ዓርብ 14 ሜይ 2021

የራስ አበበ አረጋይ ማስታወሻ ስያሜ ሽሚያዎችን አስመልክቶ የቤተመጻሕፍታችን አቋም

 

የራስ አበበ አረጋይ ማስታወሻ ስያሜ ሽሚያዎችን አስመልክቶ የቤተመጻሕፍታችን አቋም

በሁለተኛው የኢጣሊያና ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከነበሩ ፈርጦች ግንባር ቀደሙ ራስ አበበ አረጋይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ጦር በስኬት በመምራት በዱር በገደል ለአምስት ዓመታት ታሪክ ሲያስታውሰው የሚኖር ፍልሚያ አድርገው የሃገራቸውን ነጻነት አረጋግጠዋል፡፡ በዚያ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያን ባንዲራ ካውለበለቡ ጥቂቶች የጦር መሪዎች አንዱ ናቸው፡፡ የኢጣሊያ ፋሽስት መሪዎች የኢትዮጵያን ህዝብ በብሔርና በቋንቋ ከፋፍለው ለመግዛት ይጥሩ በነበረበት በዚያ ወቅት ራስ አበበ አረጋይ በአንጻሩ በሸዋ የአማራና የኦሮሞ ህዝብን አስተባብረው የተራዘመውን ጦርነት በመምራት ለድል የበቁ ናቸው፡፡

ራስ አበበ አረጋይ 1953 መፈንቅለ መንግሥት በአረንጓዴው ሳሎን ግድያ ሕይወታቸውን ያጡት ኢትዮጵያን ከሚወዱትና ለምዕራባውያን ከማይመቹት መሪዎች አንዱ በመሆናቸው ነበር፡፡ 1950ዎቹ ታቅዶ የነበረው ጭሰኝነትን ከኢትዮጵያ የሚነቅል የተባለለት ሰፊ ፕሮጀክትም ሰይፈጸም ቀርቷል፡፡ ከዚያ ወዲህም ሃገሪቱ ወደባሱ ዘርፈብዙ አዘቅቶች በመግባት እድገቷ ቁልቁል እየወረደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ታሪክን ለማስታወስ እነሆ ዘመኑ ደርሶ ራስ አበበ አረጋይም ሆነ ሌሎች የሃገር ባለውለታዎች በትውልድ እየታወሱ ይገኛሉ፡፡ እኔ በግሌ በታሪክ ትምህርት ስለጀግናው ራስ አበበ አረጋይ ተምሬ አልፌያለሁ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ ስመረቅ የመመረቂያ ጽሑፌንም በአርበኞች ተጋድሎ ላይ በተጻፈ ታሪካዊ ልቦለድ ላይ ስሰራ ከዚሁ ፍላጎቴ ይመነጫል፡፡ ከምረቃ በኋላም ታሪካዊ ጉዞዎችን በማድረግ በማስተባበርና የጉዞ ማስታወሻዎችን ጽፌ በማስነበብ አርበኞቻችንና ታሪካችን እንዲታወሱ ጥሬያለሁ፡፡ 2008 .. ከተርጓሚ፣ ደራሲና የትያትር ሰው አሊሹ ሙሜ ጋር ከአዲስ አበባ ወደ ደብረብርሃን ስንመጣ አካባባውንና ታሪኩን እያነሳን መንገድ መንገዱን ስናወራ አንድ ሃሳብ ተነሳ፡፡ ይኸውም አሊሹ ከዚህ ሁሉ ነገር የሚቆጨው ራስ አበበ አረጋይ ለዚህች ሃገር ይህን ሁሉ ውለታ ውለው አለመታወሳቸው መሆኑን ነገረኝ፡፡ በነገራችን ላይ አሊሹ የሃገራችንና የጥቁር ሕዝብ ትግል የሚስበው በማልከም ኤክስንና የማርከስ ጋርቪን ስራዎች የተረጎመ የጥበብ ሰው ነው፡፡ እኔም በጉዳዩ በመስማማት ደብረ ብርሃንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን በእርሳቸው ለመሰየም ተፈልጎ መንግሥት ስለተቀቃወመ መቅረቱን ነገርኩት፡፡ የሆነው ሆኖ ቀድሞ በነበረኝ ፍላጎትና ቁጭት 2008 . በደብረ ብርሃን ከተማ የግል ቤተመጻሕፍት ስከፍት ስያሜውን በራስ አበበ አረጋይ ለማድረግ ወሰንኩ፡፡ ይህም ቤተመጻሕፍት ህብረተሰቡን በነጻ እያስነበበ አምስተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት (ወመዘክር) በደብረ ብርሃን ከተማ ባደረገው የንባብ ሳምንት ወቅት እውቅና ሰጥቶናል፡፡ የግል ቤተመጻሕፍት በፖሊሲ በማይደገፍበተ ሃገር በንባብ ላይ የሚሰራው ቤተመጻሕፍታችን በአፍሪካ ቤተመጻሕፍት ማህበር ንቁ ተሳታፊና በዋና ዋና መርሐግብሮች ኢትዮጵያን የወከለ ነው፡፡ የአሜሪካ ቤተመጻሕፍት ማህበርም በመጽሔቱ ስለቤተመጻሕፍታችን ጸፏል፡፡ ይህ እውቅናና አብሮ የመስራት ፍላጎት ከደቡብ አፍሪካው የርቀት ትምህርት ተቋምና ከሕንዱ ስቶሪ ዊቨርም መጥቶ አብረን እንሰራለን፡፡ በንባብ ላይ ባሳረፍነው አሻራም ምክንያት የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን (ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ዩቱብ ቻነሎችና ጋዜጦች) በቤተመጻሕፍታችን ላይ ዝግጅቶችን በማቅረብ የንባብ ባህልና የቤተመጻሕፍት አገልግሎት እንዲስፋፋ ሰርተዋል፡፡ የቤተመጻሕፍቱ አገልግሎትና ስራ ሰፊ ቢሆንም በዚህ ልቋጨው፡፡

