወቅህ ዝም ብለሃል›› ያለኝን ግን አልቀበለውም፡፡ ምክንያቱም ገበያው
ደብረሲና መገብየት ይችላል ብዬ በማሰብና ለቀሩት ስፍራዎች መጎብኛ በቂ ጊዜ ለማግኘት አስቤ ስለሆነ፡፡
‹‹እንግድዋሻን
ያላዩት ሰዎች እንዲያዩት ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እንደምሰብክ ቃል እገባለሁ፡፡ መንገዱ ግን ቶሎ ቢሰራ ጥሩ ነው - አንድ ሰው ቢጎዳ
ገጽታ ስለሚያጠፋ›› ይላል አበበ፡፡
በመጨረሻም
በሁሉም በጎበኘናቸው ስፍራዎች ስለተደረገልን መስተንግዶ፣ ስለተጓዦች መነሳሳት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲያችን ስላደረገልን ትብብር በማመስገን
መምህር ዘላለም ተሾመ ስለ አጠቃላይ ጉዞው ስሜቱን በገለጸበት አረፍተ ነገር ሃሳቤን ልቋጭ - ‹‹አርብ ዕለት በጓሳ ምድራዊ ዓለማችንን
አየን፤ በማግስቱ ቅዳሜ በምስካበ ኃዙናን መድሃኔዓለም ገዳም የእግዚአብሔር መንበር ገነትን አየን፤ ነገር ግን እሁድ በመጨረሻም
የሚያሳቅቀውንና የሚያስፈራውን የሲዖልን መንገድ አየን፡፡››
ማክሰኞ 10 ማርች 2015
ቅዳሜ 24 ጃንዋሪ 2015
THIS IS A THREE DAY STORY
THIS IS A THREE DAY
STORY THAT UNFOLDS IN KEMISE.
Script writer –
Mezemir Girma
Primary Learning
Objective – The primary learning objective of this episode is to teach children
learn and apply some safety rules around the house.
Secondary Objective:
The secondary objective is to develop in children an awareness of some of the
cultural features of their societies.
Synopsis: Olyad
falls down from a big Shola tree while he was trying to take some fruits down.
He injured his leg and he was given a massage by a local physiotherapist. His
friend, Fuad, tells his classmates that Olyad was sick, and the whole class
visited the sick boy. Olyad’s parents, the teacher, and the students raise some
safety issues, and they stress the need for the application of the safety rules
in children’s lives. The following day, Olyad recovers and walks to school.
[Olyad is asleep in
bed.]
Dad: Olyad, haven’t
you woken up?
Olyad: Dad I am sick.
Dad: Oh my son! Is last
night’s accident still affecting you?
Olyad: Dadi, I
cannot move my leg.
[Dad goes to Olyad’s
room, looks at Olyad’s left leg and tries to see the swelling, which was big.]
Dad: Oli let me call
Etye Zenebech, and I will be back. My
love, please take care of our son until I call her.
[Dad rides his horse
to Etye Zenebech’s home to call her.]
Dad: Morning Etye.
Etye Zenebech:
Morning.
Dad: Etye Zenebech,
you are hard working. I see you working in this garden every time I come here.
Etye Zenebech: I was
at the church in the early morning, and I have just started weeding.
What brought you
here this morning? Is everything safe?
Dad: Olyad fell from
the Shola tree yesterday.
Etye Zenebech: Oh my
son, why did he climb that big Shola tree?
Dad: We did not see
him. He used the ladder and the ladder fell. He wanted to eat the Shola fruits.
[Dad took Etye Zenebech on horseback to his
home.]
Etye Zenebech: Oli,
my lion, the good boy, I never forget the water you fetched me from the stream.
Where is he sleeping? [She goes to his room.]
[Mom carries Olyad and
takes him to the mattress on the floor.]
Olyad: Oh my leg! Eh!
Eh! Eh!
Dad: Oli, you will
recover soon! Etye Zenebech will treat you well.
Etye Zenebech: Bring
some hot water and butter.
Olyad: Don’t touch my
leg please Mama Zenebech. It is painful! Mama Zenebech, please leave me alone,
go to your home. I will go to school with my friends.
Fuad: [calling from
outside] Olyad, the sun has risen, let us go to school. Hurry up please!
