ሐሙስ 25 ኦክቶበር 2018

አገር በቀል የሌብነት እና ዝርፊያ ዘዴዎችስ?

Inside the mind of a thief (የሌባው አስተሳሰብ)
በሚለው ዝግጅት ይህ ሌባ ምክር ይለግሳል። ለረጅም ጊዜ ሳይያዝ ሲሰርቅ የኖረ ሲሆን አሁን ፖሊስ እጅ ላይ ወድቋል። ከሃያ እስከ ሠላሳ ዓመት እስርም ይጠብቀዋል ተብሏል። የሚጠቀማቸው የስርቆት ዘዴዎች የሚከተሉትን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፦
ሀ. የውሾችን መኖር አለመኖር
ለ. የአላርምን ሁኔታ (ዋየርለስ ነው?)
ሐ. ቀን ወይም ማታ
መ. በፊት ለፊት ወይስ በጓሮ
ሠ. ከደጅ የተቀመጠ ፖስታና መልዕክት ወይም ያደገ ሳር ካለ ሩቅ አገር ሄደዋል ማለት ነው
ረ. መብራት ካበሩ (የውጪውን ወይም የውስጡን)
ሰ. ቀድሞ የተቀረጸ ድምጽ ከለቀቁ (የውሻ ወይም የራሳቸውን)
ሸ. ጎረቤት እዩልን ካሉ
ወዘተ
አሁን የዚህ መረጃ አስፈላጊነት ወዲህ ነው። በየአካባቢው ሌቦች፣ ዘራፊዎች እና ወንጀለኞች እየተበራከቱ ስለሆነ ለቅድመ ጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ የማጥቂያ ዘዴዎቻቸውን እንነጋገር። እንዴት እንከላከል? እርስዎ ምን ዓይነት ዘዴ ሠሙ?
የምትነግሩኝን አጠናቅሬ ለሁላችንም ደህንነት ስል እጽፋለሁ። መልካም ቀን!

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ቀጣዩ ትውልድ በምን ሊግባባ ነው?

 ቀጣዩ ትውልድ በምን ሊግባባ ነው? "Akkam olte haadha Ababaa? እግዚአብሄር ይመስገን። ደህና አደሩ እትዬ መገርቱ? Nagaadhaa. Ijjollee akkam? ሁሉም ደህና ናቸው።" ይህን መሰ...