ከተወሰኑ ሳምንታት በፊት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ በተሰራው የሕክምና ካምፓስ ውስጥ የሚገኘውን ቤተመጻሕፍት በራስ አበበ አረጋይ ስም ለመሰየም መወሰኑን ይህ ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት የነበሩ ግለሰቦች ነገሩኝ፡፡ ይህም ውሳኔ ራስ አበበ አረጋይን ለማስታወስ በማሰብ የተደረገ በመሆኑ አድናቆት ሊቸረው ይገባል፡፡ በፊት አስታዋሽ አጥተው የነበሩትን የሃገር ባለውለታ ዩኒቨርሲቲው ማስታወሱ የሚደነቅ ቢሆንም የራሱ አሉታዊ ጎኖች አሉት፡፡ይኸውም በከተማው ውስጥ በጀግናው የተሰየመ ቤተመጻሕፍት እያለ ሌላ ተጨማሪ መሰየሙ ግርታን የሚፈጥርና አንባቢያንንና ህብረተሰቡን የሚያሳስት ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ቤተመጻሕፍታችንም ምንም እንኳን በአነስተኛ ቦታ የተወሰነ ቢሆንም የራሱን አሻራ እያስቀመጠና በግል ቤተመጻሕፍት ዘርፍ ያለውን ክፍተት በማሳየት በትንሽ ገንዘብ፣ የሰው ሃይልና በውሱን አቅም ትልቅ ስራ መሰራት እንደሚችል እየሳየ ያለ ነው፡፡ መጻሕፍትን በማሳተምና በማከፋፈልም በመላ ሃገሪቱ የንባብና የዕውቀት ትሩፋት እንዲደርስ እየጣረ ያለ ነው፡፡ በመሆኑም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ይህንን ውሳኔውን እንዲያጤነው ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ከተቻለም ቤተመጻሕፍቱ በሌሎች ታዋቂ ደራሲያን፣ ምሁራንና የአገር ባለውለታዎች (ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ፣ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ወዘተረፈ) እንዲሰየም ሊደረግ ይችላል፡፡ ራስ አበበ አረጋይ በብዙ መልኩ እንዲታወሱ ማደረግ ይቻላል፡፡ ግርታን በማይፈጥር መልኩም እስካሁን የታወሱበትንና የተወሰኑ ፍላጎቶችን እናሳይ፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በደብረ ብርሃን በግል ቤተመጻሕፍት አስታውሰናቸዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ በስማቸው መንገድና ትምህርት ቤት አለ፡፡ እነዋሪ ላይ ሆቴል ተሰይሟል፡፡ የባንክ ቅርንጫፍም አለ፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰየም ፍላጎት እንዳለም ሰምቻለሁ፡፡ ወደፊት ዩኒቨርሲቲያችን ባለው ተጽዕኖና የሥራ ግንኙነት መሠረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በሌሎች ክልሎችም ሆነ በፌደራል ደረጃ ለራስ አበበ አረጋይ ውለታ የሚመጥን ወታደራዊ አካዳሚ ቢሰየም ከእርሳቸው ትክክለኛ ወታደራዊ ጀብዱ ጋር የሚስተካከል ማስታወሻ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ሌሎችም ጀግናውን የሚያስታውሱ ስራዎች ቢሰሩ ለውለታቸው ሲያንስ አንጂ አይበዘባቸውም፡፡

መዘምር ግርማ

የራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት ሥራ አስኪያጅ

ሰኞ የካቲት 22 2013 ..

