ሰሞኑን በትምህርት ጉዳይ አንዲት አነስተኛ ጽሑፍ እየጻፍኩ የተለያዩ ሰዎችን አወያይቼ ነበር፡፡ እስካሁን
የማላውቀውና አሁን የሰማሁት መረጃ አለ፡፡ ይኸውም በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የነበሩት እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ
ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ሦስት ብቻ እንዲቀሩ መደረጉን ነው፡፡ ምክንያቱም በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ
መሰረት የመሰናዶ (ከ11ኛ -12ኛ) ትምህርት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ሦስቱ ብቻ ሲሆኑ ሌሎቹ እስከ አስረኛ ብቻ
እንዲያስተምሩ ተደርጓል፡፡ በዚህም ውሳኔ መሰረት ጥሩ ውጤት ኖሯቸው ደብረብርሃን፣ ሞላሌ ወይም ደብረሲና ሄደው
መማር ያልቻሉ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ፣ ግብርና ኮሌጅ ወይንም ቴክኒክ እንዲገቡ ተደርገዋል ማለት ነው፡፡
የዚህን ችግር ስፋትና ጥልቀት እንገነዘብ ዘንድ በወቅቱ የውሳኔው ሰለባ የሆናችሁ ጻፉልን፡፡
ውሳኔው በሁሉም ክልሎች ብቻ የተደረገ ነበር ወይ?
እስከ 12ኛ የሚያስተምረውን ትምህርት ቤት ለአራት አመታት ዘግተው በ1997 ምርጫ ማግስት ለምን ከፈቱት? ውሳኔው የፖለቲካ እንጂ የትምህርት ባለሙያ ላይሆን ይችላል፡፡
የዚህን ችግር ስፋትና ጥልቀት እንገነዘብ ዘንድ በወቅቱ የውሳኔው ሰለባ የሆናችሁ ጻፉልን፡፡
ውሳኔው በሁሉም ክልሎች ብቻ የተደረገ ነበር ወይ?
እስከ 12ኛ የሚያስተምረውን ትምህርት ቤት ለአራት አመታት ዘግተው በ1997 ምርጫ ማግስት ለምን ከፈቱት? ውሳኔው የፖለቲካ እንጂ የትምህርት ባለሙያ ላይሆን ይችላል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