ቅዳሜ 29 ኦገስት 2015

ተጉለት ጉራንጉሩ፡ የጉዞ ማስታወሻ




መዘምር ግርማ እንደተረከው (Mezemir@yahoo.com)
ከሰባት አመታት በፊት ሳሲት* ከተማ አቅራቢያ ታሪክ ራሱን ደገመ፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ ሲያስቡት ይደንቃል፡፡ ድርጊቴንና ወኔዬን ከዳኛቸው ወርቁ ልቦለድ ገጸባህሪ ከአደፍርስ እንግዳ ተግባራት ጋር እንዳወዳድር ይዳዳኛል - ከቋንቋ ተማሪነት ወደ አማተር ጂኦሎጂስት ወይም አርኪኦሎጂስትነት ተለውጬ ነበርና፡፡ ሳሲትና አካባቢዋም ከ70 አመታት በኋላ ባለውለታዋን አስታወሰች፡፡ በሳሲትና አካባቢዋ ነዋሪዎችና በዋሻዎች መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርኝት ሊያሳይ የሚችለው ቀላሉ ነገር የተለያዩ ስፍራዎች የተሰየሙበት ከዋሻ ጋር የተያያዘ ስማቸው ይመስላል - ቀለም ዋሻ፣ ጠጠር ዋሻ፣ ጅብ ዋሻ፣ እንግድዋሻ፣ ልሳንዋሻ፣ ምግልዋሻ፣ አምባዋሻ፣ እምብስ ዋሻ፣ ጽድ ዋሻ፣ ንብ ዋሻ፣ ድል ዋሻ፣ ወርቅ ዋሻ፣ ላም ዋሻ፣ ጨለማ ዋሻ፣ ዋርካ ዋሻ፣ ሾላ ዋሻ …

በታሪካዊ ልቦለዱ በአዳባይ ላይ እንደተገለጸው ‹‹በ1931 ዓ.ም. በአንቀላፊኝ የራስ አበበ የጦር አዝማቾች ከምሁራን ባልደረቦቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ‹የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖቸ አርበኞች ማህበርን› አቋቁመው ፈረሙ፡፡›› (ገጽ 166-7)፡፡ አንቀላፊኝ ሜዳ እና ሌሎችም ታሪካዊ ስፍራዎች በትውልድ አካባቢዬ ቢገኙም በቅድሚያ የመጎብኘት ትኩረቴን የሳበው ከሳሲት እስከ ሰላድንጋይ በምድር ውስጥ ያስኬዳል ተብሎ የሚታመንበት ዋሻ ነበር፡፡ 20 ኪሎሜትር ገደማ ‹‹ይረዝማል›› ይባላል፡፡ ዋሻ መሸሸጊያ መሆኑ በታሪክ የታየበት ጊዜ አለ በሞጃ እና ወደራ ወረዳ፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት ልጅ ሆነው ተሸሽገውበት እደነበረ ያጫወቱኝ አቶ ማሞ ገብሬ፣ ካሳዬ ወንዳፈረው የተባለ የአካባቢው ተወላጅ አርበኛ ከጣሊያን ወራሪ ወታደሮች ጋር እየተታኮሰ የአካባቢውን ህዝብና ከብት ይዞ ወደ ዋሻው እንደገባ፣ ከብቱን የፋሽስት ወታደሮች ከዋሻው አውጥተው ሲያርዱና ሲጥሉት ህዝቡ ግን ራሱን ተከላክሎ ወደ ውስጥ ገብቶ እንደዳነና በማግስቱም የአምስት አመት የስደት ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ይፋት እንደወረደ ዋሻውም መጨረሻው እንደማይታወቅና ሰላድንጋይ ይደርሳል ሲባል እንደሰሙም ነግረውኛል፡፡ አቶ አስፋውና አቶ ተክለወልድ ደግሞ ከደጋው ህዝቡ ሲያባርረው የመጣን ጅብ ዋሻው ውስጥ ሊገባ ሲል እንደገደሉት አጫውተውኛል፡፡ ከአብዛኛዎቹ ተጠያቂዎቼ እንደሰማሁት ግን በአንድ ወቅት አንዲት ውሻ በዋናው በር ስትገባ ታይታ ሰላድንጋይ ለጉዳያቸው የወጡ ስትገባ ያዩዋት ሰዎች እዚያም ባለው በር ስትወጣ አይተዋታል እየተባለ እንደሚተረት ነው፡፡ እንዲያውም የዋሻው የሰላድንጋዩ መውጫ በሩ ቁሮ ገደል በተባለ ስፍራ እንደሚገኝ ነግረውኛል፡፡ ለተጠያቂዎቼ ግን ‹‹ይህን ያህል ርዝመት እንዳለው አይታችኋል›› ስላቸው ‹‹እሱ ተብሎ ያለቀ ነው›› ይሉ ነበር፡፡ በህዝቡ ዘንድ የሚወራውን ለማረጋገጥ ዘመቻ ግድ ይል ነበር፡፡

ለ15 ቀናት ያህል ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ስለዚሁ ጉዳይ እንመክራን፤ ስለ ዋሻው የሰሙ ሰዎች መጥተው የሚነግሩኝንና ለዝግጅት የሚያስፈልጉትን ቁሳቁስም እጽፋለሁ፡፡ እንደነፍሰጡር ቀናችንን መቁጠሩ የባሰ ጉጉት አሳደረብን፡፡ ከመካከላችን አንዳንዶቹ የሚያነሷቸው ሃሳቦች የሚከተሉትን ይመሳስሉ ነበር - ‹‹ወደ ዋሻው ገብተን ብንጠፋፋና የዋሻው በር ቢጠፋብን የት እናገኘዋለን?››  እና ሌሎች ደግሞ ‹‹ስንሄድ ባህር ወይም ጎድጓዳ ስፍራ ቢገጥመን ተቀርቅረን መቅረታችን አይደለምወይ?›› ይላሉ፡፡ አስጊ ሁኔታ ነበር፡፡
ከአዛውንቶች በሰበሰብኩት መረጃ መሰረት ዋሻው ወደተለያየ አቅጣጫ የሚወስዱ መንገዶች ስላሉት አንዱን ተከትለን ሰው ወደ ጎን እንዳይሄድ እየተቆጣጠርን መሄድ ፣ ሰላድንጋይ ከተማ የሚያደርስ ከሆነ መንገዱ እንደ መሬት ላይ መንገድ ስለማይቀና ስንቅ ቋጥረን የፈጀውን ያህል ጊዜ ይፍጅ እንጂ የዋሻውን መጨረሻ ማየት አለብን አልን፡፡ በጉዟችን ወቅት ድቅድቅ ጨለማውን ለማብራት ችቦ፣ ጧፍ፣ ማሾ፣ ባትሪ እና ሻማ እንያዝ የሚሉ ሃሳቦች መጡ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ችቦ ጭሱ ያፍነናል ባትሪም ዋሻው ውስጥ አይበራም በማለታቸው ማሾ እና ጧፍ ለመያዝ ተስማማን፡፡
መሽቶ ሲነጋ ሁለት ሳምንት ቀኑን ሙሉ ስለዚሁ ዋሻ ስናወራ እንውላለን፡፡ገብተን ሰይጣን ልናገኝ፣ ለደህንነታችን የሚያሰጋ ተአምራዊ ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል የሚሉ ሰዎችን ስጋት ወደኋላ እየተውን ለመግባት የሚያስፈልገውን የቁሳቁስም ሆነ የስነልቦና ዝግጅት ቀጠልን፡፡ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከመሬት በታች መላዕክት እንደሚኖሩ፣ ሰዎች የሚኖሩበት ሌላ ሃገር እንዳለ፣ በዶሮ የሚታረስበት ግዛትም እንደማይጠፋ ስንሰማ አድገናል፡፡ ምናልባት ይህን የምናይበት ሌላ አለም ሊገኝ ይችላል ብዬ እኔም አስብ ሌሎችም በአዕምሯቸው ያወጡና ያወርዱ ነበር፡፡ሰው ባገኘኝ ቁጥር አስረዳለሁ፤ ጥያቄዎቻቸውንም እመልሳለሁ፤ በሰዎቹ ፍላጎት ደስታና እርካታ ይሰማኛል፤ እጓጓለሁ፤ እገረማለሁ፡፡ በአካባቢያችን ሌሎች መሰል ዋሻዎች አሉ ቢባልና እኛም ብናውቅ መጀመሪያ ያደረግንውን ይህን ዋሻ ለመጎብኘት አንድ ቀን ቀረን - ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 1999 ዓ.ም. ፡፡ በትውስት ማሾዎች ጋዝ ሞላን፤ ጧፎቻችንን ገዛን፤ ሻማና ሌሎችንም እንዲሁ አሟላን፡፡ ሰዉ በማቴሪያል፣ በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት ከጎናችን ስለነበረ ነው ዓላማችንን በመጠኑ  ለማሳካትና ይህን ለእናንተ ለመንገር የበቃንው፡፡
በማግስቱ በዋሻው አቅራቢያ ያሉና ሊገቡ የተስማሙ ገበሬዎች በጠዋት እንድትመጡ ስላሉን ሕዝቡንም ለመቀስቀስ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ ጓደኞቼን ቀስቅሼ ሌሎችንም እንዲቀሰቅሱ አሳሰብኩ፡፡ ከነጋ በኋላ ወደ 12፡30 ሰአት ላይ ተጠቃለን ጉዟችንን ለማድረግ ከከተማዋ እምብርት ተነሳን፡፡ ያሰብንውን ያህል ባይሆንም ወደ ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ተሰባስበናል፡፡ በየቤቱ እየሄድን ስንቀሰቅሳቸው በሰበብ ባስባቡ እንደማይሄዱ አስተዛዝነው ይነግሩናል፡፡ እኛም ‹‹አላስገደድናቸው ከመጀመሪያው ለምን እሺ አሉ? ሰው ሂድ ብሎ ሳያስገድዱት እሄዳለሁ ይላል እንዴ?›› ብለን ታዘብናቸው፡፡ ለማንኛውም እኛው እንበቃለን ብለን ዝግ ባለ አረማመድ ከተማዋን ለቀን ወደ ምዕራብ ስንጓዝ ሰው ሁሉ ያየናል፡፡ ‹‹አረ የነብር ቁርስ እንዳትሆኑ!›› ሳይል አይቀርም ተመልካቹ - ካይኑ ያስታውቅበታል፡፡ ከተማዋን ለቀን ወደገጠሩ ስንገባ ሰዎች ከዚህም ከዚያም እየሮጡ ከከተማዋም ጭምር ተከተሉን፡፡ በርከትከት እያልን መጣን፡፡ በየቤቱ እንዲሰማ አድርገን የምናውቃቸውን ሰዎች ተጣርተን ብዙ ሰዎች ለመሰብሰብም ቻልን::