Dad: Fuad, he will
not go to school today. He is sick. You will visit him when you come back.
Fuad: Oh my friend!
Let me visit him now.
Dad: Fuad he will
say he has to go with you. Please go with Shambel and Addis.
Fuad: Ok Olyad’s
father. We will visit him in the afternoon.
Dad: Yes, when you
go please watch out the dogs at Worke’s house.
Fuad: Ok I will not
get closer to where the dog sleeps.
[Etye Zenebech
washes Olyad’s leg with hot water and starts to smear it with the butter. Olyad
weeps.]
Dad: Olyad please don’t cry. You will recover
soon.
Olyad: Don’t touch
that part Mama Zenebech. Uuuuu!!
Mom: Oli, once you
finish this, I will make you a good breakfast.
Dad: You will make
him a good chechebsa.
[Etye Zenebech wraps
the knee with a bandage and finishes the treatment.]
Etye Zenebech: Olyad
you will walk safe just tomorrow. Let me go home. I will bring you milk after I
milk the cows.
Dad: You will go
after you drink coffee Etye Zenebech.
Etye Zenebech: You
know I have to look after the cows till the kids come from school. Let me go
just now please.
Mom: Okay Etye Zenebech.
Please come in the afternoon when the kids come back and replace you look after
the cows.
Mother Zenebech:
Bye! Olyad! Nagaatti olii!
Mom: Dad I am making
the coffee. Please take Oli to the main room.
[Dad takes Oli to
the main room.]
[Mom brings coffee
and all the coffee gears.]
Dad: Olyad, drink
this cup of tea. I and your mother will drink coffee.
Mom: Oli, didn’t I
tell you not to climb that tree? Didn’t I say that you should ask us to bring
you fruits down? What if the ladder fell on the girl?
Dad: [to Mom] My
love, last time you remember that he spilt the boiling water from the stove on
his sister’s leg when he was walking fast.
[Olyad cries.]
Dad: Why are you
crying? It is your mistake, isn’t it? Drink the cup of tea now.
[Olyad drinks the
cup of tea.]
Mom: Have you
forgotten what the nurse told you when she treated your sister?
Olyad: She said,
“Keep everything clean including pets and play carefully.”
Mom: She also told
you, above all, to respect family orders.
Dad: Don’t sit on
things tilted. Do you remember this?
Olyad: She also told
me not to put into my mouth a dirty material or anything that is not food.
Dad: You just know
everything it is only when it comes to applying these that you fail. How would
you forget her advice?
Olyad: Dad, I wanted
Shola when you were away. I wanted to give it to my sister because she asked me
to give her.
Mom: Whoever says
whatever they want to say, will you expose yourself to danger? She is a small
kid. Why didn’t you tell her to wait till father comes?
[Dad goes out,
climbs up the tree using the ladder and brings as much Shola fruits as
possible. As he comes back the main room, he saw twenty five of Olyad’s
classmates coming to his home with their teacher.]
Dad: [calling out to
Olyad] Olyad your teacher and classmates are here to visit you.
Olyad: [looking to
the door] Oh! Where are they?
Dad: Oh have you
come? Please go in.
Wasiya: Ok sir! How
is Oliyad?
Dad: He is good. Let
us go in and you will see him.
Teacher: Good
morning Oliyad’s father. Is your dog tied?
Dad: Good morning
miss Etsegenet. Yes! It is in its cage. Don’t worry. Come in, please.
Teacher: Is Oliyad
doing well? It is Fuad who told me this morning, and I decided to bring the
students here during their break time.
Dad: Yeah! He is
recovering. Please go in.
[All of them go into
the house.]
Teacher: Olyad how
are you doing?
Olyad: I am good.
Teacher: Can you
show me your sick leg?
Olyad: Yes.
Teacher: Oh it is a
minor injury. It will come to normal soon.
Dad: We hope so.
Teacher: I want
students who are the members of the Red Cross to remind us something. What did
the nurse teach you last time? What are the preventable problems you may face?
Shewa: Don’t play on
dirty places.
Beeminet: What about
fire?
Teacher: Yes it is
the most destructive thing if used improperly.
Kahsay: Teacher, in
addition to this, we should void slippery places that result from spilling
water on surfaces.
