እሑድ 23 ኖቬምበር 2025

ብሔራዊ አገልግሎት ሲነሣ

 ብሔራዊ አገልግሎት ሲነሣ 

ከ2008 ዓ.ም. ያለኝ



በኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጊዜ የነበረው ብሔራዊ አገልግሎት በሚገባ የተጠና ነው። ከረጅም ዓመታት በፊት በጉዳዩ ላይ መጻሕፍትንና አጫጭር ጽሑፎችን ያነበብኩ ይመስለኛል። የባህሩንና የአንዲት ሰሜን አውሮፓዊት ተመራማሪ ሥራን መጥቀስ ይቻላል። አንድ የማይረሳኝ ነገር ግን በወቅቱ ተማሪ የነበሩ ሰው ያወጉልኝ ነው። "አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለብሔራዊ አገልግሎት ዉጡ ሲለን ፍርድ ቤት ከሰስነው። የዩኒቨርስቲው መተዳደሪያ ተማሪዎች ብሔራዊ አገልግሎት እንዲወጡ አያስገድድም ነበር። ስለዚህ ሕገወጥ ውሳኔ ነው። ፍርድ ቤቱም ወሰነልን። ዩኒቨርሲቲውን ረታነው። ሆኖም ግን ዩኒቨርስቲ ስንሄድ 'በሕግ ብትረቱኝም መሄድ አለባችሁ። ሳታገለግሉ አትመረቁም።' የትምህርት ማስረጃም አይሰጣችሁም አለን። ተሸነፍን። ሄድን። ስድስታችንም የተመደብነው ኤርትራ ክፍለሃገር ነበር። እንኳንም ሄድን አልን። አገራችንን አየን። በኛ ጊዜ ብሄር አይታወቅም። ትግሬዎችና ኤርትራውያን በትግርኛ ስለሚያወሩ ከመታወቃቸው በቀር ሌሎቻችን በብሔር አንታወቅም። አሁን ድረስ  አማራ ይሁኑ ኦሮሞ የማላውቃቸው የልብ ጓደኞች አሉኝ። እና የጀመርከው ሥራ ጥሩ ነው። የዘር ማጥፋትን ጉዳይ የተመለከተ ትርጉም መተርጎምህ። እኔ ነበርኩ ይህን ዓይነት ነገር መስራት የነበረብኝ። ታስሬ ሳለሁ ወጣቶች አበረታተውኝ ጀምሬ ነበር። አልገፋሁበትም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የዘር ማጥፋት አደጋ ይመጣል አይመጣም በሚለው ላይ በእርግጥ መናገር አልችልም። አረዳዴ ግን እንደሚመጣ ነው። የኔ ትንታኔ ስህተት ሆኖ አደጋው ባይመጣ ምንኛ ደስ ባለኝ። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በመልክ እንለያያለን? አንለያይም። በብዛት ተመሳሳይ ገጽታ አለን።" 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አቅራቢያ ቢሮ ወዳለው ፕሮፌሰር ፖለቲከኛ ዘንድ ሄጄ ያሉኝም ተመሳሳይ ነበር። "ሩዋንዳስ ሁለት ብሔሮች ናቸው። እነሱ የተላለቁ እኛማ 80 ብሔሮች ሆነን ምን እንደሚበጀን አላውቅም። እግዚአብሔር ይሁነን እንጂ!"

ሌላኛው ታዋቂ ዶክተር አንብቦ ቢያበረታታኝም የግል አቋሙን ግልጽ አላደረገልኝም።

እናንተስ?

ብሔራዊ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አገልግሎት ያኔም አጨቃጫቂ ነበር። ውይይትና ክርክር ሊደረግበት ይገባል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ብሔራዊ አገልግሎት ሲነሣ

 ብሔራዊ አገልግሎት ሲነሣ  ከ2008 ዓ.ም. ያለኝ በኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጊዜ የነበረው ብሔራዊ አገልግሎት በሚገባ የተጠና ነው። ከረጅም ዓመታት በፊት በጉዳዩ ላይ መጻሕፍትንና አጫጭር ጽሑፎችን ያነበብኩ ይመስለኛ...