ደብረብርሃን

እሑድ 25 ኤፕሪል 2021

ዘመዶቼንና የአገሬን ሰዎች ማግኘት የሚፈጥርብኝ የተደበላለቀ ስሜት

 

ዘመዶቼንና የአገሬን ሰዎች ማግኘት የሚፈጥርብኝ የተደበላለቀ ስሜት

11.12.10

ዛሬ ቅዳሜ በለቅሶ ምክንያት ሞጃዎችን ላገኛቸው ችያለሁ፡፡ አንዳንድ ነገርም ስለታሰበኝ ማስታወሻ ያዝኩ፡፡

1.     አደረጃጀታቸው

በሐዘን ጊዜ በአብዛኛው እገኛለሁ፡፡ በደስታ ግን አይቀየሙኝም እያልኩ እቀራለሁ፡፡ ሐዘኑ የወገንን መጎዳት እንደመጋራት ስለሚታየኝ ብዙም አልቀርም፡፡ የቀሩሁባቸውንም ሳገኛቸው ባለመቻል ወይም በሰዓቱ ባለመስማት አለመገኘቴን እናገርና በመጠኑ ለህሊናዬ ይቀለኛል፡፡   

በተገኘሁባቸው አጋጣሚዎች መታዘብ እንደቻልኩት ግን ሞጃዎች ድርጅታቸው ጠንካራ ነው፡፡ ዕድር አላቸው፡፡ ዕድሩ የተሟላ ሲሆን፤ ቁሳቁስ፣ የሠው ኃይል፣ የአመራር ተዋረድ ሥርዓትና አፈጻጸም ክትትል ጭምር አላቸው፡፡

አስገራሚ የሆነ የድንገተኛ ጊዜ አደረጃጀታቸው አሁን በዘመኑ ቴክኖሎጂ ታግዞ በስልክ እየተጠራሩ አንድ ለቅሶ ካለ ከጋውና እስከ አዲስ አበባ ያለ ሰው ለቀብር እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ በፊት ቢሆን መልዕክተኛ ተልኮ ይናገሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በለቅሶ ጊዜ ለለቀስተኛው ምግብ ያቀርባሉ፡፡ በፊት ንፍሮ ይሰጥ እንደነበር ነው የማውቀው፡፡ ህብረተሰቡም የተጎዳውን ለማጽናናትም ሆነ ሐዘኑን ለመጋራት አይቸገርም፡፡ ሙሾ ያወርዳሉ፡፡ ቀብር ያስፈጽማሉ፡፡ ይሰናበታሉ፡፡ ነፍስ ይማር ይላሉ፡፡ 

ለዚህ የድንገተኛ ጊዜ ችግር ሁልጊዜ ዝግጁ መሆናቸውን የምታውቁት አንድን ሰው ሁሉም ለቅሶ ላይ ከሳሲት ድረስ እየመጣ ስታገኙት ነው፡፡ ስራውን በወቅቱ እየጨረሰ በድንገተኛ ሁኔታ ላይ ለመገኘት መቻሉ ያስደንቀዋል፡፡ በግሉ የግብርና፣ የንግድ ወይም ሌላ ስራም ይስራ፣ ይቀጠርም እንደምንም ተቸግሮ ይመጣል፡፡ ይህ የሚያሳየኝ ለማህበራዊ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጥና ነባር ትስስሩንም ከዚህች ተቀያያሪ ዓለም ተጽዕኖ አርቆ እንዳቆየ ነው፡፡ 

 

 

 

2.     ሳትጠይቀን ምነው ጠፋህ?

እንደኔ ያለ ልጃቸውን የሚያገኙት እጅግ አልፎ አልፎ ስለሆነ ሳይሰማቸው አይቀርም፡፡ ደብረብርሃንም እንደሆነ በቀበሌ 09 ተወስኜ የቀረሁ ስለሆንኩ አያገኙኝም፡፡

 

ስራ-ተኮር ሳልሆን አልቀርም፡፡ ስቴፈን ኮቬይ መርህ ተኮር የሚለውን ገና ስላልሆንኩ ስራ ስራዬን ስል ማህበራዊ ጉዳዬን፣ ወዳጅ ዘመዶቼን ስለረሳሁ በልቅሶ ብቻ ላገኛቸው ተገድጃለሁ፡፡

 

አገር ቤት ካሉት ወዳጅ ዘመዶቼ ከስንት አንዴ ስሄድ የሚያገኙኝ ወይ ዘመዶቼ ወይ ጎረቤቶቼ ናቸው፡፡ እዚያ የምቆየውም ግማሽ ቀን ይሆናል፡፡

በነዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች ሳገኛቸው ምነው ሳትጠይቀን ጠፋህ ይሉኛል፡፡ በምንም በምንም አድበስብሼ አልፋለሁ፡፡ በህልፈተ-ህይወታቸው ወይንም በሚጎዱ ጊዜ የምቆጭባቸው ብዙ ትዝታቸው ያሉብኝ ወይም የማስታውሳቸው ሰዎች አሉ፡፡

ከወላጆቹና ዘመዶቹ ጋር አንድ መንደር ኖሮ የሚሞተው ሰው ነው የኛ ዓይነቱ የሚሻለው? ከኛም የባሰ በባዕድ አገር የሚኖሩ አሳዛኝ ፍጥረታት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ኑሮው ቢደላቸው እንኳን ናፍቆቱና ችግሩ አይለቃቸውም፡፡

 

3.     ምን ደረጃ ደረስክ?