ወደ ሰሜን ታጥፈን ቁልቁል ከወረድን በኋላ አፋፉ ላይ ስንደርስ መንዝን ካድማስ ወዲያ ማዶ እያየንና የቆላማውንም ስፍራ ልምላሜ እያደነቅን ለደቂቃዎች እንኳን ሳንቆይ፣ አያቴ ‹ያ ማዶው ሰላሌ ነው› የሚለኝን ጨለማ አገር ቃኝተን ሳንጠግብ አትኩሮታችንን ወደ ተጉለቱ ድንቅ ዋሻ መለስን፡፡ የአካባቢው ገበሬም ቀድሞን ዋሻውንና አካባቢውን ወሮታል፡፡ በዙሪያው ከሩቁ የሚታዩትና ነጫጭ የለበሱት እነዚህ ሰዎች የጥንት አርበኞችን ያስታውሷችኋል፡፡ ደምቃ ፍም መስላ ከወጣችው የጠዋት ፀሀይ ግርጌ ከግራና ከቀኝ ትልልቅ ተራሮችን የተሸከመውና በመሃልም ሸለቆ የሚንፈላሰስበት ባለረጅም አፉ ዋሻ በአረንጓዴ ቅጠላ ቅጠል ተከቦ፣ በሸለቆው ውስጥ የሚመጣው ወንዝና በዋሻው መግቢያ ፊት ለፊት የሚወርደው ፏፏቴ አንድ ላይ ሆነው ሌላ ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት እነሆ አሉን፡፡ አንዲት አጎንብሳ ጸጉሯን በሳሙና የምታሽና ጸጉሯም በመታጠቢያው ሳፋ ላይ ለሽ ያለን ኮረዳ ያስመስለዋል፡፡  ጸጉሯን በፏፏቴው፣ ከንፈሯን በዋሻው አፍ ፣ ሁለቱን ትከሻዎቿን በተራሮቹ እንዲሁም ሳፋውን  እታች ፏፏቴው በሚያርፍበት ባህር መመሰል ይቻላል፡፡ ይህን ሁሉ በማየቴ ተደነቅሁ፡፡ ከባልንጀሮቼ ጋር ወደዋሻው ተጠጋሁ፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች በዋሻው በር ላይ ተቀምጠው ታሪክ ያወራሉ፣ ይመክራሉ፡፡
ዋሻው በጎንና በጎኑ መግቢያ መንገድ ስላለው ሸረር ብለን ገባን፡፡ አቤት የነበረ ጥድፊያ!  አቤት ያን ዋሻ ተጠግቶ ሲያዩት ያለው ግርማ ሞገስ፡፡ ውስጥ ስንገባ አናቱ ደማቅ ጥቁር ፣ መሬቱ ደግሞ ቀይ ደረቅ ለስላሳ አፈር ሲሆን ጣራው የጠቆረው አባቶቻችን በጣሊያን የግፍ ወረራ ጊዜ በችቦ ለብልበውት ነው ተባልን፡፡ ምክንያቱም ማዕድን ሊሆን ስለሚችል በጣሊያኖች አይን እንዳይገባ ተብሎ ነበር፡፡ ሲፈረፍሩት የሚያብረቀርቅ ልዩ አለት እየተፈረፈረ ይወርዳል፡፡ የወንዙ/የፏፏቴው ውሃ በፊታችን ወርዶ መሬት ላይ ሲያርፍ የሚያሰማው ልዩ ድምጽ ልብን ያሸብራል፣ አዕምሮን በአንዳች ፍርሃታዊ ምትሃት ያርዳል፤ ሁለመናን ይቀሰቅስማል፡፡ ሽሽሽ… ቻቻቻ… ይላል፡፡ ይህም በአቅራቢያው ካለው አያልፉሽ ከተባለው የጸበል ቦታ፣ ከአጃና ሚካኤልም በላይ ምጡቅ ነበር፡፡ ባሕታዊነትን ያስመኝማል፡፡ በዋሻው አቅራቢያ ያለው ስነ-ሕይወታዊ መስተጋብር ለዘርፉ ምሁራን ለም የምርምር ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡ አይደርሱ የለ ደረስን፣ አየንው የንን የጓጓን የቋመጥንለትን  ዋሻ! ታዲያ አፉን እንጂ ሆድ እቃውን ለማየት ገና በዝግጅት ላይ ነበርን፡፡ ማሾዎች ተለኮሱ፤ ጧፉንም ያዝንና ታጥቀን ተመራርጠን ተነሳን፡፡ የዋሻውን አፍ ርዝመት ለክተን 105 ሜትር መሆኑን አረጋገጥን፡፡ ከፍታውም በመግቢያው በር አካባቢ ከ3 ሜትር ቢበልጥ እንጅ አያንስም፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በጉንብስ አለያም በጣም ዝቅ ሲል በደረት መሄድ ግድ ይላል፡፡
በውስጠኛው የዋሻው ክፍል አለትና ቋጥኝ፣ የጅብ ጽዳጅ፣ የእንስሳት ብሎም የሰው አጽም አግኝተናል፡፡ ዙሪያውን አሰስንው፤ ጎበኘንው፡፡ ሆኖም ግን  በዚያ በሰፊው የዋሻው ክፍል ውስጥ ወደ ውስጥ መፈናፈኛ ጠፋ፡፡ ‹‹በምን ተገብቶ ነው ሰላድንጋይ የሚደረሰው?›› ብዬ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ አብዛኛዎቹ ተጠያቂዎቼ ‹‹በግለሰቦች ተደፍኖ ነው እንጅ በር ነበረው ፤ የቱጋ እንደሆነ ለማግኘት ከቋጥኙ መብዛት የተነሳ አልቻልንም›› አሉኝ፡፡ ቋጥኞቹን አልፎ ሄድ ሲሉ በዋሻው የቀኝ ክፍል ወደ መሬት የሚያሰገባ መንገድ አግኝተው የተወሰኑት ጓደኞቻችን ገቡ፡፡ አንዲት ሽንቁር ማሰሮና ሁለት የሰው የራስ ቅል ይዘውም ተመለሱ፡፡ ደረጀ አስራተ የተባለው ሌላኛው ዘማች ደግሞ በዋሻው መግቢያ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ‹‹ጎራዴ ና ባትሪ ብቻ ስጡኝ›› ብሎ በአንዲት ሰው ሁሉ በፈራት ጠባብ ጎሬ አልፎ ሄዶ ቀረብን፡፡ ግማሹ ሰው ፈራ ተባ እያለ ‹‹ወደ ኋላ ልመለስ ወይንስ ልጠብቀው፣ ጅብ በልቶት ይሆን ነብር?›› ሲል፣ ደምሰው ታችበሌ በልበሙሉነት ሲጋራውን ሲያጨስ በመጨረሻ የደረጀ ድምጽ ሲሰማ ህዝቡ እፎይ አለ፡፡ እኔም ደስ አለኝ፡፡ ‹‹ምን አለ›› ስንለው ‹‹የሆነ ወደላይ የሚያስወጣ መንገድ አለ ወጥቼ ልምጣ›› ሲለን እንደገና ደንገጥ አልንና ጠበቅንው፡፡ ‹‹አይይይ ምንም የለ›› ሲል አንድ ሆነ፡፡ 
ወደ አስር የሚሆኑ በዋሻው የግራ አቅጣጫ የሄዱ ሰዎች ደግሞ ትንሽ ሄደው ሰማይ ሲያዩ ‹‹ሌላ አገር የደረስን መሰለን›› ብለው ጮሁ፤ ግን ሌላ የዋሻው መግቢያ በር ነበር፡፡ ስለዚህኛው መግቢያ በር፣ ከዋናው በር ሌላ መሆኑ ነው፣ በዚያኛው ቡድን በኩል ባለመሆኔ ማየት ባልችልም ከሰማሁት ለመናገር ግን እችላለሁ፡፡ እኔ የነበርኩት በበሩ ትይዩ በነበረው አቅጣጫ ነበር፡፡ አቶ ታደሰ ዘነበ እንደነገሩኝ ደግሞ በዚሁ በቀኙ አቅጣጫ ወደታች አይቼ ልምጣ ብለው ገብተው ጓደኞቻቸው ጥለዋቸው/ረስተዋቸው ሄደው መውጫው ጠፍቷቸው ለደቂቃዎች ተቸግረውና ቢጣሩ የሚሰማቸው አጥተው በስንት ፍለጋ የገቡባትን ከሰው ትከሻ የማትሰፋ በር አግኝተው ወጥተዋል፡፡  ‹‹እኔ ተቻኩዬ ተመለስኩ እንጂ ያችማ ያች የተባለችው ከጎተራ አፍ ትጠባለች ያሏት ወደሰላድንጋይ የምታወጣው የጠፋችብን ዋናዋ በር ሳትሆን አትቀርም፤ ስንትና ስንት መንገድ እኮ ሄጃለሁ፤ በደንብማ ቢፈለግ ይህ ዋሻ አንድ ነገር አይጠፋውም ›› ብለዋል በእለቱ ከሰዓት በኋላ ጉዟችንን ስንገመግም፡፡

