ረቡዕ 15 ኖቬምበር 2017

የአንድ ገጽ የመጻሕፍት ማጠቃለያዎቼ My One Page Book Summaries - ሕዳር 7፣ 2010





የመጽሐፉ ሽፋን





ርዕስ - በግል ሕይወቴ ከደረሰውና ካጋጠመኝ፣ አንዳፍታ ላውጋቸሁ፤ ደራሲ - ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ ዘውግ - የሕይወት ታሪክ፤ የገጽ      ብዛት - 327 ፤ ዋጋ -  65.80 ፤  የታተመበት ዘመን - 2000 ዓ.ም.
አዛውንቱ የቋንቋ ሊቅ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የሕይወት ታሪካቸውን መታሰቢያ ያደረጉላቸውና በቅኔም ያመሰገኗቸው እናትና አባታቸውን ነው፡፡ በልጅነታቸው አገሪቱ በጣሊያን ተወረረች፡፡ ቤተሰብ ተለያይቷል፡፡ በዘመድ ቤት ለመጠጋት፣ ተገን ፍለጋ ለመንከራተትና ለመጎዳት ግድ ሆነባቸው፡፡ በመከያው ከምሁሩና ህመምተኛው አባታቸው ጋር ጠበል ፍለጋ ሲዘዋወሩ በአብያተክርስቲያናት ለመጠለልና ትምህርት ለመቅሰምም በቁ፡፡ ግዕዝን በጥልቀት ለመማር የቻሉት ጌታቸው፤ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትን ተቀላቅለው ዕውቀታቸውን ዘመነኛ ቅርጽ ለማስያዝ ቻሉ፡፡
በዚሁም ዘርፍ ጸንተው ወደ ግብጽ በማቅናት የመካከለኛው ምሥራቅንና የኦርቶዶክሳውያንን ቋንቋዎች፣ ፖለቲካ፣ ነገረ-መለኮትና ታሪክ ለማጥናት ቻሉ፡፡ በካይሮው የአሜሪካ ዩነቨርሲቲም ዓለማዊ ትምህርት በማታው መርሃ-ግብር ተምረው ዲግሪ ያዙ፡፡ ወደ ጀርመን ሄደው በከፍተኛ ትምርታቸው ገፉበት፡፡ ተጨማሪ ቋንቋዎችንና ዕውቀቶችን ቀሰሙ፡፡ ከግብጽ እስከ ጀርመን ተምረው ዶክትሬታቸውን እስኪይዙ በአጣቃላይ 11 ዓመታትን ወስዶባቸዋል፡፡ አረብኛን፣ እብራይስጥን፣ ቅብጥን፣ ጀርመንኛንና ሌሎችንም ቋንቋዎች መቻላቸው የዕውቀትን ጥግ እንዲመረምሩ ዕድሉን የከፈተላቸውና አንድ ሰው ይማረዋል ተብሎ የማይታሰብ ትምህርት የተማሩ ሰው ናቸው፡፡
ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጠሩ፡፡ እዚያም ሳሉ ለሃገሪቱ ጠቃሚ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ ካይሮ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚሰሩት አምባሳደር መለስ አስገዶም የሚደገፉ የኢትዮጵን አንድነት የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች በተደጋጋሚ ለሚያሳትሙት የአረብኛ መጽሔት በምስጢር ትርጉም ሰርተው ምላሽ እንዲሰጠው ማድረጋቸው አንድ አብነት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረው በሚሰሩበት ወቅትም አማርኛን በእንግሊዝኛ የማስተማርን ስራ አስቁመዋል፡፡ በአማርኛ አካዳሚ ውስጥም ሰርተዋል፡፡ ከሞላ ጎደል በመላ ሐገሪቱ ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና ጽሑፎች በማይክሮፊልም እንዲነሱ በተደረገው ጥረት ተሳትፎ አድርገውም ነበር፡፡ በዓለምአቀፍ የአብያተ-ክርስቲያናት ማህበራት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ወክለዋል፡፡ በእናት አገራቸው ትዳራቸውን ፈጽመውና ቤታቸውን ሰርተው የወደፊቱን ሕይወታቸውን በማስተካከል ላይ ሳሉ ደርግ ይመጣና አንድ ኮሚቲ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ በዚያም ውስጥ የሐሳብ አለመጣጣም ይመጣና ወደቤታቸው ወታደሮች ተልከው የጥይት በረዶ ያዘንቡባቸዋል፡፡ አንዷ ጥይትም ጀርባቸውን ትመታቸዋለች፡፡ በአገር ውስጥ ህክምና ስላልዳኑ ወደ እንግሊዝ አገር ሄደው ታክመው መለስተኛ የጤና መሻሻል አገኙ፡፡ ከዚያም ለስራ ወደ አሜሪካም አቀኑ፡፡ አሁን በዊልቸር የሚሄዱት ፕሮፌሰሩ በአሜሪካኑ የቅዱስ ዮሐንስ ዩኒቨርሲቲ ከየገዳማቱ በማይክሮፊልም ለተቀዱት መጻሕፍት ካታሎግ በመስራትና በነዚህ ጥንታዊያን ሰነዶች ላይ ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ እኝህ አንድ ሰው ባገኙት የካበተ ትምህርት በመጠቀም ሰነዶቹን እያጠኑ ለጥቅም ያውላሉ፡፡ አብዛኛውን ምርምራቸውን በጥናታዊ መጽሔቶች ለባለሙያዎች የሚያቀርቡ ቢሆንም ለማናቸውም አንባቢ በሚገባ አካኋን ያቀረቧቸው መጸሕፍትም አሏቸው፡፡ የሚከተሉት ናቸው፡-
-         ባሕረ- ሃሳብ የዘመን ቆጠራ ቅርሳችን ከታሪክ ማስታወሻ ጋር
-         ደቂቀ-አስጢፋኖስ፣ በህግ አምላክ
-         ግዕዝ በቀላሉ ከናሙና ድርሰቶቹ ጋር
-         የአባ ባሕርይ ድርሰቶች ኦሮሞዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋራ
የጥንታዊውንና የመካከለኛውን ዘመን ዓለማዊና መንፈሳዊ ታሪካችንን በጥልቀት እያጠኑ ያሉትን የእኝህን ሊቅ የሕይወት ታሪክ እንድታነቡና እዚህ ያልጠቀስኳቸውን ጉዳዮች እንድትመረምሩ ስጋብዛችሁ በታላቅ ትህትና ነው፡፡



የወደድኩት ገጽ




2 አስተያየቶች:

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...