2017 ፌብሩዋሪ 24, ዓርብ

ሦስተኛው የእግር የደርሶ መልስ ጉዞ ወደ አጤ ምኒልክ የትውልድ ቀዬ!



የካቲት 16 2009
መዘምር ግርማ
‹‹የአንጎለላው ጉዞ ስኬታማ ነበር። አምና ከሄድነው አሥር ሰዎች ዘንድሮ ሁለቱ ብቻ ነን የሄድነው። ስምንት አዳዲስ ሰዎችን ጨምረን ዘንድሮም አሥር ሠዎች ነበርን። የአምናዎቹ አላችሁ? ሳምንት ሐሙስ ደግሞ አንኮበር ነን። ይሄ ዓመታዊ ጉዞ የዓድዋን ድል በማሰብ የምናደርገው ሲሆን የዘንድሮው ሶስተኛ ዓመቱ ነው። ተቀላቀሉን። በቀጣይ ምን ይጎብኝ?
መጎብኘት ይልመድብን!
መዋጮ ያለው የጉዞ ማህበር ቢኖረን ብለን ዛሬ ምሽት በቤተመፃሕፍት በርከት ብለን ተወያይተናል። ልምድ ካላችሁ አጋሩን።››
ከላይ የተጠቀሰው ልክ ከጉዞ እንደተመለስኩ የጻፍኩት ማስታወሻዬ ነው፡፡ ስለ አንጎለላ ለማወቅ ባለፉት ሁለት ዓመታት የጻፍኳቸውን ማስታወሻዎች ከብሎጌ ፈልጋችሁ እንድታነቡ እጋብዛችኋለሁ፡፡ የዘንድሮ መንገዳችን የተለያዩ ትዕይንቶችን ያየንበት ነበር፡፡ ስንነሳ አካባቢ አንድ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ሰልጣኞቻቸውን በሳይክል እየተከተሉ በልምጭ ይቀጣሉ - ሾጥ፡፡ ቀረት የሚሉትን ለማትጋት መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ያየነው ነገር ቢኖር የንጉሥ ሳህለሥላሴ ዋሻ መግቢያው ላይ ቅርስ ፍለጋ በሚል ሰበብ ነዋሪዎች ሌሊት ተደብቀው እንደቆፈሩት ለማየት ችለናል፡፡ ያልሰሩበትን ገንዘብ ለማግኘት የመትጋት አባዜ ወይንስ ይጎበኛል ወይም ምርምር ይደረግበታል ተብሎ ሲታጠር ውድ ንብረት ያለበት መሰላቸው! ምጽዋት ለመቀበል መቀመጥ ነውር ሆኖ ይሁን በሌላ መንገድ በርካታ ኬሻ መሬት ላይ በረድፍ ተነጥፎ ምጽዋት ይጠብቃል - በተለይ የእህል፡፡ አንዳንዱ ኬሻ ነው ሰው አጠገቡ ያለው፡፡ የመጣልኝ ነገር ቢኖር አስር አስራ አምስቱ የአንድ ሰው ነው የሚል ነው፡፡ ስንመለስ ደግሞ እየዘመርን በቡድን ስንመጣ ያዩን የአዲስ አበባና የሌሎች ቦታዎች መንፈሳዊ ተጓዦች ወደ ቤታቸው በመኪና እየተመለሱ ሳለ በመስኮት በማጨብጨብ አበረታቱን፡፡ ሹፌሩም ጭምር፡፡ ፈጣሪ በየቦታው ሲመሰገን ማየት እንዳስደሰታቸውና ክርስቲያናዊ ህብረታቸውን እንዳሳዩን ታዘብኩ፡፡ የቡድናችን አባላት አማተር ዘፋኞች ስለነበሩበት ‹‹ቅዳሴው ሲያልቅበት …›› እንደተባለው ማንጎራጎቸውም አልቀረም፡፡ የአምና ተጓዦችን አስበናቸዋል፡- Alem Ayele Dodge Eden Sale Yitayish Addisu YIDNEK England























































































ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት

  በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት ረቡዕ፣ የካቲት 20፣ 2016 ዓ.ም. መዘምር ግርማ ደብረብርሃን   ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ ላምበረ...