ዓርብ 24 ፌብሩዋሪ 2017

ሦስተኛው የእግር የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ አጤ ምኒልክ የትውልድ ቀዬ!



የካቲት 16 2009
መዘምር ግርማ
‹‹የአንጎለላው ጉዞ ስኬታማ ነበር። አምና ከሄድነው አሥር ሰዎች ዘንድሮ ሁለቱ ብቻ ነን የሄድነው። ስምንት አዳዲስ ሰዎችን ጨምረን ዘንድሮም አሥር ሠዎች ነበርን። የአምናዎቹ አላችሁ? ሳምንት ሐሙስ ደግሞ አንኮበር ነን። ይሄ ዓመታዊ ጉዞ የዓድዋን ድል በማሰብ የምናደርገው ሲሆን የዘንድሮው ሶስተኛ ዓመቱ ነው። ተቀላቀሉን። በቀጣይ ምን ይጎብኝ?
መጎብኘት ይልመድብን!
መዋጮ ያለው የጉዞ ማህበር ቢኖረን ብለን ዛሬ ምሽት በቤተመፃሕፍት በርከት ብለን ተወያይተናል። ልምድ ካላችሁ አጋሩን።››
ከላይ የተጠቀሰው ልክ ከጉዞ እንደተመለስኩ የጻፍኩት ማስታወሻዬ ነው፡፡ ስለ አንጎለላ ለማወቅ ባለፉት ሁለት ዓመታት የጻፍኳቸውን ማስታወሻዎች ከብሎጌ ፈልጋችሁ እንድታነቡ እጋብዛችኋለሁ፡፡ የዘንድሮ መንገዳችን የተለያዩ ትዕይንቶችን ያየንበት ነበር፡፡ ስንነሳ አካባቢ አንድ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ሰልጣኞቻቸውን በሳይክል እየተከተሉ በልምጭ ይቀጣሉ - ሾጥ፡፡ ቀረት የሚሉትን ለማትጋት መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ያየነው ነገር ቢኖር የንጉሥ ሳህለሥላሴ ዋሻ መግቢያው ላይ ቅርስ ፍለጋ በሚል ሰበብ ነዋሪዎች ሌሊት ተደብቀው እንደቆፈሩት ለማየት ችለናል፡፡ ያልሰሩበትን ገንዘብ ለማግኘት የመትጋት አባዜ ወይንስ ይጎበኛል ወይም ምርምር ይደረግበታል ተብሎ ሲታጠር ውድ ንብረት ያለበት መሰላቸው! ምጽዋት ለመቀበል መቀመጥ ነውር ሆኖ ይሁን በሌላ መንገድ በርካታ ኬሻ መሬት ላይ በረድፍ ተነጥፎ ምጽዋት ይጠብቃል - በተለይ የእህል፡፡ አንዳንዱ ኬሻ ነው ሰው አጠገቡ ያለው፡፡ የመጣልኝ ነገር ቢኖር አስር አስራ አምስቱ የአንድ ሰው ነው የሚል ነው፡፡ ስንመለስ ደግሞ እየዘመርን በቡድን ስንመጣ ያዩን የአዲስ አበባና የሌሎች ቦታዎች መንፈሳዊ ተጓዦች ወደ ቤታቸው በመኪና እየተመለሱ ሳለ በመስኮት በማጨብጨብ አበረታቱን፡፡ ሹፌሩም ጭምር፡፡ ፈጣሪ በየቦታው ሲመሰገን ማየት እንዳስደሰታቸውና ክርስቲያናዊ ህብረታቸውን እንዳሳዩን ታዘብኩ፡፡ የቡድናችን አባላት አማተር ዘፋኞች ስለነበሩበት ‹‹ቅዳሴው ሲያልቅበት …›› እንደተባለው ማንጎራጎቸውም አልቀረም፡፡ የአምና ተጓዦችን አስበናቸዋል፡- Alem Ayele Dodge Eden Sale Yitayish Addisu YIDNEK England























































































