ቅዳሜ 11 ፌብሩዋሪ 2017

Photos of my morning walk in Debre Birhan, 2017





















ሕንድ የተማረ ወዳጄ ከነገረኝ ላጋራችሁ።


1. ሕብረተሰቡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በጥቅም እንዲተሳሰር ተደርጓል። ለምሳሌ ከዩኒቨርሲቲው ውጪ መጥተው ኢንተርኔት በክፍያ ያስገባሉ፤ ልብስ ይሸጣሉ።
2. ብዙው ሠው እንግሊዝኛ ይችላል። የማንበብ ልምዱም ከፍተኛ ነው። ዘበኞች ዕለታዊ ጋዜጣ ሲያነቡ ይስተዋላሉ።
3.እያንዳንዱ ልማት ኑሮህ ላይ ለውጥ ሲያመጣ ታየዋለህ።
4. ኑሮ እጅግ ርካሽ ነው።
5. ሙቀቱ በብዛት አርባ ቤት ነው።
6. ውበት ከወገብ በላይ ነው።
7. በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ሰር ነው።
8. ኃይማኖት መጠየቅ፣ በኃይማኖት መጥቀም የተለመደ ነው። በየቢሮው የተቀረፀ ጣኦት አላቸው። በሬና ላም እንደ ፈጣሪ ስለሚታዩ ህገመንግሥቱም ጥበቃ ያደርግላቸዋል። አይታረዱም!
9. ሕዝቡ በአራት ደረጃዎች ይመደባል። ይህ አሰራር ኢፍትሃዊነቱ በየዘርፉ ይታያል።
10. ያላገባሃትን ሴት . . . ጨዋ አገር ነው። ጥሎሽ የምትጥለው ሴት ነች። ዱሮ ሴት ከተወለደች ትገደል ነበር። ጥሎሹን ፍራቻ! እንግሊዞች አስተዋቸው።
11. መብት በሽ ነው። ክልሎች ብዙ ጥያቄ በረሃብ አድማ ያስመልሳሉ።
12. ትምህርቱ ጥራት አለው።
13. በሕንድ በትምህርት ጎበዞች ሴቶች ናቸው።
14. አነስተኛ የኪስ ገንዘብ የሚሰጣቸው የውጪ አገር ተማሪዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱም ደምወዛቸው ከሁሉም ያነሰ ነው። ሱዳን አገር በወለደው ልጅ ብዛት ደምወዝ ይከፈለዋል።
15. ሲበዛ ታማኞች ናቸው ሕንዶች።
እዚያ የተማራችሁ ወይም በመማር ላይ ያላችሁ ተጨማሪ ሐሳብ ብትነግሩኝ ፅሑፉን ማዳበር እችላለሁ።
ምን አስገረማችሁ አንባቢያን?

Mezemir Girma

ከታዋቂ አበሾች ሕንድ የተማሩ ፕሮፌሰር መስፍንን አውቃለሁ ። ብዙ ሕንዶች እኛ አገር አስተምረዋል ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ሸርማ ሁለት ኮርስ ሰጥቶኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ 50 ዓመት በጥራትና በሠዓት አክባሪነት አስተምሩዋል።
Edited · Like · Reply · Edit · Yesterday at 10:33pm

Ze Ethiopia Hageri

ሲተዋወቁህ/ሽ የመጀመሪያው ጥያቄያቸው ከየት ሃገር መጣህ እና አግብተሃል/ሻል ነው። ከጋብቻ በፊት ምንም አይነት የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነው፤ በተለይ ለሴት ልጅ። በማንኛውም የግልም ይሁን የመንግስት አገልግሎት መስጫ ቦታ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዜጎቻቸው ነው። ትራንስፓርት ወይም መንገድ ላይ ትህትና እዛውንት ማክበር ብሎ ወንበርን ለቆ ማስቀመጥ ታችኛው ካስት እንደሆነ ማሳያ ነው። የተቀደደ ገንዘብ የሚቀበል ሰው የለም። ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የሀይማኖት እንቅስቃሴ ያለገድብ ማስኬድ ይቻላል። ወ.ዘ.ተ...እጅግ ብዙ ነው እዚህ ላይ ላቁም። ግን እንግሊዝኛ እንኳን በአብዛኛው አይችሉም የተሳሳተ እንዳይሆን መረጃህ መዜ!
Edited · Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Solomon Genet

Fetena wustim hone class wust shint kemetabik fekad meteyek yelem tensto mewutat bicha new( tamagn silehonu). tiyakie lemeteyekm hone lememeles ye astemariwun fekad meteyek yelem, directly memeles bicha new.
Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Barok Seyoum