ሳድግ እንዳዩኝና እንደሚያውቁኝ ምን ደረጃ እንደደረስኩ ለማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ቤት ሰርቼ እንደሆን፣ ትዳር ይዤ እንደሆን፣ ማዕረግ እንዳለኝ፣ ልጃቸውን አገኘው እንደሆን ወዘተ ይጠይቁኛል፡፡ አንዳንዱ ያለሁበት ሁኔታ ሲያስደስታቸው አንዳንዱ ያስከፋቸዋል፡፡ ይመክሩኛል፡፡ የምስማማባቸው ምክሮች እንዳሉ ሁሉ የማልስማማባቸውም አይጠፉም፡፡ ዓመት ከዓመት የሚመክሩኝና እኔ የማልሻሻልባቸው ነገሮች ሦስት ናቸው፡፡ ለእነሱ እልህ ነው መሰለኝ እኔም አላሻሽል ብያለሁ፡፡ ሞጃዎችን ማናደድ ግን ምን ያደርግልኛል!

 

4.     ቀብሬን አድርገው ባገሬ

እንደ በዓሉ ግርማ የምቀበርበትን አላውቀውም አልላችሁም፡፡ እንደራስ መስፍን ግን ሐውልቴን አላሳንጽም፡፡

ዘመናዊውን ትምህርቴን ከማህበረሰቤ አስተሳሰብ ጋር የማስታርቅበት መንገድ የለኝም፡፡ በአቸቤ ልቦለድ ላይ ያለውን ሚካኤል ኦቢን የሚመስል ስብዕና ያለኝ መሰለኝ፡፡ ቢሆንም

እስከ ቀብሬ ድረስ ግን ብዙ ታሪክ መስራት ይኖርብኛል!

 

የኔልሰን ሩሃሊሃሊሃ ማንዴላን ትልቁን መጽሐፍ - ኤ ሎንግ ዎክ ቱ ፍሪደም - የሚለውን አንብቤዋለሁ፡፡ እዚያ ላይ እንዳየሁት ማንዴላ የትውልድ መንደራቸውን ኩኑን ጥለዋት የሄዱት የስምንት ዓመት ልጅ ሳሉ መሰለኝ፡፡ ዓለም በቴሌቪዥን መስኮት እያየ ያስቀበራቸውም ኩኑ ላይ ነው፡፡ በተወለዱበት የመቀበር ዕድል ለማናችንም መነፈግ የሌለበት ይመስለኛል፡፡ ከኩኑ እስከ ኩኑ - ከሳሲት እስከ ሳሲት፡፡  

 

 

5.     ስሜታቸው

ከእነሱ አነስ ስለምል ወንዱም ሴቱም አንቺ የሚሉኝ ሰዓት አለ፡፡ የሚወዱኝና የሚያከብሩኝ እንዳሉ ሀሉ የሚጠሉኝም አይጠፉም፡፡ በየአጋጣሚው ለፍቅሩም፣ ለጥላቻውም፣ ለአክብሮቱም ለንቀቱም ጊዜ ስለነበረው፡፡

 

6.     ትዝታቸው

ብዙዎቹ ማለት ይቻላል ሳገኛቸው ከኔ ጋር ያላቸውን ብዙ ትዝታ ይነግሩኛል፡፡ አንዱ ልጅ ከገጠር ሳሲት መጥቶ ከኔ ጋር እንደመጣላት እንዳለና ‹‹አፍንጫህን ነው የምልህ›› እንዳልኩት፡፡ ከኔ በቁመቱና በአቅሙ ከፍ ቢልም ‹‹ትመታኝ ይሆን እንዴ ይቺ ልጅ›› ብሎ ሰግቶ ሳይጣላኝ እንደሄደ እንዳወጋቸው ዛሬ ያገኘኋቸው ነገሩኝ፡፡ እኔ ግን ረስቼዋለሁ፡፡ አስቆኛል፡፡ እንዲያውም ለጠብ የሚደፍሩት እኔን እንደሆነ አውቃለሁ፡፡

