ቅዳሜ 2 ኦገስት 2025

ካሚሪቱ ኬኒያ

 ካሚሪቱ


በኬኒያ በሚገኘው የካሚሪቱ የማህበረሰብ ትምህርትና ባህል ማዕከል የናይሮቢ ዩኒቨርስቲ መምህራን የጀመሩት በኬኒያ  የመጀመሪያው የአፍሪካ ቋንቋና ከአዳራሽ ዉጪ ቲአትር ሲሆን በቅኝገዢውም ሆነ ከነፃነት በኋላ በመጣው መንግሥት አልተወደደም ነበር። ተዋንያኑ ከህብረተሰቡ ውስጥ የሚመረጡ ናቸው። በተውኔቱ ጽሑፍ፣ በተዋንያን መረጣና በልምምድ ህብረተሰቡ ስለሚሳተፍ እንደ ምዕራባውያን ቲያትር ድብቅነት የሌለውና ሁሉም ችሎታ እንዳለው ያስገነዘበ ተብሏል። ከናይሮቢ ወጣ ብላ በምትገኘው መንደር የሚመደረከውን ተውኔት ኬኒያውያን ከሩቅ ቦታዎች በመኪና እየመጡ ይመለከቱት ነበር።
ከኬኒያ ልዩ ልዩ ብሄሮች ተዋንያንን በማካተት ተውኔቱን ወደ ናይሮቢ ወስደውት በብሄራዊ ታያትርም ሆነ በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ ቲያትር ለማሳየት ያደረጉት ሙከራ በመንግሥት ተስተጓጉሏል።
በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ያሳተሙትና ዓለምአቀፍ ዕውቅና ያላቸው እነ ጉጊ ዋቲዎንጎ በቋንቋቸው ብቻ ለመጻፍ በወሰኑበት ወቅት የነበረው ይህ ቲያትር በአፍሪካ ቋንቋ ህብረተሰቡ ውስጥ ገብቶ መስራት የማህበረሰብ ለውጥን የሚያመጣ፣ አእምሮን ከቅኝግዛትና የእጅአዙር ቅኝግዛት እስር የሚያላቅቅ የተባለለት ነው። መምህራኑ እነ ጉጊ ታሰሩ፤ ተሰደዱ። በ1984 እኤአ ፕሬዚዳንት ሞይ ኪባኪም በቦታው የቲያትሩን ስም ለማጥፋት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሠራ አዘዙ።
ይህ ታሪክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቲያትር የፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ፋቡላ የቀረበበትን ሁኔታ፣ በሃገር ፍቅር ማህበር አገርን ለመከላከል የጥበብ ሥራዎች የቀረቡበትንም ታሪክ ያስታውሳል። ጉጊ ዋቲዎንጎ በአፍሪካ ቋንቋዎች ስለመጻፍና አእምሮን ከቅኝአገዛዝ እሳቤ ሲጽፍ ቀደምት  ኢትዮጵያውያን ደራስያንን ህሩይ ወልደሥላሴንና ግርማቸው ተክለሃዋርያትን በአርአያነት ያነሣል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

‎በአማራ ክልል የግእዝ ትምህርት ይሰጥ በተባለው ላይ

እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄዎችና አስተያየት አሉኝ። ይኸውም በአጠቃላይ ስናየው የቋንቋ ትምህርት አስፈላጊ ነው። ማወቅ አይከፋም። ‎ግእዝን አስመልክቶ የተመረጠበት ምክንያት ይኖረዋል። ምናልባት ቀደምት በኢትዮጵያ የዘመናዊ...