በሁሉም አቅጣጫዎች የአለቱን ብዛት አንድ መሃንዲስ ቢኖር በቢያጆ ይገምትልን ነበር፡፡ አንድ ትምህርት ቤት ይሰራል፡፡ ወደፊት በዚያ ዋሻ ሄደን ምናልባት ሰዎች ካገኘን ለልጆቻቸው ትምህርት ቤት መስሪያ ስሚንቶ ብቻ ከገዙ ይበቃቸዋል፡፡ ዋሻችን ከላይ የሚያዥ ነገር እና መሬትም ላይ የዚያው ክምችት (stalactites and stalagmites) ብዙ ቦታዎቹ ላይ አለው፡፡ ወለሉ ጫር ጫር ሲያደርጉት አፈሩ ልስልስና በእጅም ቢዝቁት የሚዛቅ ነው - ልክ አሸዋ በሉት፡፡ አንዳንዴ በቡድን በቡድን ሆነን ስንድህ ልጅነታችንን ያስታውሰናል፡፡ ከዚያ ደግሞ ሄደን የሚያስቆምና የሚያስፎክር ቦታም እናገኛለን፡፡ በእንደዚህ አይነት ጉዞ ታዲያ መደራጀትን የመሸሽ ችግር አይቀረፍምና ‹‹በቃ እንሂድ፤ በቃ አገራችን እንውጣ!›› እያሉ ካስቸገሩትና ባጭሩ ተስፋ ከቆረጡት በላይ አንዳንዶቹ ከዋሻው እየወጡ ወደ ሳሲት ይመለሱ ጀምረው ነበር፡፡ አንድ ሽማግሌ ደግሞ ከዋሻው በር ላይ ካለው ካብ ላይ ትልልቅ ድንጋይ እያነሱ ታች ቆላ ወዳለው ባህር ሲወረውሩ ረበሹኝ፡፡ ‹‹አረ ተው አብዬ ምነው?›› ሲሏቸው መች ይሰማሉ፡፡ ብቻ ይስቃሉ ደስ ብሏቸዋል መሰለኝ ቦታው፡፡ ይህ በዋሻው በር ላይ የተካበው ካብ አርበኞች ምሽግ አድርገው ይጠቀሙበት የነበረ ይመስለኛል፡፡
በጎብኝዎቹ መጣደፍ ምክንየት ብቻ ከሰአታት መጠነኛ አሰሳ በኋላ ወደ ሳሲት ከተማ በዋሻው በር በሌላኛው አቅጣጫ ወጥተን ትንሽ ዳገትም (ልዩ ስሙ ትልቅ አረህ) ፈትኖን የመልስ ጉዟችንን ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይዘን ጀመርንው፡፡ የወረድንው በጭጨት ነበር፡፡ ብዙም ተጉዘን እረፍት ተደረገና ወደ ከተማችን ደርሰን አንድ ቤት ገብተን ውይይትና ጨዋታው ቀለጠ፡፡ ከጉዟችን በኋላ ገበሬው ማዕድን አለበት እያለ የዋሻውን አናት ያገልሰው እንደያዘ ሰማን፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት ከተደረገው ቀጥሎ (ከሰባ አመታት በኋላ) ህዝብ ተነሳስቶ የገባበት ትልቁ ዘመቻ በዚህ መልኩ ተጠናቋል፡፡ ሌላ ጉብኝትና ጥናት ለማድረግ ሰባ አመታት እንጠብቅ ይሆን? ስለተነሳሽነቱ ህዝቡን ባያሌው አመሰግናለሁ፡፡ ህዝቡ ያለው ‹‹ዱሮስ እሱን አምነን›› ሳይሆን ‹‹ይህ ዋሻ ቀን ይወጣለታል›› ነው፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዶ/ር ሲቪል መሃንዲስ ሀይለጊዮርጊስ ወርቅነህ የህይወት ታሪክ ላይ እንደተመለከተው ከሶስት መቶ በላይ የአርበኛ ጦር ከነቤተሰቡ በሳሲት አቅራቢያ ባለ አንድ ዋሻ መሽጎ ነበር፡፡ በተጉለት ሌሎች አርበኞችን ፍለጋ የሚዘዋወረው ይህ ጦር ዋሻ ውስጥ እንደመሸገ በአካባቢው ነዋሪዎች ይጠቆምበትና በአንድ ሺህ የጣሊያን ጦር ይከበባል፡፡ አስራ አራት ቀን ሙሉ በረሃብ ተሰቃይተውና ከዋሻው የላይኛው ክፍል የሚያዠውን ውሃ እየመጠጡ፣ ኮርቻ ፈልጠው እያነደዱ የጤፍ ቆሎ እየቆሉ እየበሉ፣ የጣሊያን ጦር እየተኮሰባቸው ከቆዩ በኋላ በአስራ አራተኛው ሌሊት ወንዶቹ ጥሰው ሲወጡ ተጨፈጨፉ፤ አስራ ሁለት አመት ገደማ ያሉ ወንድ ልጆችም ተረሸኑ፤ ሴቶቹና ህጻናት መጀመሪያ ወደ መንዝ ከዚያም ወደ ደብረ ብርሃን እስርቤቶች ተወሰዱ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትም ዶ/ር በዚያን ወቅት አስር አመታቸው ሲሆን በኋላ አድገው ተምረው አለምአቀፍ ምርምሮችን አቅርበው ተሸልመዋል፡፡ በሳይንስ መዛግብት ላይ ስማቸውን ያሰፈረላቸው እስከ 150 ኪሎሜትር ርቀት ጠጣር ነገርን የሚያስተላልፈው ቧንቧቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ (አልፈዋል)! ከመጽሀፋቸው የሚከተለውን እንመልከት ፡- ‹‹በዋሻው ውስጥ አባቴ፣ አጎቴ፣ እናቴና ያጎቴ ባለቤት እና ከዘጠኝ የሚበልጡ የቅርብ ዘመዶቻችን፣ እና ሌሎች ቤተሰቦች እንዲሁም ከ300 የሚበልጥ መሳሪያ ያለው ሰው ነበር፡፡ በዚያም ላይ የቀንድና የጋማ ከብቶችና የቤት እንስሳዎችን የመሳሰሉ ሁሉ ከዋሻው ውስጥ ነበሩ፡፡ ለጥቂት ቀናት የሚበቃ ምግብ፣ ውሃና ማገዶም ተይዞ ተገብቶ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ለ14 ቀናት ያህል በመከበባችን፣ ያ ይዘን የገባንው ምግብና ማገዶ አለቀ፡፡ ዋሻው ፊት ለፊት ከሚፈሰው ውሃ ለመቅዳት እንዳንችል፣ ጠላት ፊት ለፊት መሽጎ ይጠባበቅ ስለነበረ፣ በጣም አስቸጋሪ ሆነ፡፡›› የህይወቴ ታሪክ (10)    
ይህን ታሪክ እኔና ሳሲቶች የገባንበት እንግድዋሻ አለያም በሱው አቅራቢያ የሚገኘው ልሳን ዋሻ ሊጋሩት ይችላሉ፡፡ ልሳን ዋሻ በአንድ ቀን ብቻ ከ600 በላይ ሰው እንደተረሸነ አዛውንቶቹ አጫውተውኛል፡፡ ይህ ከላይ የተጠቀሰው ግድያ ሊሆንም ይችላል፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም የታሪክ፣ የጂኦሎጂና የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎቹን አስተባብሮ ይህን ዋሻ፣ ሌሎችን ዋሻዎችና ታሪካዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ስፍራዎችን ቢያስጠና ለአካባቢው ህዝብ ባለውለታ ያደርገዋልና ቢያስብበት እላለሁ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የፌደራሉ መንግስት፣ የአርበኞች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶችም የተጉለት ቅርሶች ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ቢሰሩ በማለትም አሳስባለሁ፡፡
ጣሊያን ቤቱን ሲያቃጥልበት ህዝቡ ዋሻዎች ውስጥ ነበር የኖረው፡፡ አሁንም ዋሻ እንደሚፈለግ ያሳየኝ ክስተት ቢኖር አንድ አዛውንት በ1999 ዓ.ም. ‹‹አንተ ልጅ ጓዳችንን ለምን ለሰው ታሳያለህ?›› ያሉኝ ነው፡፡ የእርሳቸውን ሃሳብ እያከበርኩ አሁን የአለም ሁኔታ እየተቀየረ መሄዱንና ዋሻ ውስጥ እስክንገባ የሚያሳድደን ነገር እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዋሻውን ለአገር ጎብኝ እያሳየን የገቢ ምንጭ እንድናደርገው እና እኛም እንጎበኘው ዘንድ የሁላችሁንም ትብብር በሁሉም ዘማቾች ስም እጠይቃለሁ፡፡ በመጨረሻም ለጭቁን ህዝቦች አርዓያና መጽናኛ በሆኑት በኢትዮጵያ በአርበኞች መዝሙር ልሰናበት፡-
ጥንታዊት ኢትዮጵያ እናታችን ሆይ
አርበኛሽ ጽኑ ነው ቆራጥ ተጋዳይ
የደሙ ምልክት ያው በልብሱ ላይ
ጥንታዊት ኢትዮጵያ አትደፈሪቱ
ጠላትሽ ግፈኛ አረመኔ ከንቱ፡፡
ጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ማህበር
ጠላትሽ ተዋርዶ ስምሽ እንዲከበር
እንሸከማለን የመከራ ቀንበር፡፡

አዳባይ (243)


*ሳሲት ከተማ ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን 92 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኝ ተጉለቴ ነች፡፡ ከሞጃና ወደራ ወረዳ መዲናዋ ከሰላድንጋይ ደግሞ 20 ኪ.ሜ ትርቃለች፡፡ ሰላድንጋይን ብዙ ሰው በጻድቃኔ ማርያም ገዳም ያውቃታል፡፡