በተያያዘ ዜና አንድ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚባል ጥቁር ልጅ ሳሲት ከተማ ይኖር ነበር፡፡ ታዲያ የፈላ ተማሪዎች በሳሲት ጉድኝት ለስፖርት ውድድር መጥተው አሸንፈው ኖሯል፡፡ ዛሬ ከነሱ አንዱ ሲነግረኝ ማለት ነው፡፡ ትምህርት ቤት ያለውን የከፍታ ዝላይ ምናምን ውድድር ጨርሰው ወደ መስክ ለሩጫ ሲሄዱ በሆታ ነበር፡፡ ‹‹ፈላ ጉድ አፈላ›› እያሉ፡፡ ያ ልጅ ስለ ሳሲት መሸነፍ አዝኖ ይሁን ወይም ለጠብ ፈልጓቸው አነስ ያለውን ልጅ እየተከተለ ይተናኮላል፡፡ አነስ ያለውም ልጅ ሊጣላው ይጋበዛል፡፡ ጠጋ ሲለው ያ ትንሽ የመሰለው የሳሲት ልጅ ደረቱ ላይ ጸጉር ያወጣ ጎረምሳ መሆኑን ያያል፡፡ ጠቡን ትቶ ሸሸት የሚለውን ትንሽ ልጅ ጎረምሳው መተናኮሉን ቀጥሏል፡፡ በመጨረሻ ትልልቆቹ ጣልቃ ገብተው አስጣሉኝ አለን፡፡ ሁሉም ለኔ ጋር ትውስታ ካላቸው እያንዳንዱን ጠባሴ፣ ደብረብርሃን በሚገኘው ራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት ባገኛቸውና ባናግራቸው ጥሩ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ያው እኔ ለቅሶ ከመጣብኝ ቤቴ ባዶ ስለሆነች ራስ አበበ ቤተመጻሕፍት ለቀስተኛ እንደምንቀበል ከጓደኞቼ ጋር ስለምንቀልድ እውነትም ይሆን ይሆናል፡፡

 

7.     ምን አደረኩላቸው

ይህ ስሜት የሚሰማን ልንኖር እንችላለን፡፡ ተሰምቶን የሆነ ነገር እናድርግ ብንል በሆነ መልኩ ልንሞክርና ልንፍጨረጨር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ግን ዝምተኞችና አቅም ያጣን ነን፡፡ አጠቃላዩ ነገር ከላይ እንዲሻሻል በማሰብ ከፖለቲካ እስከ ውትድርና በሃገር ደረጃ የሚፍጨረጨሩ ሞጃዎች ይኖራሉ፡፡ ሁሉም በጊዜ ሂደት ውጤቱ የሚታይ ይሆናል፡፡ የህብረተሰቡም ለውጥ እንደዚያው፡፡

ሞጃዎች የሚፈልጉት ግን ምንም እንድናደርግላቸው አይደለም፡፡ ልጃችን እዚህ ደረጃ ደረሰልን ለማለት እንጂ፡፡ ይህም የኛን ጥሩ በመውደድ ነው፡፡ ይህ የአብዛኛው ሁኔታ ነው፡፡

አንዳንዴ የሚከሰቱና መታረም ያለባቸው ነገሮች አሉ፡-

‹‹አንተ››

‹‹ወይ››

‹‹እንተናን ታቀዋለህ››

‹‹የቱን››

‹‹ያን አብሮን የተማረውን››

‹‹አዎ››

‹‹እንትን አገር በእንትንነት እየሰራ ብዙ ገንዘብ ያገኛል››

‹‹ምናባቱ አሁን እሱ አይጥ››

‹‹ምን አረገህ››

‹‹ተወው እባክህ››

 

ይህን አይነት ወግ አሳልፌያለሁ፡፡ ለዚች አጭር እድሜ እስኪ እንዋደድ፡፡ ደግ ደጉን እንመኝ፡፡ የቤተሰብ ቂም፣ የግል ፉክክር፣ መጥፎ ስሜት የትም አያደርሰንም፡፡ ራሳችንን ይጎዳናል፡፡

 

ብዙ ላደረገልን ህዝብ ምንም ውለታ ስላልከፈልን እስኪ በዚህ ዙሪያ እናስብ፡፡

 

8.     ለቅሷቸው

በደስታ ጠርታችሁኝ አልመጣሁም፡፡ እስኪ ወደፊት ጥሩኝ፡፡ ደጋግማችሁ ጥሩኝ፡፡ ልጅ ልካችሁ አስወስዱኝና ደስታንም ልላመደው፡፡ በሐዘን ብቻ ሳገኛችሁ ዘመዶቼ ሁልቀን ተጎዱብኝ እያልኩ ማሰቡ ይግዳኛል፡፡ እናንተም እኔን በለቅሶ ላይ ብቻ ካለ ትዝታ ጋር ማስተሳሰርን ትተዉ ይሆናል፡፡

 

9.     ሞጃ በፖለቲካ

ሞጃ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ፖለቲካ የገባት ነች፡፡

አሁን ያለው ተስፋ ሰጪም ተስፋ አስቆራጭም ሁኔታ ያሳሰባችሁ ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ ምልከታችሁ ገብቶኛል፡፡

ከኢትዮጵያ ህዝብ የጦርነት ልምድ ያለው ህዝብ እንዳለ ነግራችሁኛል፡፡

ተዘዋውራችሁ ያያችኋት ለምለም አገራችንን የማስተዳደር አቅምና ፍቅር እንዳጣን አጫውታችሁኛል፡፡

ከአገራችን ህብረተሰቦች በአገዳደል ሳይቀር አረመኔነት የሚታይባቸው እንዳሉ ተማምነናል፡፡

 