"ውበት ከወገብ በላይ ነው" ለካ ለዚ ነው ፊልም ላይ ብዙ ጊዜ ፊታቸውን ፊታቸውን የሚያሳየን ከስር ቁምጣ እየለበሱ ነው እንዴ የሚቀረፁት
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · 11 hours ago

Yeshalem Gezahegn

for no. 14, nepals , butans ,maldives were getting pocket money less than ethio i think.
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · 3 hours ago

Mezemir Girma

Afterthought: Indians are festival people. There is a festival everyday.
Like · Reply · Edit · Just now

ዓርብ 10 ፌብሩዋሪ 2017

African Storybook Debre Birhan

Stories written by Debre Birhanis to be published: ቢኒያም አስፋው (The Shepherd and His Best Friend)፣ እዮቢ ቅጣው (Abel and his Sister’s Doll)፣ ቤተልሔም ዋልተንጉስ (Petros and His Dog) ፎዚያ መሐመድ (Amina and Her Animals) በአፍሪካ የተረት መጻሕፍት መርሃ-ግብር ለልጆች ተስማሚና ምርጥ ተብለው ከደብረ ብርሃን የተመረጡ ታሪኮች ስለሆኑ እንደሚታተሙ መረጃ ደርሶኛል፡፡ ይህ ደብረብርሃን ላይ ያካሄድነው ሁለተኛ የተረት መጻፍ ውድድር ውጤት ነው፡፡ የመጀመሪያውን ውድድር ነገር ተነጋግረን እንወስናለን፡፡ ከቢኒያም ውጪ ሦስቱ ያሸነፉት ተረቶች የልጆች በተለይም የሴቶች ልጆች መሆናቸው በጣም ያኮራል፡፡ እናመሰግናለን!

ረቡዕ 8 ፌብሩዋሪ 2017

ከፌስቡካችን



December 30, 2016
በደብረብርሃን ከተማ መሐመድ አብዱልሰመድ መልቲፕሌክስ በሚገኘው ራስ አበበ ቤተመፃሕፍት በመጪው እሁድ ታህሳስ 23 2009 ከቀኑ ሠዓት ጀምሮ የፈረንጆችን አዲስ ዓመት ስለምናከብር በዝግጅታችን ላይ እንዲገኙ ጋብዘነዎታል። በቀደም ክሪስማስን ስንዘክር ቅር የተሰኘውም ልጅ መምጣት የሚከለክለው የለም። የመፅሐፍ ሥጦታ ለመሰጣጠት የምትፈልጉ ይዛችሁ ብትመጡ በዕጣ እናቀያይራችኋለን። New Year Festivities at Ras Abebe Libraries, Debre Birhan
የፈረንጅ አዲስ አመት ለኛ ምናችን ነው?
Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
የፈረንጆችን አዲስ ዓመት ለማክበር ??????????????????????????? በጣም ይገርማል
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
እኛ የዓለም ዜጎች ነን።
Like · Reply · Edit · Dec 31, 2016
world Of Citizen Is drived from Davos Man. The Collectin Of rich people in the eorld bihaned the idea robing poor nations
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
in the world
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
አረ ተዉ አታስደፍሩን እንጂ። የኛን አዲስ አመት እነሱ ትዝ ይላቸዋል እንዴ? ይልቅ ልደታ ማርያምን ዘክሩ።
Unlike · 3 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
ይህ ትክክል ነው ብየ አላምንም ለመሆኑ የኛን አዲስ አመት በዚህ መልክ አክብራችኋል?
Unlike · 3 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
ችግር የለውም። ከዓለም ተነጥለን የምንኖር አይመስለኝም። የተወሰነ አገር ነው ደግሞ በኛ አቆጣጠር የሚጠቀመው። እስከ መቼ በጁሊያን ካሌንደር እንቀጥል ይሆን? ሀሳቤን የሚረዳው የተወሰነ ሰው ነው።
Like · 1 · Reply · Edit · Dec 31, 2016
ይቅርታ እኔም አልስማማም የራሳችን የምንኮራበት አቆጣጠር አለን... ባይሆን ገና በማስመልከት ስጦታ መስጣጠት ቢሆን ደስ ይላል
Like · 1 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
That is so lame that we have two Xmas, Two new year & Two Easter !!
Unlike · 1 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
ከፈረንጅ የምንጠቀመው አለ፤ የምንጎዳበት አለ።
Like · Reply · Edit · Dec 31, 2016
Ferenjphobia will take us no where. Technology, deplomacy, money, everything comes from ferenj. እንኳን ፈረንጆችን እርስ በእርሳችን አንዋደድ!
Like · Reply · Edit · Dec 31, 2016
new year? who cares, totally non sense for us.
Unlike · 2 · Reply · Delete · Report · Dec 31, 2016
ይሔ አያገባንም !!!
Like · Reply · Delete · Report · Jan 1

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...