ማክሰኞ 18 ኦገስት 2015

የሙታን መንገድ


ደራሲ-ችንዋ አቼቤ (1930 - 2013)
መዘምር ግርማ እንደተረጎመው
የሚካኤል ኦቢ ምኞቶች የተሳኩለት አስቦት ከነበረው እጅግ ቀድመው ነበር፡፡ በጥር 1949 ዓ.ም የንዱሜ ማዕከላዊ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሆኖ ተሾመ፡፡ ትምህርት ቤቱ ብዙጊዜ ኋላቀር ሆኖ ስለቆየ የሐይማኖታዊ ተልዕኮው ባለስልጣናት ወጣትና ጉልበቱ ያልተነካ ሰው ያስተዳድረው ዘንድ ለመላክ ወሰኑ፡፡ ኦቢም ይህንን ኃላፊነት በደስታ ተቀበለው፡፡ ብዙ አስደማሚ ሃሳቦች ስለነበሩት ይህ ሁነኛ ዕድል በተግባር ይተረጉማቸው ዘንድ የሚጠቅም ነበር፡፡ የተከታተለው ጥሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሌሎች በሐይማኖታዊው ተልዕኮ ስር ካሉ ርዕሳነ መምህራን አጉልቶ ያወጣው «ወሳኝ መምህር» የሚል ስም በመስሪያ ቤቱ አስገኝቶለት ነበር፡፡ የአሮጌዎችንና በአብዛኛው ብዙም ያልተማሩትን ሰዎች ጠባብ አመለካከቶች ሲያወግዝ አይጣል ነው፡፡
«ልንጠቀምበት ይገባል፤ አይደል?» ሲል ወጣት ሚስቱን አስደሳቹን የዕድገቱን ዜና ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰሙ ጠየቃት፡፡ «የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፡፡» ስትል መለሰች፡፡ « ቆንጆ የአትክልት ስፍራዎች ይኖሩናል፣ እና ደግሞ ሁሉ ነገር ዘመናዊና ማራኪ ይሆናል …» በሁለት አመት የጋብቻ ቆይታችው «ለዘመናዊ አሰራሮች» ባለው ፍቅርና «ለአሮጌና ጊዜ ላለፈባቸው በትምህርት ሙያ ውስጥ ላሉና በኦኒሻ ገበያ ነጋዴ ሆነው ቢቀጠሩ ለሚሻላቸው ሰዎች» ባለው አግባብ ያልሆነ የትችት ፍቅር ሙሉ በሙሉ ተለክፋለች፡፡ ራሷን የወጣቱ ርዕሰ መምህር ተደናቂ ሚስት የትምህርት ቤቱም ንግስት አድርጋ መውሰድ ጀምራለች፡፡ በሷ ቤት የሌሎች አስተማሪዎች ሚስቶች የሷን ቦታ ይመቀኛሉ፡፡ በሁሉ ነገር ቀዳሚ ትሆናለች…
ከዚያም በድንገት ሌሎች ሚስቶች አይኖሩ ይሆናል የሚል ሃሳብ ብልጭ አለላት፡፡ በተስፋና ፍራቻ መሃል እየዋለለች ባለቤቷን በስጋት እያየች ጠየቀችው፡፡
«ሁሉም የስራ ባልደረቦቻችን ወጣትና ላጤ ናቸው፡፡» አላት እሷ በመጀመሪያ ባልተጋራችው የደስታ ስሜት፡፡ «መልካም ነገር ሆነልን ማለት ነው፡፡» ሲልም ቀጠለ፡፡
«ለምን?»
«ለምን? ሙሉ ጊዜና ጉልበታቸውን ለትምህርት ቤቱ ይሰጣሏ፡፡»
ናንሲ አቀረቀረች፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ስለአዲሱ ትምህርት ቤት ጥርጣሬ ገባት፤ ግን ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ነበር፡፡ ትንሿ የግል ዕድለቢስነቷ የባሏን አስደሳች የወደፊት ህልም ልታጨልምበት አይገባም፡፡ በወንበሩ ላይ እንዳቀረቀረ ባሏን አየችው፡፡ ወገበ ጎባጣና የሚሰበር የሚመስል ነበር፡፡ ሆኖም አልፎ አልፎ በድንገት በሚያሳየው አካላዊ ጉልበት ሰዎችን ያስገርማል፡፡ በአሁኑ ተክለ ሰውነቱ ግን አካላዊ ጥንካሬው ሁሉ ገባ ገባ ባሉት አይኖቹ ውስጥ የተቀበረ ይመስላል፤ ለዓይኖቹ ጥልቅ ሰርጎ ገብ ሃይልም ሰጥቷቸዋል፡፡ ሃያ ስድስት አመቱ ቢሆንም ሲያዩት የሚመስለው ግን ሰላሳ ወይም ከዚያ በላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ግን አስቀያሚ አልነበረም፡፡
«ስለምን እያሰብክ ነው ማይክ?» አለች ናንሲ ከአፍታ በኋላ አንብባው የነበረውን የሴቶች መጽሔት በማስመሰል፡፡
«ትምህርት ቤት እንዴት እንደሚተዳደር ለነዚህ ሰዎች ለማሳየት በስተመጨረሻ እንዴት ያለ ትልቅ ዕድል እንዳገኘን እያሰብኩ ነበር፡፡» አላት፡፡
ስለ እውነት ከሆነ የንዱሜ ትምህርት ቤት ኋላቀር ነበር፡፡ አቶ ኦቢ ሙሉ ሕይወቱን ለስራው አውሎ ነበር፤ ሚስቱም እንዲሁ፡፡ ሁለት አላማዎች ነበሩት፡፡ ጥሩ ደረጃ ያለው ትምህርት ግድ የሚል ሲሆን የትምህርት ቤቱ ቅጽረ ግቢ ደግሞ ወደ ውበት አውድነት መቀየር ነበረበት፡፡ የናንሲ ምኞት የነበሩት የአትክልት ስፍራዎች ዝናቡ በሰዓቱ በመምጣቱ ሳቢያ ህያው ሆኑ፤ አበቡም፡፡የሚያማምሩ ደማቅ ቀይና ቢጫ አበቦች የተተከሉባቸው መደቦች በእንክብካቤ የተያዘውን የትምህርት ቤት ግቢ ከአቅራቢያው መንደር የቁጥቋጦ ጫካ ለይተው አወጡት፡፡
አንድ ምሽት ኦቢ ስራውን እያደነቀ ሳለ አንዲት ሽማግሌ ሴትዮ ከአቅራቢያው መንደር እያዘገሙ በትምሀርት ቤቱ ግቢ የቢጫዎቹንና ቀዮቹን አበቦች መደቦች እየረገጡ አቋርጠው ሲያልፉ በማየቱ የውርደት ስሜት ተሰማው፡፡ ሴትዮዋ ወዳቋረጡበት ስፍራ ሄዶ ቢመለከት ብዙም አገልግሎት የማትሰጥ ከመንደሩ ትምህርት ቤቱን አቋርጣ በሌላው አቅጣጫ ካለው የቁጥቋጦ ጫካ የምትወስድ የእግር መንገድ የጠፉ ምልክቶችን አገኘ፡፡
«መንደርተኞቹ ይህን መንገድ እንዲጠቀሙ መፍቀዳችሁ ይደንቀኛል፡፡ እንዲያው የማይታመን ነገር እኮ ነው በሉ፡፡» አለ ኦቢ በትምህርት ቤቱ ለሶስት አመታት ሲያስተምር ለቆየ አንድ መምህር፡፡ ራሱንም ነቀነቀ፡፡
«መንገዱ» አለ መምህሩ በይቅርታ ድምጽ «ለእነርሱ በጣም አስፈላጊ ይመስላል፡፡ ብዙም ባይጠቀሙበትም የመንደሩን የአምልኮ ስፍራ ከቀብር ቦታቸው ጋር ያገናኛል፡፡»
«እና ያ ታዲያ ከትምህርት ቤቱ ጋር ምን ያገናኘዋል?» ሲል ርዕሰ መምህሩ ጠየቀ፡፡
«አይ እሱን እንኳን አላውቅም» ሲል መምህሩ ትከሻውን በምን ቸገረኝ ስሜት ነቅንቆ መለሰለት፡፡ «ግን ከተወሰነ ጊዜ በፊት መንገዱን ልንዘጋው ሞክረን ትልቅ አለመግባባት መከሰቱን አስታውሳለሁ፡፡»
«ያ ከተወሰነ ጊዜ በፊት ነው፡፡ አሁን ግን ማንም ሊጠቀምበት አይችልም፡፡» ብሎ ኦቢ ሄደ፡፡ ‹‹የመንግስት ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊውስ በመጪው ሳምንት ትምህርት ቤቱን ለመገምገም ሲመጣ ምን ያስባል? መንደርተኞቹ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ በቁጥጥሩ ወቅት መማሪያ ክፍሉንም ለአረማዊ አምልኮ እንጠቀማለን ብለው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡››
መንገዱ ወደ ትምህርት ቤቱ በሚገባና በሚወጣባቸው ቦታዎች ላይ እንጨት ተተከለ፤ ከዚያም በእሾሃም ሽቦ ታጠረ፡፡
ከሶስት ቀናትም በኋላ አኒ የተባሉ የመንደሩ የሃይማኖት አባት ርዕሰ መምህሩን ማነጋገር እፈልጋለሁ ብለው መጡ፡፡ ጎብደድ ብለው የሚሄዱ ሽማግሌ ናቸው፡፡ በውይይታቸው መሃል አንዳች ጥሩ ነጥብ በሰነዘሩ ቁጥር አጽንዖት ለመስጠት መሬቱን መታ መታ የሚያደርጉበትን ወፍራም ምርኩዛቸውን ይዘው ነበር፡፡
‹‹ሰማሁ›› አሉ ከተለመደው የሰላምታ ልውውጥ በኋላ ‹‹ያባቶቻችን መንገድ በቅርቡ መዘጋቱን ሰማሁ…››
‹‹አዎን›› ሲል መለሰ አቶ ኦቢ፤ ‹‹ማንም ትምህርት ቤታችንን መንገድ እንደዲያደርገው አንፈቅድም፡፡››
‹‹እየውልህ ልጄ›› አሉ የሃይማኖት አባቱ ምርኩዛቸውን ወደ መሬት ዝቅ እያደረጉ፤ ‹‹ይህ መንገድ አንተም ሆንክ አባትህ ሳትወለዱ የነበረ ነው፡፡ የመንደሩ ሕይወት በሙሉ የተመሰረተው በሱው ላይ ነው፡፡ የሚሞቱ ዘመዶቻችን በመንገዱ አድርገው ነው የሚሰናበቱን፤ እንዲሁም የሞቱት አያቶቻችን ሳይቀሩ እየመጡ የሚጠይቁን በዚያው ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ሊወለዱ የሚመጡ ህጻናት የሚመጡበት መንገድ ነው…››
አቶ ኦቢ እርካታ የተሞላበት ፈገግታ በፊቱ ላይ እያሳየ አዳመጠ፡፡
‹‹የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ዓላማ›› አለ በመጨረሻ ‹‹እንደዚያ ያሉትን እምነቶች ማስወገድ ነው፡፡ የሞቱ ሰዎች የእግር መንገድ አያስፈልጋቸውም፡፡ ሃሳቡ በአጠቃላይ የማይሆን ነው፡፡ የኛ ኃላፊነት ልጆቻችሁን በእንደዚህ አይነቶቹ ሃሳቦች ላይ እንዲስቁ ማስተማር ነው፡፡››
‹‹የምትለው ትክክል ሊሆን ይችላል፤›› አሉ አረማዊው ቄስ፡፡ ‹‹እኛ ግን ያባቶቻችንን እምነት ነው የምንከተለው፡፡ መንገዱን ከከፈትክልን የምንጣላበት ምንም ነገር የለንም፡፡ እኔ ሁልጊዜ የምለው ነገር ቢኖር ጭልፊትም ትኑር አሞራም ትኑር ነው፡፡›› ቄሱ ለመሄድ ተነሱ፡፡
‹‹አዝናለሁ›› አለ ወጣቱ ርዕሰ መምህር፡፡ ‹‹ግን ትምህርት ቤቱ መተላለፊያ አይሆንም፡፡ ከሕጋችን ጋር አይሄድም፡፡ ሌላ መንገድ የትምህርት ቤታችንን ግቢ ሳይነካ ብትሰሩ የሚሻል ይመስለኛል፡፡ መንገዱን ለመስራትም ልጆችም ልንሰጣችሁ እንችላለን፡፡ ለጥንቶቹ አባቶቻችሁ ተቀያሪ መንገዱ ብዙ ያስቸግራቸዋል ብዬ አላስብም፡፡››
‹‹የምለው ሌላ ነገር የለኝም›› አሉ ሽማግሌው ቄስ እውጭ ሆነው፡፡
ከሁለት ቀናት በኋላ በሰፈሩ የነበረች አንዲት ወጣት ሴት በወሊድ ምክንያት ሞተች፡፡ ወዲያውኑም አዋቂ ተጠይቆ በአጥሩ መታጠር የተሰደቡትን የጥንት አባቶች ለማስታገስ ከበድ ያለ መስዋዕት እንደሚያስፈልግ ተናገረ፡፡
በማግስቱ ጠዋት ኦቢ ከመኝታው ሲነሳ የሰራው ነገር ሁሉ ፈራርሶ አገኘው፡፡ የሚያማምሩት የአበባ መደቦች ወድመዋል፤ ይህም ደግሞ በአጨቃጫቂዋ መንገድ አጠገብ ብቻ ሳይሆን በግቢው በአጠቃላይ ነበር፤ አበቦቹ ተረጋግጠው ተበላሽተዋል፤ ከትምህርት ቤቱ ህንጻዎችም አንዱ ፈርሷል… በዚያች ዕለት ነጩ ተቆጣጣሪ ትምህርት ቤቱን ለመገምገም መጥቶ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ሁኔታ ላይ መጥፎ ማስታወሻ ለበላይ አካላት ጻፈ፡፡ በተለይም ‹‹በአብዛኛው ከአዲሱ ርዕሰ መምህር አቅጣጫውን የሳተ ወኔ የሚመነጭ በትምህርት ቤቱና በመንደርተኞቹ መካከል እያቆጠቆጠ ያለ የጎሳ ጦርነት የሚመስል ሁኔታ›› እንዳለ አጽንዖት ሰጥቶ ነበር የጻፈው፡፡
ለአስተያየትዎ: mezemirgirma@gmail.com, mezemir@yahoo.com

ሰኞ 20 ጁላይ 2015

Cave Guard

Teshome Hailegnaw, the guard of the cave, explains its history. Location - Sasit, 90 kms from Debre Birhan. Promoter- Mezemir Girma- mezemir@yahoo.com

Engidwasha Cave, 90 kms from Debre Birhan

This cave is the heritage we are proud of. To find out more follow us at Segenet Ethiopia on fb and twitter!