Abdu: Children must
use electric materials carefully. Don’t touch switches with wet hand if they
are vulnerable.
Sakote: Bathing and
swimming should only be with the guidance of with parents or grownups.
Hadas: Children
should avoid using chemicals and drugs except with the help of grownups.
Teacher: Can you
tell us what you mean by chemicals and drugs?
Hadas: Teacher,
chemicals are things like detergents and acid. Drugs are that doctors give us
when we are sick. The nurse told us last time that we should not take tablets
or any medicine prescribed for other people.
Hundesa: Avoid
touching and using sharp materials and keeping away from kitchens.
Zinash: Don’t touch
your eyes with dirty hands. I want to add to what Hadas just said. Even if a
certain medicine is prescribed to us, we should take the amount we are ordered
to take.
Kelkay: Use the dust
bin properly. As to drugs, they should be paced where children cannot reach.
Teacher: Cool. Children
I really appreciate you for your advice.
It gives a good lesson for children who don’t know anything about
safety.
Mom: Children, even
if some kids knew, they may not apply what they know. Our son climbed up that
huge tree and fell down. This happened not because he didn’t know that he would
fall, but because he is careless.
Teacher: Olyad why
did you do that?
Olyad: I wanted Shola
fruits.
Teacher: Would you,
for example, rush to a running cow because you wanted to drink milk?
Olyad: No.
Teacher: The same is
true here. You shouldn’t have climbed up that tree.
Olyad: Sorry
teacher.
Teacher: Children,
you have seen what happened to him, yes? Please be careful when you play, walk
or do anything.
[Dad gives them all Shola
fruits and they start eating. They drink the milk Etye Zenebech brought.]
Mom: Olyad!
Olyad: Yes Mom!
Mom: Why don’t you
sing them the song that I sang for you last time?
Olyad: Which song
mom?
Mom: Since they are
eating Shola fruits, sing them ‘Yeshola Fire.*’
Olyad: Before that I
have some advice to children. They should also take care of their younger
siblings.
[They start to
sing.]
Olyad: Yeshola fire
nesh
Yeshola fire nesh
Yeshola fire nesh
Lafuachilish
Mom: Yeshola fire
nesh
Yeshola fire nesh
Yeshola fire nesh
lafuachilish
Olyad: Meseretish
girum
Mom: sholaye
Olyad: Keyet new
minchish?
Mom and all the
other people: Solaye!
Olyad: Gomzhiche metahugn
Mom and all the
other people: Sholaye
Olyad: Abet mamarish!
Mom and all the
other people: Solaye!
Olyad: Abet mamarish!
Mom and all the
other people: Solaye!
Olyad: Eyew yanchi
wubet
Mom and all the
other people: Sholaye
Olyad: Melken akelaw
Mom and all the
other people: Sholaye
Olyad: Min ale
endanchi
Mom and all the
other people: Sholaye
Olyad: Hulum bidelaw
Mom and all the
other people: Sholaye
Olyad: Hulum bidelaw
Olyad: Hulum bidelaw
Olyad: Yeshola fire
nesh
Yeshola fire nesh
Yeshola fire nesh
Lafuachilish
Mom and all the
other people: Yeshola fire nesh
Yeshola fire nesh
Yeshola fire nesh
Lafuachilish
[Mom gives the
children a big ambasha in a gebete, and they eat chatting. They leave the room
saying good bye and wishing Olyad a swift recovery.]
ON THE NEXT DAY
[Fuad comes to
Olyad’s house and the two go to school singing the song they sang the previous
day.]
Etye- a title given
to old women as a form of respect
·
‘Yeshola
Fire’ is an Amharic song by the late legendary singer Tamirat Molla.
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?
'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...
-
6 June 2019 Basic Writing Skills (Sophomore English) Lecture 1.1. Phrases and Clauses 1.1.1. Phrases A phrase can ...
-
እሁድ ከደብረብርሃን ካምፕ ወደ ኦሮሚያ የተመለሱት አማራ ተፈናቃዮች ምን ገጠማቸው? መዘምር ግርማ ደብረብርሃን ረቡዕ፣ የካቲት 13፣ 2016 ዓ.ም. ከብዙ ጭንቀት በኋላ በዕለተ ማክሰኞ ምሽት 4፡1...