ቅዳሜ 11 ፌብሩዋሪ 2017

ሕንድ የተማረ ወዳጄ ከነገረኝ ላጋራችሁ።


1. ሕብረተሰቡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በጥቅም እንዲተሳሰር ተደርጓል። ለምሳሌ ከዩኒቨርሲቲው ውጪ መጥተው ኢንተርኔት በክፍያ ያስገባሉ፤ ልብስ ይሸጣሉ።
2. ብዙው ሠው እንግሊዝኛ ይችላል። የማንበብ ልምዱም ከፍተኛ ነው። ዘበኞች ዕለታዊ ጋዜጣ ሲያነቡ ይስተዋላሉ።
3.እያንዳንዱ ልማት ኑሮህ ላይ ለውጥ ሲያመጣ ታየዋለህ።
4. ኑሮ እጅግ ርካሽ ነው።
5. ሙቀቱ በብዛት አርባ ቤት ነው።
6. ውበት ከወገብ በላይ ነው።
7. በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ሰር ነው።
8. ኃይማኖት መጠየቅ፣ በኃይማኖት መጥቀም የተለመደ ነው። በየቢሮው የተቀረፀ ጣኦት አላቸው። በሬና ላም እንደ ፈጣሪ ስለሚታዩ ህገመንግሥቱም ጥበቃ ያደርግላቸዋል። አይታረዱም!
9. ሕዝቡ በአራት ደረጃዎች ይመደባል። ይህ አሰራር ኢፍትሃዊነቱ በየዘርፉ ይታያል።
10. ያላገባሃትን ሴት . . . ጨዋ አገር ነው። ጥሎሽ የምትጥለው ሴት ነች። ዱሮ ሴት ከተወለደች ትገደል ነበር። ጥሎሹን ፍራቻ! እንግሊዞች አስተዋቸው።
11. መብት በሽ ነው። ክልሎች ብዙ ጥያቄ በረሃብ አድማ ያስመልሳሉ።
12. ትምህርቱ ጥራት አለው።
13. በሕንድ በትምህርት ጎበዞች ሴቶች ናቸው።
14. አነስተኛ የኪስ ገንዘብ የሚሰጣቸው የውጪ አገር ተማሪዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱም ደምወዛቸው ከሁሉም ያነሰ ነው። ሱዳን አገር በወለደው ልጅ ብዛት ደምወዝ ይከፈለዋል።
15. ሲበዛ ታማኞች ናቸው ሕንዶች።
እዚያ የተማራችሁ ወይም በመማር ላይ ያላችሁ ተጨማሪ ሐሳብ ብትነግሩኝ ፅሑፉን ማዳበር እችላለሁ።
ምን አስገረማችሁ አንባቢያን?

Mezemir Girma

ከታዋቂ አበሾች ሕንድ የተማሩ ፕሮፌሰር መስፍንን አውቃለሁ ። ብዙ ሕንዶች እኛ አገር አስተምረዋል ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ሸርማ ሁለት ኮርስ ሰጥቶኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ 50 ዓመት በጥራትና በሠዓት አክባሪነት አስተምሩዋል።
Edited · Like · Reply · Edit · Yesterday at 10:33pm

Ze Ethiopia Hageri

ሲተዋወቁህ/ሽ የመጀመሪያው ጥያቄያቸው ከየት ሃገር መጣህ እና አግብተሃል/ሻል ነው። ከጋብቻ በፊት ምንም አይነት የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነው፤ በተለይ ለሴት ልጅ። በማንኛውም የግልም ይሁን የመንግስት አገልግሎት መስጫ ቦታ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዜጎቻቸው ነው። ትራንስፓርት ወይም መንገድ ላይ ትህትና እዛውንት ማክበር ብሎ ወንበርን ለቆ ማስቀመጥ ታችኛው ካስት እንደሆነ ማሳያ ነው። የተቀደደ ገንዘብ የሚቀበል ሰው የለም። ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የሀይማኖት እንቅስቃሴ ያለገድብ ማስኬድ ይቻላል። ወ.ዘ.ተ...እጅግ ብዙ ነው እዚህ ላይ ላቁም። ግን እንግሊዝኛ እንኳን በአብዛኛው አይችሉም የተሳሳተ እንዳይሆን መረጃህ መዜ!
Edited · Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Solomon Genet

Fetena wustim hone class wust shint kemetabik fekad meteyek yelem tensto mewutat bicha new( tamagn silehonu). tiyakie lemeteyekm hone lememeles ye astemariwun fekad meteyek yelem, directly memeles bicha new.
Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Barok Seyoum

"ውበት ከወገብ በላይ ነው" ለካ ለዚ ነው ፊልም ላይ ብዙ ጊዜ ፊታቸውን ፊታቸውን የሚያሳየን ከስር ቁምጣ እየለበሱ ነው እንዴ የሚቀረፁት
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Yeshalem Gezahegn

for no. 14, nepals , butans ,maldives were getting pocket money less than ethio i think.
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · 3 hours ago

Mezemir Girma

Afterthought: Indians are festival people. There is a festival everyday.
Like · Reply · Edit · Just now

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

Z.A. They warn Oromo parents to advise their kids to avoid interacting with Amhara kids at school.

  Z.A. They warn Oromo parents to advise their kids to avoid interacting with Amhara kids at school. The Shenes said they wanted to aven...