10.  ማጠቃለያ

እያንዳንዳችሁ በማህበራዊ ጥሪ ላይ ስትገኙ የምትመጡት ቤታችሁን ዘግታችሁ፣ ስራችሁን አቋርጣችሁና ልጆቻችሁን በትናችሁ ስለሆነ ያስመሰግናችኋል፡፡

ከሃያ ዓመት በኋላ ስለተያየንና ደግመን ስለማንተያይ የምንነፋፈቅና ተራርቀን የምንቀር ሰዎች መኖራችን ይገርመኛል፡፡

የደብረ ብርሃን ቀበሌ 08 የሚገርም ሰፈር ነው፡፡ ነዋሪው በብዛት ሁሉም የሞጃ ተወላጅ ነው፡፡ አንድ ላይ የተሰባሰብንበት እውነተኛ ምክንያት አልገባኝም፡፡ ማህበራዊ ይሆን? የጸጥታ? የንግድ?

ያለን ሐብት እህል ብቻ ነው እንዴ?

በተሻለ መንገድ እንዴት እንገናኝ?

የልብ ህመም ያመማት አንድ እህታችን ወደ ህንድ አገር ሄደሽ ካልታከምሽ አትድኚም ስለተባለች እንዴት እናሳክማት?

የቤተሰቡ አባል የሚሞትበትን ሰው ከእድር ውጪ የምናግዝበት አደረጃጀት መፍጠር እንችል ይሆን?

መልካሙን ሁሉ እመኝላችኋለሁ፡፡ እወዳችኋለሁ፡፡

ዓሣ እና ስጦታ

A Fish and a Gift (taken from ASb)

ዓሣ እና ስጦታ

Yusuf waits in anticipation for his father to return from fishing. He has promised to bring Yusuf a gift today.

ዩሱፍ አባቱ ከዓሣ ማስገር እስኪመለሱ ድረስ በጉጉት ይጠባበቃል፡፡ አባትዬው ለዩሱፍ ዛሬ ስጦታ እንደሚያመጡለት ቃል ገብተውለታል፡፡

One special Friday Yusuf's father gets dressed before a flicker of light brightens the sky. He pulls on his heavy weather-proof jacket and the green woolen cap that covers his ears. He waves his boy goodbye. Yusuf's eyes brighten when Papa says, "Today is the day I will catch a fish and bring a gift home for you."

በአንዲት ልዩ አርብ ዕለት አንዲት የብርሃን ፍንጣቂ ሰማዩን ከማብራቷ በፊት የዩሱፍ አባት ልብሶቻቸውን ለባበሱ፡፡ ከባድ የዝናብ ልብሳቸውን ለበሱ፤ እስከ ጆሯቸው ድረስ የሚሸፍነውን አረንጓዴ የሱፍ ኮፍያቸውን አደረጉ፡፡ ለልጃቸውም በእጃቸው የስንብት ምልክት አሳዩት፡፡ አባትዬው ለዩሱፍ ‹‹ዛሬ ዓሣ የማጠምድበት ቀን ስለሆነ ስጦታ አመጣልሃለሁ›› ሲሉት  ዓይኖቹ በብርሃን ተሞሉ፡፡   

A fish and a gift? Oh, what will it be? Papa cycles down to Muizenberg Beach. Squeak squeak go the wheels all the way to Surfer's Corner. Gulls circle the sky. "Whaaat? Whaaat? Whaaat?" they cry. "What will you bring back for Yusuf?" Papa rings his bell. "Wait and see what it will be!"

ዓሣ እና ስጦታ? ኦ፣ ምን ሊሆን ይችላል? አባትዬው ወደ ሙዘንበርግ የወንዝ ዳርቻ በብስክሌት ወረዱ፡፡ የብስክሌቷም ሰንሰለት እስከ ጀልባ ቀዛፊዎቹ ስፍራ እስኪደርሱ ድረስ ሲጥጥ ሲጥጥ ሲል ቆየ፡፡ ባለ ረጃጅም ክንፍ ወፎች ሰማዩን ከበውታል፡፡ ‹‹ምን? ምን? ምን?›› በማለትም ይጮሁ ጀመር፡፡ ‹‹ለዩሱፍ ይዘህለት የምትሄደው ምንድነው?››   እያለ አባባ ደወሉን ደወለ፡፡ ‹‹ጠብቁና ምን እንደሆነ እዩ!››

The fishermen watch the sun rise. They check their nets. They check their oars. They listen to the wind. They drag their boats down to the water. Yusuf's grandfather, Oupa Salie was a treknet fisherman. Before him his father, Oupagrootjie Ridwaan, knew the sea too.