ዓርብ 3 ጁላይ 2015

አርበኛዋ ግራር

የጉዞ ማስታወሻ በመዘምር ግርማ mezemir@yahoo.com ሚያዝያ 27፣ 2007 ዓ.ም. ሁለት መምህራን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማሀበር ወደተመሰረተበት ስፍራ ተጉዘን ነበር፡፡ ጉዟችን በመስሪያ ቤታችን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መኪና ሊሆን ቢታሰብም መኪኖቹ በሌላ ስራ በመያዛቸው በህዝብ ትራንስፖርት እንድንጓዝ ሆነ፡፡ አምና ሰባት ሆነን ወደ ስፍራው ስንጓዝ የገጠመን በየደቂቃው የሚበላሽ መኪና እና ስንመለስም የነበረችው መኪና ውስጥ የምትወልድ ሴት ዓይነት ያልታሰበ ነገር ስላላጋጠመን የዘንድሮው ጉዟችን የተሻለ ነበር፡፡ የጉዟችን ዓላማም በበዓሉ አከባበር ላይ መሳተፍና የስፍራውን ታሪክ መጻፍ ነበር፡፡ ከደብረ ብርሃን እስከ ጣርማበር ባለው 50 ኪሎሜትር አስፋልት ሸለቆውን እየቃኘን ሄድን፡፡ ጣርማበር ከተማ ስንደርስ መኪናችን ውስጥ የምግብና ፍራፍሬ ሻጮች አጥለቀለቁን፡፡ ‹‹ጦስኝ፣ ቆሎ፣ ኩኪስ፣ አገዳ፣ ሙዝ›› ሲሉ ለጆሮ እንደሙዚቃ ይጥማሉ፡፡ ከዚያም 22 ኪሎሜትሩን ፒስታ መንገድ ቁልቁል በስተ ምዕራብ ሰላድንጋይ ድረስ መንገጫገጭ ግድ ይላል:: እዚያች ታሪካዊ ከተማ ሰላድንጋይ ላይ ቆም ብሎ አጼ ምንሊክ የቆረቆሩት የቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን እና የቅድም አያታቸው የልዕልት ዘነበወርቅ ሰገነት በከተማው ዳርቻ ጎን ለጎን ለፍልሚያ የተዘጋጁ አውራ ዶሮዎች መስለው ተረተር ላይ ቆመው ተፋጠው ሲጠባበቁ እያዩ ዘመናዊው ምስራቅ ሆቴል በረንዳ ላይ ሻይ ቡና ማለት የቤተክህነትንና የቤተመንግስትን ተጠባብቆ ኑሮ ያስገነዝባል፡፡ የሞጃና ወደራ ወረዳ ትልቋ ከተማ የሆነችው ሰላድንጋይ ከተማ ከመቼውም በላይ ተውባ ጠበቀችን፡፡ ከመብራት እንጨቶች በአውራ መንገዱ አግድም ከዳር እዳር ረጃጅም የኢትዮጵያ ባንዲራ ሶስት ወይንም አራት ቦታዎች ላይ ተንጣሎ አየን፤ ፎቶም ተነሳን፡፡ ይህ ሁሉ ባንዲራና ድምቀት ግን የአርበኞች በዓልን ለማሰብ መስሏችሁ እንዳትሳሳቱ፡፡ የህዳሴው ግድብ ዋንጫ ወደ ወረዳው በማግስቱ ስለሚመጣ አቀባበል ለማድረግ ነው፡፡ ይህ የግድብ ዋንጫ በሚዞርባቸው ከተሞች ሁሉ ለቦንድ ቃል ይገባል - ይፈጸምማል! ሰላድንጋይ ከተማ ላይ በአንድ ቤት በር ላይ ሳልፍ ስለአርበኞች በሬድዮ ሲወራ ሰማሁ እንጅ ምንም የበዓል አከባበር በከተማዋ አላየሁም፡፡ በነገራችን ላይ እርስዎም ጓድ መንግስቱ ኃ/ማርያም እንዳሉት ‹‹ሰላድንጋይ ምንድነው?›› የሚሉ ከሆነ ግን ከተማዋ ያላትን ታሪክ ብቅ ብለው ይጎብኙ እልዎታለሁ፡፡ ወደ ሳሲት የሚወስድ መኪና በየሰዓቱ ስለማይጠፋ ጠብቆ መሳፈር ይቀጥላል ከዚህ በኋላ፡፡ ይችን የሳሲት 20 ኪሎሜትር መንገድ በእግራችን ስንትና ስንት ጊዜ ፉት እንዳልናት! መኪና ደግሞ ወደ ደብረ ብርሃን ተመላሿ ጠዋት ካመለጠችን ሰላድንጋይ ላይ ማደር ግድ ይል ነበር፡፡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአስር ዓመት በፊት አልነበረም፡፡ ስልክ ደግሞ አንድ የህዝብ ስልክ ቤት ነበረች፡፡ ውሃውም መጠነኛ ነበር፡፡ አሁን ግን እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ ከብሄራዊው ኬክ ጠርዝ ሞጃዎች ትንሽ እየላሱ ነው ለማለት እችላለሁ፡፡ ሞጃዎችን እኮ ጃንሆይ አሳደዋቸዋል፡፡ ልጆቻቸው መንግስቱ እና ግርማሜ ነዋይ ‹አስቀይመዋቸው› ሞጃ የተባለን ሁሉ ከስራ አባረዋል፡፡ ያ አልፏል፤ አሁን ግን ከመንግስት ጋር ታርቀዋል፡፡ ለማናቸውም ሳሲት የሚሄደው መኪና ላይ እኔ፤ ሳለአምላክ ጥላሁን እና እሙዬ አረጋ (ጊፍቲ እኔ እንደምጠራት) (ይቺ ልጅ አምና አብራን ለአርበኞች በዓል ስትሄድ የአባቷን የጋሼ አረጋን ሞት በስልክ አርድተዋት እነዚህም አባቶቼ ናቸው ብላ አርበኞቹን አይታና ለልጆቻቸው ትምህርት ቤት እንዲቀመጥ የገዛችላቸውን የመጻሕፍት ስጦታ ሰጥታ ነበር የመጣችው) ተሳፈርን፡፡ የሳሲትን መንገድ ሳጋምሰው ከሰላድንጋይ ወደ ሳሲት በእግሩ የሚወርድ አንድ ጉብል ተቀኘ ያሏት ግጥም ትዝ አለችኝ፡፡ እነሆ- ሰላድንጋይ ውዬ ባር ሜዳ መሸብኝ ላጨርሽው ፍቅር ምነው ጀመርሽብኝ! ከሰላድንጋይ ወደ ሳሲት ስንሄድ ያገኘሁት የወረዳው ሰራተኛና የትውልድ ስፍራው አንዲት ግራርን አልፎ ጋውና ላይ የሆነው አቶ ሶሎሞን አበበ ‹‹ይህ በዓል አርበኞች አገሪቷን ከጠላት ወረራ ለመከላከል ያደረጉትን ተጋድሎ ለማስታወስ ሲባል የሚከበር በዓል ነው፡፡ ሰራተኛው እንጅ ተማሪው እና አርሶ አደሩ የምን በዓል እንደሆነ አያውቁትም - ሚዲያ ስለማይከታተሉ፡፡ መድረክ በየቀበሌው እና በየወረዳው ቢዘጋጅ ብዙ ሰው ያውቀዋል፡፡ በአርበኞቻችን ኩራት ይሰማኛል፡፡ ስለበዓሉ ግን በትምህርት ቤት ምንም የተማርኩት ነገር አልነበረም፡፡›› በመኪናችን ውስጥ ለቀስተኞች ተቀምጠዋል፡፡ የየራሱን መንገድ የሚሄደውን ያደርሳል ሹፌሩም፡፡ ሳሲት ደርሰን በደጓ በወይዘሮ ዘነበች አስፋው ቤት ስንጋበዝ ይህችን ተዘውታሪ ግጥም አስታወስኩ - ኧረ ሳሲት ሳሲት ትንሿ ከተማ የሚበላው ስንዴ ጉዝጓዙ ቄጠማ ! ከዚች ከተማችን ወደ መዳረሻችን የሚወስደን መኪና እስኪገኝ ቡና መጠጣትና ምሳ መብላት ያዝን ያውም ሁለት ቤት ገብተን፡፡ ‹‹በእግራችን አስር ኪሎሜትሩን እንሂድ›› ስል አብራን ያለችው ልጅ ‹‹አልችልም›› አለችና ቀረን፡፡ የአርበኞች መታሰቢያ የሆነው የግራር አምባ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አሰፋ አስታጥቄ ናቸው የዘንድሮ መርሃ ግብር አዘጋጅ፡፡ መሪነቱ ወደ ትምህርት ቤቱ መተላለፉ በዓሉ የወላጆች፣ የመምህራንና የተማሪዎች ስለሚሆን ቀጣይነቱን ያረጋግጣል፡፡ ከእርሳቸው ጋር ስልክ እየተደዋወልን እየመጣን እንደሆነ ነገርናቸው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ መብራት ጠፍቶ አድሮ የኔም ስልክ ዘግቶ ስለነበር በጓደኞቼ ስልክ ነበር የደወልኩላቸው፡፡ ከቤታችን ስንነሳና እርስ በእርስ ስንቀሳቀስም በአካል ሄደን ነበር እንጅ የስልክ ነገር ልይቶለት ነበር፡፡ ወደ ግራሯ ለመሄድ መኪና ስንፈልግም ኮንትራት 600 ብር ክፈሉ ተባልን፡፡ በዚህም ወቅት ከዘነበች ቤት ተሰናብተን ሄደን በታላቅ ወንድሜ ቤት ቡና እያስፈላን ስለነበረ መኪና ካልተገኘ እዚሁ ሰብሰብ ብለን እናክብር የሚል ሃሳብ ሰነዘርኩ፡፡ ከሳሲት ወደ አንዲት ግራር የሚወርዱ አምስት የሳሲት ነዋሪዎችም ስለነበሩ ነው እዚሁ እናክብረው ማለቴ፡፡ ህዝቡ መጀመሪያ የወላጆችን በዓል በግራር አምባ ትምህርት ቤት አክብሮ ወደ ግራሯ መጥቶ እየጠበቀን እንደሆነ በመስማታችን ከህዝቡ ጋር ለማክበር ወደ ግራሯ ለመሄድ ጓጉተን ነበር፡፡ ግራር አምባ ትምህርት ቤት የወላጆች በዓል ሚያዝያ 27 መከበሩ አያኮራዎትም? እውነትም የአርበኞች መታሰቢያ ትምህርት ቤት! በመሆኑም አንድ የወረዳው የስራ ሃላፊ በስልክ ደውለው መኪና አስመጥተውልን ፒክ አፕዋ ላይ ከውስጥም ከላይም ሆነን ወደ ስፍራው አመራን፡፡ የእለቱ ልዩ እንግዳና ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ስፍራውን ያየው የበላይ ዘለቀ ያገር ልጅ መምህር ሳለአምላክ ጥላሁን በሳሲት የቤቶቹ መጠጋጋትና የህዝቡ መጎሳቆል አሳዝኖታል፤ አስገርሞትማል፡፡ እኔ ግን እዚያው ተወልጄ ስላደግሁ ምንም አልመሰለኝም ነበር፡፡ ወደ አንዲት ግራር በሚወስደው መንገድ ስንሄድ የገጠር ቤቶችንና የእርሻ ማሳዎችን እንዲሁም አልፎ አልፎ የሚታዩ የግራር ዛፎችን እያየን ነበር፡፡ የአማራ ክልል ኤፍ ኤም ባለፈው ዓመት በአንዲት ግራር ተገኝቶ የዘገበውን ዘገባ ዘንድሮ በድጋሚ እያቀረበው ኖሮ በመኪናው በተከፈተው ራድዮ ስናደምጠው ወረድን፡፡ ድንቅ ዝግጅት ነበር፡፡ በዚህ ዓመት አቶ ሕላዌ ዮሴፍና አቶ አዲሱ ለገሰም ግራሯን እንደጎበኙ ሹፌራችን ኤርሚያስ በጨዋታ መሃል ነግሮኛል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ባለውቃቢ ወፋ ነገሰን ለመጠየቅ ከሃገራችን የተለያዩ ክፍለ ሃገራት የሚመጡት ባለጉዳዮች በእግራቸው ወደ እርሳቸው መንደር ለመሄድ መንገዱን ሲጠይቁ የሳሲት ነዋሪ ‹‹ዝም ብላችሁ መኪና መንገዱን ተከትላችሁ ስትሄዱ አንድ ትልቅ ግራር ሜዳው ላይ ታገኛላችሁ፡፡ ከዚያ ወደ ቀኝ ታጥፋችሁ ትንሽ ሄዳችሁ እርሳቸው ቤት ትደርሳላችሁ፡፡›› የሚሏቸው ትዝ አለኝ፡፡ በእርግጥ ገንዘብ ለሚከፍል ተጓዥ መንገድ የሚያሳዩና ሻንጣ የሚሸከሙ ወጣቶች ሳሲት አይጠፉም ነበር፡፡ ይህ የሚሆነው የመሬሬው ጥቁር ጭቃ መኪና በማያስገባበት በክረምት ወቅት እንጅ በበጋማ በጭነት መኪና ተጭኖ የሚሄደው ሰው በአንድ ጊዜ ወደ መቶ ይጠጋ ነበር፡፡ አሁን ሳስበው የሚያናድደኝ አንድ ከተሜ በልጅነቴ አይቻለሁ፡፡ ተስተናግዶ ሲጨርስ ወፋ ነገሰ ቤት አቅራቢያ ያሉ አርሶ አደሮችን ‹‹ታምሜያለሁና በቃሬዛ ተሸክማችሁ ሳሲት ድረስ አውጡኝ ፤ ባይሆን ገንዘብ እከፍላችኋለሁ›› ብሎ ተሸክመው ይዘውት መጥተው ገንዘቡን ከፍሎ እየሳቀ ከተሸከሙበት አልጋ ሲወርድ አይቻለሁ፡፡ ቅኝ ገዥዎች የአፍሪካ ህዝብ ላይ እንዳደረጉት ያለ ለህዝቡ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ድርጊት ነው፡፡ አሁን ወደ አርበኞች በዓላችን እንመለስ፡፡ ጥላሁን ጣሰው የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ የተመሰረተው ዲሞክራሲያዊ ማሕበር የሆነው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የተቋቋመበት አንዱ ምክንያት ለአርበኛው ድርጅት ማስፈለጉ ግልጽ በመሆኑ ነበር ይሉናል፡፡ የማህበር ማቋቋሙ ሂደት ግን ፈተናዎች እንደነበሩበት ታሪክ ያወሳል፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በአርበኞች መካከል አለመስማማት፣ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ማለት እና ወደ ጠላት መክዳት ይጠቀሳሉ፡፡ ‹‹የነጻነታችን መሰረት አንዲት ግራር›› በሚል ርዕስ የሞጃና ወደራ ባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ያዘጋጀው ግንቦት 2007 የተዘጋጀ ያልታተመ ጽሑፍ እንደሚያትተው ‹‹የሚንቀሳቀሰውን የወራሪ ጦር መደምሰስ የሚያስችል ሌላ የጦር ስልት ለመንደፍ በባላምባራስ በሻህ ኃይሌ አመራር ሰጭነት በየዱር ገደሉ የነበሩት አርበኞች ያስከተሉትን ጦር በመያዝ ጥር 1፣ 1931 በእንግድ ዋሻ ቀበሌ፣ አንቀላፊኝ ሜዳ፣ አንዲት ግራር ስር እንዲሰበሰቡ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡ በትዕዛዙ መሰረት ሁሉም የጦር አለቆች ያስከተሉትን ጦር በመያዝ በተባለው ቦታ እንዲገኙ ተደረገ፡፡ ወደ ስፍራው ከመጡት መካከል ዋና ዋናዎቹና ይመሩት የነበረው የጦር ሃይል ብዛት ራስ አበበ አረጋይ - 1600 ጦር ልጅ ግዛቸው ኃይሌ - 800 ጦር ባላምባራስ በሻህ ኃይሌ - 600 ጦር ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ - 600 ጦር ፊታውራሪ ታደሰ በላይነህ - 600 ጦር ልጅ ከፈለው ወልደጻድቅ - 500 ጦር አቶ ፀሐይ እንቁ ሥላሴ - 750 ጦር ራስ መስፍን ስለሺ 1600 - ጦር ›› (3) ነበር፡፡ ሰነዱ ሲቀጥልም ‹‹እነዚህን የነጻነት አባት አርበኞችን ሊዘክር የሚችል ሃውልት በቦታው ተሰርቶ ጥር 1፣ 2002 ዓ.