ማክሰኞ 7 ኖቬምበር 2017

ማስታወቂያ




ደብረብርሃን የንባብ ከተማ!
ቀድመው ሊመዘገቡበት የሚገባ ትምህርታዊና ጥበባዊ ዝግጅት በራስ አበበ አረጋይ ቤተ-መጻሕፍት፣
የዚህ ሣምንት የዕለተ-ሐሙስ (30/2/10፣ 12፡00 – 2፡00) ዝግጅታችን ሃያ አምስት ሰዎችን ብቻ ስለሚያስተናግድ፤
በርካታ ሰዎች የመሳተፍ ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚችል በመገመቱ፤
በምንነጋገርበት ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ወደፊት ሰርተው ከየተሻለ ጥቅም ሊያመጡ የሚችሉትን ሰዎች ለማሰባሰብ በማሰብ፤
ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡ የምዝገባው ሁኔታ፣
በቤተመጻሕፍቱ በስራ ሰዓት በመገኘት፣
በስልካችን (0970381070) የጽሑፍ መልዕክት በመላክ ወይንም በመደወል፣
በፌስቡካችን መልዕክት በመላክ ይሆናል፡፡
የዕለቱ ትምህርት ርዕሶች፡- 1. ‹‹ልሳነ - ግዕዝ››
                  2. ‹‹የማናውቀው፣ ጨለማው፣ 96 በመቶውን የሚሸፍነው የበይነ-መረብ ክፍል ምን ይዟል?›› የሚሉት ናቸው፡፡
በዕለቱ የተለመደው የስነጽሑፍ ስራ እንደሚኖር ግልጽ ነው፡፡ ከሰሞኑ ያነበብነውን የምናጋራበት ዝግጅትም እንዲሁ፡፡ የጥበብ ስራ ቀድመው ለሚያስገቡ እና/ወይም ከሰሞኑ ያነበቡትን መጽሐፍ በአጭሩ ለሚገልጹ ተሳታፊዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ተሳታፊ የሚበዛ ከሆነም ሌሎች የማጣሪያ ዘዴዎችን የምጠቀም ይሆናል፡፡
ጥቂት ስለ አቅራቢው፡-
አቅራቢው ቤተመጻሕፍቱ በተቋቋመ ወቅት ጎብኛችን የነበሩ፣ አሁን ቀረት ቀረት ያበዙ ናቸው፡፡ ዛሬ ምሳ ሰዓት ተገናኝተን ለኔ የሚያስረዱኝ ነገር አብዛኛው ከአቅሜ በላይ ስለሆነና ለቤተመጻሕፍቱ አባላት ቢያስረዱልን ይጠቅማል ስላልኩ ጋበዝኳቸው፤ ያለ ምንም ማቅማማት ተቀበሉኝ፡፡
የዚያው ሰው ይበለን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...