ዓሣ አጥማጆቹ ፀሐይዋ ስትወጣ አዩዋት፡፡ የዓሣ ማጥመጃ መረቦቻቸውን አወጡ፡፡ መቅዘፊያዎቻውን አነሱ፡፡ ነፋሱንም አዳመጡ፡፡ ጀልባዎቻቸውንም ወደ ዉኃው ጎተቱ፡፡ ኡፓ ሳሊ የተባሉት የዩሱፍ አያት፣ ዓሣ አጥማጅ ነበሩ፡፡ ከእርሳቸው በፊትም አባታቸው ኡፓግሮትጄ ሪድዋን ባህሩን በሚገባ ያውቁት ነበር፡፡

The boat rides into the waves. Papa's arms stretch to the oar. His leg brace s against the side. His neck strain , his back muscles ripple. Papa sings as he works: "Drop and swish. Find a fish. Pull and plop. Don't you stop."

ጀልባዋ ነፋሱን ተከትላ ትቀዝፍ ጀመር፡፡ የአባባ ክንዶች አግድም መቅዘፊያውን ይዘዋል፡፡ እግሮቻቸውም ወደ ጎን ተዘርግተዋል፡፡ አንገታቸው  ቀጥ ብሏል፡፡ ጀርባቸው ይወዛወዛል፡፡ አባባ እየሰሩ ይዘፍናሉ፡፡ ‹‹ውደቅ አንሣ፤ ፈልግ ዓሣ፡፡ ሳበው ዛቀው፤ እንዳትለቀው፡፡›› 

All day long Yusuf looks at the sky. It is bright and clear and windless. A fish and a gift! What will Papa bring home from the sea? Sometimes he brings a beautiful shell. Sometimes he brings a jewel green bottle rinse d by the waves.

ዩሱፍ ቀኑን ሙሉ ሰማይ ሰማዩን ሲያይ ዋለ፡፡ ብሩህ፣ ንፁህና ነፋስ አልባ ሰማይ ነው፡፡ ዓሣና ስጦታ! አባባ ከባህሩ ምን ይሆን የሚያመጣልኝ?  አንዳንዴ ቆንጆ ዛጎል ያመጣልኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ማዕበል ያንሳፈው አረንጓዴ የጠርሙስ ጌጥ ያመጣል፡፡

Some days Yusuf's father brings a story. Like the time they found sea turtles on the sand, hundreds washed up in a storm. "Whaaat? Whaaat? Whaaat?" cried the gulls. "What will you do to help the turtles?"  Papa said, "We saved those turtles, I tell you straight. We sent them back to the ocean, every last one."

አንዳንዴ የዩሱፍ አባት ተረት ያመጣሉ፡፡ አሸዋው ላይ ማዕበል ያመጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የወንዝ ዔሊዎች ያገኙ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ፡፡  ‹‹ምን? ምን? ምን?›› በማለት ባለ ረጃጅም ክንፎቹ ወፎች ጮሁ፡፡ ‹‹ዔሊዎቹን እንዴት ታግዛቸዋህ?›› አባባ ‹‹እነዚያን ዔሊዎች አድነናቸዋል አልኩህ፡፡ መልሰን ወደ ውቅያኖሱ አስገባናቸው፡፡ አንድም ሳይቀር፡፡›› 

Always Papa brings a song. He sings the song while he pulls the oars. He sings the song while he pulls the nets. He sings the song as he winds the ropes. He sings the song as he cycles home. "Drop and swish. Find a fish. Pull and plop. Don't you stop."

ሁልጊዜ አባባ ዘፈን ያመጣል፡፡ መቅዘፊያዎቹን ይዞ ሲቀዝፍ ይዘፍናል፡፡ መረቦቹን ሲስብ ይዘፍናል፡፡ ገመዶቹን ሲጠቀልል ይዘፍነዋል፡፡ ወደ ቤት በብስክሌት ሲመጣ ይዘፍናል፡፡ ‹‹ውደቅ አንሣ፤ ፈልግ ዓሣ፡፡ ሳበው ዛቀው፤ እንዳትለቀው፡፡›› 

Ouma Safiya wants a nice fat yellowtail for her supper. "But we'll be lucky if they catch even a tiny crab. More likely it will be fish tail Friday. There's not so many fish left in the sea," says Ouma shaking her head.  Yusuf holds Ouma's hand. They cross the road at the bathing cabin s."Whaaat? Whaaat? Whaaat?" cry the gulls perched on the bright rooftops. "What is for supper?"

ኡማ ሳፊያ ለራት ቆንጆ ወፍራም ባለቢጫ ጭራ ዓሣ መብላት ትፈልጋለች፡፡ ‹‹ግን ትንሽዬም ዓሣ እንኳን ካጠመዱ ደስተኞች እንሆናለን፡፡ ዛሬ የዓሣ ጭራ የሚበላበት አርብ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወንዙ ውስጥ ብዙም ዓሣ የለም፤ አልቋል፡፡›› አለች ኡማ ራሷን እየነቀነቀች፡፡ ዩሱፍ የኡማን እጅ ያዘ፡፡ መታጠቢያ ቤቱ ጋ ያለውን መንገድ አቋረጡ፡፡ ‹‹ምን? ምን? ምን?›› በማለት ባለ ረጃጅም ክንፎቹ ወፎች በአንጸባራቂዎቹ ጣራዎች ላይ ሆነው ጮሁ፡፡  ‹‹ለራት የምትበሉት ምንድነው?››

Last year the fishermen fought with the surfers. Angry fists and shouting words. "Whaaat? Whaaat? Whaaat?" cried the gulls. "There's enough sea for everybody," said Yusuf's father. He showed them the fishing license that had been Oupa Salie's. "Waves for all. Water for free."