ም. በጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ ተመርቋል፡፡›› (4) ይለናል፡፡ አርበኞች የተሰባሰቡባት የሰፊው ሜዳ ጌጥ የነበረችውን አንዲት ግራር ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት በ1990 የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ሲሆን አጥር የነበራትም ይመስለኛል ያኔ ሳያት፡፡ አድባር ነበር የመሰለችኝ፡፡ ታሪኳን አሁን ነው እየተረዳሁት የመጣሁት፡፡ አሁን ግን ነሐሴ 6 በጣለው መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ምክንያት መብረቅ መትቷት ወድቃለች፤ ህዝቡም እንደሰው ቁርባን እንዳቆረበላት እና ውለታዋን እንዳልዘነጋ ይታያል፡፡ ግራሯ ወዴት ወገን ወደቀች፤ እንዴት ወደቀች እየተባለ የራሱ የሆነ ትንታኔ በአካባቢው ነዋሪዎች ተሰጥቷል፡፡ አንድ ትልቅ ሰውም ይወድቃል የሚል ስጋት ጥሎባቸው ነበር፡፡ የቀድሞው የሰሜን ሸዋ አርበኞች ሊቀመንበር ባላምባራስ በየነ ይህ ስፍራ አርበኞች ማህበር በመመስረት ትግሉን ያጠናከሩበት የቃል ኪዳን ቦታ ነው ይሉናል፡፡ አርበኞች ከአራት ኪሎው ዋና ጽ/ቤታቸው ለመታሰቢያ በአቅራቢያው የተመሰረተውን የግራር አምባ ትምህርት ቤትንም ያግዛሉ፡፡ አዲሱ ሊቀመንበራቸው ልጅ ዳንኤል መስፍን ስለሺም ትምህርት ቤቱ የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች በራሳቸው ወጭ በከፊል አሟልተዋል፡፡ እንግዲህ በዚህ ስፍራ የምናስባቸውን አርበኞች ተግባር ምንነት ለመረዳት አንድ ስማቸውን ለመጥቀስ ያልፈለጉ መምህርን አርበኛ ማለት ምን ማለት ነው? ብዬ ጠይቄያቸው ‹‹አርበኛ ማለት ትልቅ ጥልቅ የሃገር እና የወገን ፍቅር ያለው፣ የሃገሩን እና የወገኑን ጉዳት ማየት የማይሻ እና ለዚህም ማሳያ የሚሆን ውድ የሆነውን የህይወት መስዋዕትነት እስከመስጠት ድረስ ወደኋላ የማይል ነው፡፡›› ብለውኛል፡፡ ለእርስዎስ አርበኛ ምንድነው? የአርበኞች ቀንን እንዴት ያከብሩታል ብዬ ላቀረብኩት ጥያቄ እኝሁ መምህር ሲመልሱልኝ ‹‹በውስጤ ነው የማከብረው፤ አከባበራችን ይለያያል፡፡ የማስበው ያን ያክል መስዋዕትነት ለማድረግ የነበራቸው የህዝብና የሃገር ፍቅር ስሜት ምናልባትም አሁን ካለው ትውልድ ጋር በማወዳደደር ዛሬስ ያለው ትውልድ ይሄን ትልቅ የህዝብ እና የሃገር ፍቅር ስሜት ይኖረዋል ወይስ ጠፍቷል የሚል አከባበር ነው፤ ስለሚያሳስበኝ ነው፡፡›› እኝህ መምህር ወደ ስፍራው ሳንሄድ ከሰጡኝ ከዚህ ምላሽ እንደምንረዳው በህሊናው አርበኞችን የሚያስብ እንዳለ ነው፡፡ በዓሉን በመሰባሰብ የሚያከብሩት ሰዎችስ እንዴት ያከብራሉ የሚለውን እስኪ እንይ! ግራሯ በስፍራው ወድቃ ማንም ሳይነካት እንዳለች ይሄው አምስተኛ አመቷን ልጽደፍን ነው፡፡ ግራሯ ወድቃ ባችበት ስፍራ ስንደርስ ህዝቡ ተሰባስቦ ይፎክርና ይሸልል ነበር፡፡ በስፍራ የተገኙት ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ተጋባዥ የአካባቢው ነዋሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ እኔና ጓደኛዬ መምህር ሳለአምላክም የተሰማንን ስሜትና ህዝቡ ስላዘጋጀው ዝግጅት ያለንን አክብሮት ገለጽን፡፡ አንዲት ሰላድንጋይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምትማር ወጣት የላከችው ግጥም በመምህር ሻውል ማሞ ሲነበብ ስሰማ የወጣቱን ተሳትፎና ፍላጎት አደነቅሁ፡፡ ከግጥሟ ሁለት መስመር ብንወስድ ‹‹ኑ ታምሯን እዩ የሸዋን አፈር አብቅላለችና አንዲቷን ግራር፡፡›› ይላል፡፡ ድንቅ እይታ! ለግራር አምባ ትምህርት ቤት በስጦታነት ይዤ የሄድኩትን አጀንዳ መያዣ መዝገብ በስነ ስርዓቱ ላይ ሳበረክት አንድ ሽማግሌ የሚከተለውን መልዕክት ጽፈው ሰጡኝ፡፡ ‹‹ለመምህር መዘምር ግርማ፣ በረከቱ በአርበኛው ሰብሳቢ በኩል ለተረካቢው ቢሰጥ›› ይል ነበር፡፡ ለአርበኞና ለማህበራቸው ስጦታ ይዤ ባለመሄዴ ተጸጸትኩ፡፡ በሌላ ቀንም ለመውሰድ ቃል ገባሁ፡፡ በወረዳው 602 አባላት ያሉት የአርበኞች ማህበር ነው ያለው፡፡ ከስጦታ ወሬ ሳንወጣ ባለፈው ዓመት ለግራር አምባ ትምህርት ቤት ያሰባሰብንውን መጽሃፍ ስንለግስ የሌሎቹ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ‹‹ሁሉንም ለግራር አምባ መስጠታችሁ ምነው?›› ብለውኝ ስለነበር መጽሐፍ ለሌሎቹም ወደፊት የማሰባሰብ የቤት ስራ አለብኝ፡፡ ሌላ የደረሰኝ ማስታወሻ የሚከተለው ነው፡፡ ‹‹ማሳሰቢያ ሰጭ አቶ አወቀ አክሊሉ ስሆን በዚች አንዲት ግራር እንድትተካ አንድ እግር ወርካ ተክዬ እየተንከባከብኩ ስገኝ አጽድቄ እያለሁ ሰዎች ነቅለውብኝ ሞራኔ ከስሮ እገኛለሁ፡፡›› ይላል፡፡ ባለፈው ዓመት አሁን ወድቃ በምትገኘው ግራር ምትክ እንዲተክሉ የቤት ስራ የወሰዱት አባት ነበሩ ይህን መልዕክት የላኩልኝ፡፡ ጥረታቸው አለመሳካቱ ያሳዝናል፡፡ አርበኞቹ የሚታወሱበት እንደ ህዝቡ ጥያቄ አንድ ሐኪም ቤት ወይንም ሌላ ለሕዝቡ የሚጠቅም ተቋም ቢቋቋም ግን ከዛፍ የበለጠ ማስታወሻ ይሆናል እለላሁ፡፡ አርበኞች በስፍራው በ1931 ዓ.ም. በጦርነት ወቅት ሆነው መደራጀታቸውን ሁሌም አደንቃለሁ፡፡ ያልተደራጀ ሕዝብ ምንም የረባ ነገር ላይሰራ ይችላል ብዬ ስለማስብ፡፡ አባቶች በበዓሉ እለት ስለአርበኞች ማህበር አመሰራረት የሚያውቁትን ነግረውናል፡፡ ሰነዳቸውን ካጸደቁ በኋላ 200 ዓመት ያህል ዕድሜ ባላትና ሰዎች ሲጣሉ በሚታረቁባት በዚህች ታሪካዊ ግራር ላይ ያረዷቸውን በጎች ስጋ ሰቅለው እየቆረጡ እየበሉ ተማማሉ ይሉናል፡፡ የአርበቻችን የትግል ህይወት ምን ይመስል እንደነበርና በስፍራው ተሰባስበው በሚመክሩበት ሰሞን ዋና ዋናዎቹ አርበኞች እነማን ቤት እንዳረፉ ጭምር ተነግሮናል፡፡ ቄስ ለማ ገብረመስቀል ባቀረቡት ግጥምና መልዕክት ማጠቃለያ ላይ የሚከተለውን ብለው ነበር፡፡ ‹‹ክቡራን እንግዶች፣ ትውልድ ያልፋል፤ ስም ግን ከመቃብር በላይ ስለሚቆይ ጊዜውን ጠብቆ በኢትዮጵያ ላይ ፈተና የሚገጥም በመሆኑ ወደፊትም በትጋትና በወኔ መቋቋም እንዲቻል የአርበኞቹን ተተኪዎች ልጆች እንድታስቡን አሳስባችኋለሁ፡፡›› የተዘጋጀውን ዳቦና ጠላ ከተጋበዝን በኋላ እና እየፈረሰች ባለችው ሐውልት አጠገብ ፎቶ ከተነሳን በኋላ ቸኩለን ስለነበር እና ዝናብም ስለጀመረ ወደ ሳሲት የመልስ ጉዞ ጀመርን፡፡ በዚህን ጊዜ አንድ አባት አርበኛ እየሮጡ መኪናችንን ሲከተሉ አይተን አቁመን አሳፍረናቸው ይዘናቸው ስንሄድ የሃምሳ አለቃ በላቸው እንደሚባሉና የሞጃ አርበኞች ሊቀመንበር አንደሆኑ ነገሩን፡፡ ለበዓሉ ሲሉ ይህን ሁሉ መንገድ በእግራቸው ሳይሆን አይቀርም የወረዱት! በበዓሉ ላይ ብዙ የማይረሳ ትዝታ ቢኖረኝም አሁን ስለበዓሉ ያናገርኳቸው ሰዎች ወደሰጡኝ ምላሽ እንሄዳለን፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ አክሊሉ ይርጉ ‹‹አንዲት ግራርን ካሁን በፊትም አውቃታለሁ፡፡ ስፍራው ጀግኖች አርበኞቻችን ማህበራቸውን ያቋቋሙበት እንደሆነም አውቃለሁ፡፡ የሰሜን ሸዋው የአርበኞች ማህበርም ለማስተዋወቅ ጥረት እያደረገ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ማስተዋወቁ ደግሞ ታሪኩ ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተዋወቅና እንዲቀጥል እንዲሁም ስለስፍራው ዕውቀት እንዲኖረን ያግዛል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያንን በመዋጋት አባት አርበኞቻችን ያደረጉትን ተጋድሎ በተገቢው መንገድ ለመዘከር ያስችለናል፡፡ ቦታውን የቱሪስት መስህብ ለማድረግና ለማስተዋወቅ ኮሌጃችንም ሆነ ዩኒቨርሲቲያችን የጋራ ሃላፊነት አለባቸው፡፡›› እሙዬ አረጋ (ጊፍቲ) ስለ በዓሉ አከባበር በሰጠችኝ አስተያየት ‹‹የአምናው አከባበር አሪፍ ነበር - አስበውበት ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን የአርበኞች ሽለላ እንኳን አነስተኛ ነው፡፡ የዘንድሮው ምንም አልታሰበበትም፡፡ ወይ ከምርጫው ወይ ከዋንጫው ሊሆን ይችላል፡፡ አምና በዛ ብለን ነበር የመጣንው፡፡ በእርግጥ ዘንድሮም ትምህርት ቤት አዘጋጅተው ሊሆን ይችላል እኛ ቸኩለን ዝናብም ሆኖ ነው እንጅ፡፡ አምና የልጁ መወለድ ነው ያስመሸን፡፡ የቀይት ጤና ጣቢያን አለፍ ብለን ሲወለድ ደብረ ብርሃን ከምንሄድ ተብሎ ነው የተመለስንው እና ልጁን ሃኪሞች መኪና አዋለዱ፡፡ የልጁ ስም ግን ማን ሆኖ ይሆን? አምና አብረውን በዓሉን ግራሯ ጋ ያከበሩት አራት አባቶች መሞታቸው አሳዝኖኛል፡፡ እኛ ፎካሪው ሰውዬ ሞተው እንዳይሆን …›› ብላኛለች፡፡ እኝህ ፎካሪ ባለፈው ዓመት ‹‹ራያው ከፌ አዳባይ ገባ እንደ ወለፌ ቦንብ አይሮፕላን ቲጥል በተራ መትረየስ ቲጮህ መድፍ ቲያጓራ የጎበራ ልጅ ይደባለቃል ተነጭ ጋራ!