ቅዳሜ 11 ፌብሩዋሪ 2017

Photos of my morning walk in Debre Birhan, 2017





















ሕንድ የተማረ ወዳጄ ከነገረኝ ላጋራችሁ።


1. ሕብረተሰቡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በጥቅም እንዲተሳሰር ተደርጓል። ለምሳሌ ከዩኒቨርሲቲው ውጪ መጥተው ኢንተርኔት በክፍያ ያስገባሉ፤ ልብስ ይሸጣሉ።
2. ብዙው ሠው እንግሊዝኛ ይችላል። የማንበብ ልምዱም ከፍተኛ ነው። ዘበኞች ዕለታዊ ጋዜጣ ሲያነቡ ይስተዋላሉ።
3.እያንዳንዱ ልማት ኑሮህ ላይ ለውጥ ሲያመጣ ታየዋለህ።
4. ኑሮ እጅግ ርካሽ ነው።
5. ሙቀቱ በብዛት አርባ ቤት ነው።
6. ውበት ከወገብ በላይ ነው።
7. በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ሰር ነው።
8. ኃይማኖት መጠየቅ፣ በኃይማኖት መጥቀም የተለመደ ነው። በየቢሮው የተቀረፀ ጣኦት አላቸው። በሬና ላም እንደ ፈጣሪ ስለሚታዩ ህገመንግሥቱም ጥበቃ ያደርግላቸዋል። አይታረዱም!
9. ሕዝቡ በአራት ደረጃዎች ይመደባል። ይህ አሰራር ኢፍትሃዊነቱ በየዘርፉ ይታያል።
10. ያላገባሃትን ሴት . . . ጨዋ አገር ነው። ጥሎሽ የምትጥለው ሴት ነች። ዱሮ ሴት ከተወለደች ትገደል ነበር። ጥሎሹን ፍራቻ! እንግሊዞች አስተዋቸው።
11. መብት በሽ ነው። ክልሎች ብዙ ጥያቄ በረሃብ አድማ ያስመልሳሉ።
12. ትምህርቱ ጥራት አለው።
13. በሕንድ በትምህርት ጎበዞች ሴቶች ናቸው።
14. አነስተኛ የኪስ ገንዘብ የሚሰጣቸው የውጪ አገር ተማሪዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱም ደምወዛቸው ከሁሉም ያነሰ ነው። ሱዳን አገር በወለደው ልጅ ብዛት ደምወዝ ይከፈለዋል።
15. ሲበዛ ታማኞች ናቸው ሕንዶች።
እዚያ የተማራችሁ ወይም በመማር ላይ ያላችሁ ተጨማሪ ሐሳብ ብትነግሩኝ ፅሑፉን ማዳበር እችላለሁ።
ምን አስገረማችሁ አንባቢያን?

Mezemir Girma

ከታዋቂ አበሾች ሕንድ የተማሩ ፕሮፌሰር መስፍንን አውቃለሁ ። ብዙ ሕንዶች እኛ አገር አስተምረዋል ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ሸርማ ሁለት ኮርስ ሰጥቶኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ 50 ዓመት በጥራትና በሠዓት አክባሪነት አስተምሩዋል።
Edited · Like · Reply · Edit · Yesterday at 10:33pm

Ze Ethiopia Hageri

ሲተዋወቁህ/ሽ የመጀመሪያው ጥያቄያቸው ከየት ሃገር መጣህ እና አግብተሃል/ሻል ነው። ከጋብቻ በፊት ምንም አይነት የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነው፤ በተለይ ለሴት ልጅ። በማንኛውም የግልም ይሁን የመንግስት አገልግሎት መስጫ ቦታ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዜጎቻቸው ነው። ትራንስፓርት ወይም መንገድ ላይ ትህትና እዛውንት ማክበር ብሎ ወንበርን ለቆ ማስቀመጥ ታችኛው ካስት እንደሆነ ማሳያ ነው። የተቀደደ ገንዘብ የሚቀበል ሰው የለም። ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የሀይማኖት እንቅስቃሴ ያለገድብ ማስኬድ ይቻላል። ወ.ዘ.ተ...እጅግ ብዙ ነው እዚህ ላይ ላቁም። ግን እንግሊዝኛ እንኳን በአብዛኛው አይችሉም የተሳሳተ እንዳይሆን መረጃህ መዜ!
Edited · Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Solomon Genet

Fetena wustim hone class wust shint kemetabik fekad meteyek yelem tensto mewutat bicha new( tamagn silehonu). tiyakie lemeteyekm hone lememeles ye astemariwun fekad meteyek yelem, directly memeles bicha new.
Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Barok Seyoum

"ውበት ከወገብ በላይ ነው" ለካ ለዚ ነው ፊልም ላይ ብዙ ጊዜ ፊታቸውን ፊታቸውን የሚያሳየን ከስር ቁምጣ እየለበሱ ነው እንዴ የሚቀረፁት
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Yeshalem Gezahegn

for no. 14, nepals , butans ,maldives were getting pocket money less than ethio i think.
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · 3 hours ago

Mezemir Girma

Afterthought: Indians are festival people. There is a festival everyday.
Like · Reply · Edit · Just now

ዓርብ 10 ፌብሩዋሪ 2017

African Storybook Debre Birhan

Stories written by Debre Birhanis to be published: ቢኒያም አስፋው (The Shepherd and His Best Friend)፣ እዮቢ ቅጣው (Abel and his Sister’s Doll)፣ ቤተልሔም ዋልተንጉስ (Petros and His Dog) ፎዚያ መሐመድ (Amina and Her Animals) በአፍሪካ የተረት መጻሕፍት መርሃ-ግብር ለልጆች ተስማሚና ምርጥ ተብለው ከደብረ ብርሃን የተመረጡ ታሪኮች ስለሆኑ እንደሚታተሙ መረጃ ደርሶኛል፡፡ ይህ ደብረብርሃን ላይ ያካሄድነው ሁለተኛ የተረት መጻፍ ውድድር ውጤት ነው፡፡ የመጀመሪያውን ውድድር ነገር ተነጋግረን እንወስናለን፡፡ ከቢኒያም ውጪ ሦስቱ ያሸነፉት ተረቶች የልጆች በተለይም የሴቶች ልጆች መሆናቸው በጣም ያኮራል፡፡ እናመሰግናለን!

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...