ባለፈው ዓመት ዓሣ አጥማጆቹ ከቀዛፊዎቹ ጋር ተጣልተው ነበር፡፡ እጃቸውን እየሰነዘሩ ሲጯጯሁ ‹‹ምን? ምን? ምን?›› በማለት ባለ ረጃጅም ክንፎቹ ወፎች ጮሁባቸው፡፡ የዩሱፍ አባትም ‹‹ለሁላችሁም የሚበቃ ወንዝ አለ እኮ›› አሉ ፡፡ የኡፓ ሳሊን ዓሣ የማስገሪያ ፈቃድ አሳዩዋቸው፡፡ ‹‹ሞገዶ ለሁሉም፡፡ ዉኃ በነጻ›› ይላል፡፡

Ouma Safiya watches through her binoculars, her fingers curled in curiosity. The shark siren sounds. Swimmers run back to the sand and grab their towels. Surfers rush to the shore, carrying their boards under their arms. Under the showers they strip off their wetsuits. "Whaaat? Whaaat? Whaaat?" cry the gulls. "What will Yusuf's father bring from the ocean?"

ኡማ ሳፊያ በመነጽሯ ታያለች፤ እጆቿም በጉጉት መነጽሩን ይዘዋል፡፡ የዓሣነባሪን መምጣት የሚያስጠነቅቀው ድምጽ ጮኸ፡፡ ዋናተኞች ወደ አሸዋው ተመልሰው ፎጣዎቻቸውን ያዙ፡፡ ቀዛፊዎች መቅዘፊያቸውን በክርኖቻቸው ስር ይዘው ወደ ዳርቻ ወጡ፡፡ በዝናብ እርጥብ ልብሶቻቸውን አወለቁ፡፡ ‹‹ምን? ምን? ምን?›› በማለት ባለ ረጃጅም ክንፎቹ ወፎች ጮሁ፡፡ ‹‹የዩሱፍ አባት ከባህሩ ምን ይዞ ይሄዳል?››

Yusuf's father and uncle and cousins heave and pull. A little shark has been caught. It twists and thrash es in the waves. Yusuf's father untangle s the nets, singing to the shark: "Drop and swish. Find a fish. Pull and plop. Don't you stop."  When the shark at last is free it streak s back into the waves, leaving only one fat yellowtail in the net. Ouma Safiya will be pleased.

የዩሱፍ አባት፣ አጎቶችና የአጎቶች ልጆች እያቃሰቱ ይስባሉ፡፡ ትንሽ ዓሣነባሪ ተይዟል፡፡ ሞገዱ ሳያግደው ይታገላል፡፡ የዩሱፍ አባት ለዓሣነባሪው እየዘፈኑ መረቦቹን ይፈታታሉ፡፡  ‹‹ውደቅ አንሣ፤ ፈልግ ዓሣ፡፡ ሳበው ዛቀው፤ እንዳትለቀው፡፡››  በመጨረሻም ዓሣነባሪው  ምንም እንዳልያዘው አውቆ ወደ ሞገዱ ገባ፡፡ መረቡም ላይ አንድ ትልቅ ባለቢጫ ጭራ ዓሣ ብቻ ቀረ፡፡ ኡማ ሳፊያ ትደሰታለች፡፡

The men pull the boat in and coil up the cables. A hard white triangle catches Papa's finger. "Whaaat? Whaaat? Whaaat?" cry the gulls. "What did you bring back for Yusuf?" As the sun goes down, Papa answers the gulls. "A lucky shark tooth for my boy." At home Yusuf holds his gift up to the stars.

ሰዎቹ ጀልባዋን ስበው ገመዶቹን ጠቀለሉ፡፡ የአባባን ጣት አንድ ነጭ ጠጣር ሦስት ጎን ያዛቸው፡፡ ‹‹ምን? ምን? ምን?›› በማለት ባለ ረጃጅም ክንፎቹ ወፎች ጮሁ፡፡ ‹‹ለዩሱፍ ምን አመጣህለት?›› ፀሐይዋ ስትጠልቅ አባባ ለባለ ረጃጅም ክንፎቹ ወፎች መለሱላቸው፡፡ ‹‹ለልጄ የዓሣነባሪ ጥርስ፡፡›› እቤት ሲደርሱ ዩሱፍ ስጦታውን ወደ ኮከቦቹ ከፍ አድርጎ ያዘ፡፡ 

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...