›› ብለው ጎራዴ ይዘው ሲፎክሩ የገባኝን ያህል ተረድቼ ግማሹ አማርኛቸው ስለከበደኝ ራሴን ከባህሌና ቋንቋዬ ምን ያህል እንደራቅሁ እንድታዘብ የረዱኝ ናቸው፡፡ እኝህ የኋላሸት የተባሉ ሽማግሌ አሁንም በህይወት እንዳሉ ከመርሃ ግብሩ መጠናቀቅ በኋላ በሌላ ቀን ሰው ጠይቄ አረጋግጫለሁ፡፡ የፖለቲካል ሳይንስና የፍልስፍና መምህሩን ለማ ሚዴቅሳንም በጉዳዩ ላይ አነጋግሬያቸው ነበር፡፡ ለእርሳቸው ‹‹ጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን የእነርሱ የሆነ አንድ ገናና አስተሳሰብ ብቻ ሃገሪቱ የምትመራበት ይሁን ብሎ ማሰብ በጣም ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ምንጫቸው ከምንም ይሁን ከምን የተለያዩ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ የሚችል፣ የሚጠይቅ፣ በህግ የተሰጠውንም ነጻ አስተሳሰቦችን የመሰንዘር መብቱን የሚጠቀም ትውልድ ሊፈጠር ይገባል፡፡ የራስን ቁሳዊ፣ መንፈሳዊና ታሪካዊ እሴቶች የማያከብር፣ የማይንከባከብ እና የማያሳድግ ትውልድ ብዙም አያድግም፡፡ ‹‹ይሄ ታሪክ የመላው ኢትዮጵያውያን ታሪክ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት የጋራ በሆኑ ታሪካዊ ቅርሶቻችን ላይ ሁላችንም ልንሰራ ይገባል፡፡ ያከባበር ስራዓቱ ሰፋ ባለና በደመቀ ሁኔታ ቢከበር ወጣቱ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲያስብ እና ሃላፊነቱን እንዲወጣ ያግዝ ነበር፡፡ ነገር ግን ያ አለመሆኑ ነገሮች የበለጠ የከፉ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለን አዲስ ፌደራል ስርዓት ነው፡፡ ሰዎች በፊት ሲሰማቸው የነበረው ብሔራዊ ስሜት እየተሸረሸረ ክልላዊነት እያየለ መጥቷል፡፡ እና ይህን ባላንስ ያደርግ (ያመጣጥን) ነበር፡፡ ምን ያህል የሚያምር ታሪክ እንደነበረን፣ ከኛም አልፎ ለጥቁሮች አርዓያ የሆነ ታሪክ እንደነበረን ያስታውስ ነበር፤ ሊሰራበት ይገባ ነበር፡፡ ‹‹ትውልድ ያልፋል ሃገር ግን ቋሚ ነው፤ ጠንካራና ያደገች አገር ለመመስረት የአንድነት ጠንካራ መሰረት ሊኖር ይገባል፡፡ አሁን ያለው አገር ያለመስዋዕትነት ያገኘነው አይደለም፡፡ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ ወደፊትም ቢሆን አንድ ሃገር ከውስጥም ሆነ ከውጭ አደጋ አይገጥማትም ማለት አይደለም፡፡ ይችን አገር በነበረችበት የጥንካሬ መሰረት ላይ ለማስቀመጥና እየጠነከረች እንድትሄድ ለማድረግ እንዲህ አይነት በዓላት ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ፖለቲካዊ ይዘት ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ይዘትም አላቸው፡፡ በተጨማሪም ብዙ ፋይዳ አላቸው፡፡ የታሪካ አጋጣሚ ሆኖ በወቅቱ የነበሩት የፖለቲካ ልሂቃን ከሰሜን ሸዋ የወጡ ስለነበሩ ይህ የታሪክ መታሰቢያ እዚህ መደረጉ የሚከፋ አይደለም፡፡ ነገር ግን በሌሎች ቦታዎችም ያሉ ወጣቶችም የጋራ የሚያደርጋቸው በዓል ስለሆነ በዓሉ ሁሉም ቦታ ላይ ሊከበር ይገባዋል፡፡›› የአርበኞች መሪዎች በአሁኑ ወቅት የአሁኑ ትውልድ ድህነትን መዋጋት ነው ያለበት ሌላ ወራሪ የለብንም በሚሉት ላይ ለጠየቅኋቸው ጥያቄ ሲመልሱ መምህር ለማ የሚከተለውን ብለዋል፡፡ ‹‹ለአንድ ሃገር ጠላቱ ድህነት ብቻ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ችግሩ ፈርጀ ብዙ ነው፡፡ ሁሉንም ችግሮች በጋራ ለመቋቋም የሚያስችለን ስነ ልቦና መፍጠር አለብን፡፡ እንደዚህ ዓይነት ታሪካዊ ክስተቶችን ማውሳት ደግሞ ለዚያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ›› ሌላው ወደስፍራው አብሮኝ የተጓዘው መምህር ሳለአምላክ ደግሞ ‹‹በቦታው የተገኘነው የአርበኞች አባቶቻችንን በዓል ለማክበር ነው፡፡ አርበኞች አባቶቻችን አገራችንን ባህሏን፣ እምነቷን ሃብቷን ጠብቀውልናል፡፡ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ግን ያነበራቸውን ብዙ ነገር አጥተዋል፡፡ የነርሱን ውለታ መክፈል የምንችለው በዓሉን በየዓመቱ በማክበር ነው፡፡ በበዓሉ ላይ ተማሪዎችም አባቶችም ነበሩ፤ የመንግስት ተወካዮች ግን አልነበሩም፤ በዚህ ትንሽ ቅር ተሰኝቻለሁ፡፡ ለበዓሉ ትኩረት እንዳላደረጉ ነው፡፡ እንዲያውም ታስታውስ እንደሆነ ሰላድንጋይ እንደደረስን ከተማዋ በጣም አሸብርቃ ነበር በባንዲራ፡፡ እና እኛ ያሰብነው ምንድነው በዓሉ እየተከበረ ነው በሚል ነበር፡፡ ነገር ግን በኋላ የተረዳነው ነገር የአባይን ዋንጫ ለመቀበል እየተዘጋጁ መሆኑንና ስለበዓሉ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ጠይቀናቸው ስለበዓሉ ምንም ዓይነት ነገር አልሰጡንም፡፡ በቦታውም ስንደርስ የመንግስት ተወካይ አልነበረም፡፡ ይህ የሚሳየው በመንግስት ትኩረት እንዳልተሰጠው ነው፡፡ ለወደፊቱ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ይሄ በዓል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ተምሳሌት ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ አካባቢው የመሰረተ ልማት ችግር አለበት፡፡ ትምህርት ቤት ይከፈት ብዬ ስጠይቅ አርበኞች ምንድነው ያሉ ሆስፒታል ቢሆንልን ነው፡፡ እና የጤናም ችግር እንዳለ ያሳያል፡፡ እንደሚታወቀው እድሜህ በገፋ ቁጥር በሽተኛ ትሆናለህ፡፡ እንክብካቤ ያስፈልግሃል፤ ርቀት ሄደህ መታከም አትችልም፡፡ ገቢም ላይኖርህ ይችላል፡፡ እና በዚያ አካባቢ ለአርበኞች ሆስፒታል እንዲቋቋምላቸው ለመጠየቅ እንደተዘጋጀን አስታውሳለሁ፡፡ ሳሲትን ከጠበቅኋት በታች ነው ያገኘኋት፡፡ ምን አልባትም የኪስ ከተማ ስለሆነች ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡ መንገዱ አስፋልት አልሆነም ከዋናው መንገድ ገባ ስትል፡፡ ምንም እንኳን ምቹ ቢሆንም አስፋልት ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ በክረምት ግን ጭቃ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ እና በጣም ግሎባላይዜሽን (ሉላዊነት) የገባባት ከተማ አትመስልም፤ በጣም ትንሽዬ ከተማ ናት፤ ደህና ካፌ እንኳን የለባትም፤ ገብተን ቡና ልንጠጣ ሻይ አዝዤ ቡና ብቻ ነው ያለው አለችኝ፡፡ ህዝቡም ቢሆን ምን ያህል በድህነት አረንቋ ውስጥ ያለ ህዝብ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ እኔ ስፍራው ላይ ተገኝቼ በዓሉን በማበሬ ኩራት ተሰምቶኛል፡፡ ለወደፊቱም ሌሎችንም አሳምነን መንግስትም ያመነበት አይመስልም መንግስትም ህብረተሰቡን ቀስቅሶ እንድናከብር እመኛለሁ፡፡ ይህ በዓል እንደሚታቀው ትልቅ በዓል ነው፡፡ እዚያ ግራር አለች አባቶቻችን ጣሊያንን ለመዋጋት መጀመሪያ የተደራጁባት፤ ይሄ ነው የምትለው እንኳን ሐውልት አልቆመለትም፤ ይሄ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ይሄ የውጭ ወራሪን ያሸነፍንበት በዓል ነው፡፡ እና በግሌ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ወደፊትም ህጻናቱ እንዳቀረቡልን ስነጽሑፍ አዘጋጅተን ሰዎችንም ይዘን ተደራጅተን እናከብረዋለን ብዬ አስባለሁ፡፡ ›› መንግስት ለአርበኞች ማህበር መጠናከሪያ ገንዘብ እና ሌላም ድጋፍ በማድረግ እንደሚያግዛቸው ሁሉ ይህን በዓል በድምቀት በማክበር፣ የቀድሞው የመቶ ብር ኖት ላይ የነበረውን የአርበኛ ምስል መልሶ በማተም እና በሌሎችም አርበኞችን በሚያስታውሱ ተግባራት እንዲሳተፍ አሳስባለሁ፡፡ አስተያየትዎንም ይጻፉልኝ፡፡ እስኪ በነዚህ ፉካሮዎች እንሰናበት፡፡ ግን ለመጭው ዓመት ክብረ በዓል እንዳትቀሩ! አደራ በምድር አደራ በሰማይ!!! እንበለውና ጉልበት ጉልበቱን እያነከሰ ጨካኙ ጣሊያን ይውጣ ዳገቱን፡፡ የኢትዮጵያ ጀግኖች እኛው መጡ አይናቸው ይመስላል መዳኒት የጠጡ እንደ ሰደድ እሳት እየገላመጡ ለጎጃም ንገሩ ለወሎ ንገሩ ያ ጨካኙ ጣሊያን ተመልሶ ሄደ በመጣበት እግሩ፡፡ ራያ ከፈለው አይምጣ ይቅር ጣሊያንን ገደለው አቤት አቤት ሲል፡፡ ዋቢ ጽሑፎች እና ቃለ ምልልሶች ‹‹ሪፖርተር›› Adwa victory by gallant Ethiopian warriors. 05/03/2014 Robert Wren’s article on www.adefris.info (this site is currentlu suspended) ተድላ ዘዮሐንስ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ - ኢጣሊያ በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ማንኩሳ አሳታሚ፣ 2004 ዓ.ም. ‹‹አውራምባ ታይምስ››፣ 3ኛ አመት ቁ 113፣ ሚያዝያ 23/2002 ጥላሁን ጣሰው፣ አዳባይ፣ አዲስ አበባ፣ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት፣ 1975 ዓ.ም. ከባላምባራስ በየነ አደለኝ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፣ ሚያዝያ 10፣ 2006 ዓ.ም መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ሐይሉ ወልደታሪክ፣ መንግስቱ ለማ፣ አ.አ.ዩ. ፕሬስ፣ 2003 ዓ.ም. ፣ አ.አ - ኢትዮጵያ ከመምህራኑ ለማ ሚደቅሳ፣ ሳለአምላክ ጥላሁን፣ አክሊሉ ይርጉ እና ከወይዘሮ እሙዬ አረጋ ጋር በግንቦት 2007 የተደረጉ ቃለ ምልልሶች፡፡

