ሐሙስ 16 ኤፕሪል 2015

በዓል ባይኖር ኖሮ

የበዓል ሰሞን የሚገርም ግርግር ትታዘባለችሁ፡፡ በብዛት ሰዎች የመጎብኘት ልማድ ባይኖራቸውም በዚህ ወቅት ግን ተጓዡ ይበዛል፡፡ በሚገርም ሁኔታ የምግብ ዝግጅት፣ ሽያጭና ፍጆታ ደግሞ ይጧጧፋል፡፡ ራድዮ ጣቢያዎች የማስታወቂያ ውርጅብኝ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ የሙዚቃ ግብዣ ብሎም የበዓል ዝግጅቶች ያበዛሉ፡፡ ቴሌቪዥን ጣቢዎችም ልክ ሰሞኑን ኢቢኤስ ከቴዲ አፍሮ ቤት የበዓል ዝግጅት እንደጋበዘን ሁሉ ቀደም ብለው የተቀረጹ ዝግጅቶችን እንካችሁ ተቃመሱ ይሏችኋል፡፡ የበዓል ሰሞን መቼም በአቅም ማነስ፣ ከቤተሰብ በመራቅ፣ በህመም፣ በምግብ አለመመቸትና ሌሎችም ምክንያቶች የሚከፋውም አይጠፋም፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑ ደግሞ እነ እከሌ ቤት ይሄ ተበላ ይሄ ተጠጣ የሚለው ማሳበቅ ይረብሽም ይሆናል በተለይ እንዲህ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ በተለያየበት ወቅት፡፡ ምንም ቢሆን ግን ስንትና ስንት በዓል ሲያሳልፉ የታዘቡት ብዙ ለውጥና ሁኔታ ይኖራል፡፡ ምንም እንኳን ማስታወሻ የመያዝ ልማዳችን ደከም ቢልም የማይረሱ ገጠመኞችና ትዝብቶች ስለሚኖሩ አንዳንዶቹን እያነሳን ብናወጋ ለሁላችንም ያስተምርና ያዝናና ይሆናል፡፡ ታዲያ ወረድ ብሎ ባለው የአስተያየት መስጫ ላይ እንድተጽፈልኝ ነው ይህን ማለቴ፡፡ በመጨረሻም የሚከተሉትን የውይይት ሃሳቦች እነሆ ልበላችሁ! 1. በጃንሆይ ጊዜ ትምህርት 15 ቀን ለፋሲካ ይዘጋ ነበር ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ከሞላ ጎደል አሁንም እየተዘጋ ስለሆነ ለምን መንግስት እውቅና አይሰጠውም የሚል ሃሳቤን በትህትና አቀርባለሁ፡፡ 2. የህዝቡ ኑሮ ይሻሻል ዘንድ የሚታትሩ ሰዎች ዓላማቸው ይሳከላቸው ስትሉ ጸልዩ፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለበዓል በግ ቢያርድ ደስ ይላል! 3. የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው እንኳን አደረሳችሁ ሲላችሁ ምላሹ ምንድነው? 4. እርጥብ ስጋ መብላት ሳይንስና ባህል ከሚጋጩባቸው ተግባራት አንዱ ነው፤ እርስዎ ከሳይንስ ወይስ ከባህልዎ ጋር ተባበሩ? 5.
ብለው አስበው ያውቃሉ? 6. የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች በዓላቸውን ሲያከብሩ እርስዎ ምን ይሰማዎታል? 7. በዓል ሲከበር በሰው አገር ሆነው ያውቃሉ? 8. በ2050 የሚከበረውን አንድ ሃይማታዊ በዓል ስታስቡት ምን ገጽታዎች የሚኖሩት ይመስላችኋል? 9. ዘፈን ለራስዎ ወይንም ለሌላ ሰው ለበዓሉ ጋብዙ ቢባሉ የማንን ዘፈን ይጋብዛሉ? ለምን? 10. መጭውን በዓል በተሻለ ሁኔታ ለማክበር ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ? በመጨረሻም መልካም የበዓል ሳምንት እመኝልዎታለሁ!!!

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...