ሰኞ 22 ጁን 2015

Read, Write, Apply and Transform Community!

The Road to Literacy On the afternoon of Friday, 19 June 2015, the head of the Department of English Language and Literature of Debre Birhan University informed me that I was one of the people invited to attend an NGO- meeting the following day. I was surprised to hear that because these days meetings and such educational opportunities have become the gathering places of the officials and their friends. I am a friend of none. The right person on the right occasion! I was told that I would brief the participants about the book club I co - founded and run and the benefit we got from the books Code Ethiopia, the organizer of the event, donated to the university. The department head, as he promised, phoned me in the evening and told me the place and time of the speaking event - Hiwot Hotel, at 8:30 AM, on Saturday. I went there the next morning just in time and found the place ready. “Punctuality is not always the pride of the princes if the world has to drag this country called Ethiopia along,” I thought at the meeting place just a few yards from the former Debre Birhan Palace, where the royal family stayed at when they visited Tegulet. The participants of the day’s event were late to arrive at this place. This is very Ethiopian as some three generations of guests were arriving late. Canadian Organization for Development through Education (CODE Ethiopia) Anyhow, outside a small hall on the fourth floor, posters describing Code Ethiopia’s activities and their outcomes were posted for early comers to devour till the other participants come. “Who we are CODE Ethiopia (CE) is a non-governmental and non-profit making organization working on the establishment of a ‘Literate Environment’ in Ethiopia through development of reading culture. Since its inception in 1994 it has established 97 community libraries in rural districts and trained librarians, library management committee members, supplementary book writers in local languages [and English],editors and local educational newsletter producers.” This NGO that supplied close to three million books to schools in this country for free believes, “If you can learn to read and write, you can learn to do, and be anything. That is the idea behind CODE.” http://www.codecan.org When the program started at 9:30 AM, 30 minutes after the actual schedule, it was Mr. Nema who opened the day’s speaking event by stating its objectives. He said that the generous Canadian philanthropist, Mr. William Bill Burt, visited Ethiopia in 2007 and promised to sponsor an award for a literary contest in Africa. He was motivated to start this after he noticed high school students spoke or understood no English. As a result, through CE he sponsors novels in English written by Ethiopians about Ethiopian life. Mr. Nema stated that CODE had to organize such speaking events in Debre Markos and Debre Birhan towns of the Amhara Regional State to get new writers as there were none involved in the contest from this vast region so far. I say to you, please let us publish Amhara Region! After him, an official from the North Shewa Zone gave a key note address, and afterwards two community librarians from the Oromia Regional State shared their rich experiences about their libraries supported by CE. In Sheno and Fiche towns they have reading weeks, girls’ clubs, paying readers and much more that promote reading and literacy. I wished this was realized at all corners of the nation. The Burt Award for African Literature (BAAL) Next was the time for the Burt Award Winning writers to share their experiences with reading, writing and publishing. In each round CE has been awarding winners and runners-up with modest prizes. The 6th round will be launched in September 2015 and any Ethiopian can involve. The novels that you write should target Ethiopian young adult readers in the age group 12 – 18. Daniel G, one of the winners and a lecturer in Electrical Engineering at Wollo University, had the following to say: Readers are benevolent. People become cruel because they don’t read. Today’s youth has no good understanding. They just discuss European football. This is because they don’t read. Regarding my writing experience, I used to hide, tear or burn what I wrote fearing that people find it. Now I have published thanks to the award. I include in my writing the stories I heard from people in my locality including the story of the shepherd who plays the flute and towards whom a leopard comes to enjoy the music. I had a shortage of books as a child. Kibrom the author of The Revelatoin and a PR practitioner said this: A generation that doesn’t read is a lost one. Reading shaped me. In lower grades, my father pledged to buy me a bike and I stood first. However, when he failed to fulfill that, I stood last. After that, I forgot learning and it was at another time I started to read. Knowledge and wisdom are found in books. WE PRAY TO GOD TO GIVE US FOOD. WE SHOULD ALSO PRAY TO HIM TO LET US READ. I have published 27 children’s books most of which are translations from Amharic into Tigrinya. Code opened my eyes to reading. It has brought readers and writers together. Both authors were asked questions including one that says what they would do with the manuscripts if they were not selected for the prize. They had a very good discussion with us. THE DIAMOND TEACHER When I checked the schedule for the day I found this: Orientation to students and teachers on inspiring students to read literature, 12:00 – 1:10 PM, Ato Messeret. I suspected that the presenter probably must be my former African Literature instructor at Addis Ababa University (AAU). Mr. Nema invited whom he called a diamond teacher at AAU to the stage. Mr. Messeret deserrves this as he inspired thousands of his students and members of the public to read and live a literate life. He never harasses you as most of the others there do. Many an AAU instructor wasted our golden time and planted a hatered towards knowledge and research in most of us. Messeret, on the contrary, is always interesting to be with. He started by telling the audience about his upbringing. He told us that he was a ‘lazy’ student and his lower grade teachers learned to play soccer with his ass. Reading motivations including his non-literate mother who counted the right marks he scored in his notebook were mentioned and acnowledged. Later, she would send him to a local gas seller as an apprentice witnessing that he was weak at numerical skills. I think Messeret has always been the teacher I wanted to come to the class. He said that avid readers from our country contributed to the world through their reading experiences. For instance, demining or mine clearance, according to him, is Haddis Alemayehu’s idea. This renowned author didn’t attend above fourth grade. This sociable lecturer added this: Reading is a university by itself, so everyone should keep reading. We should not beg people to read in a country that has more than 2000 years of writing history. It is a paradox when we hear the other world call us uneducated taking part of their knowledge from our Geez books they looted. We should not be ridiculed as people from whom money should be hid in a book. When we move elsewhere in the world, space exploration is a French writer’s idea. This man of letters wrote that man could move to the moon using a machine he would build. Science has been taking such ideas from literature in this interdisciplinary world. Our mind can process 500 words per minute, so we should give it that much while we read. If we do not give it, it would wander here and there as we are reading. There should be a flow in your reading - you start an idea and shouldn’t move out of it. Then, you will be taken by the idea. True reading is like meditation. Feel the feelings of the characters, and move across the other world through reading. Don’t measure a book in its volume; rather worry how much it appeals to your mind. Teaching English skills would be sentences, yet literature, which promotes critical thinking, is language in context, and it helps you be aware of the culture and language in a wider context. Concerning his reading experience, Messeret says he understood English well after he read fiction at university. They were difficult to him at the beginning. He taught at AAU for 26 years. He told us that literature, which is a liberal subject, is fun to teach and learn. He doesn’t agree on blaming the youth which is taken as a trend from Socrates’ time on. Blaming and denouncing is simple, but building is difficult. I met Mr. Messeret during the tea- break and he shared his various ideas with me and my former classmate, Gebresillase. Our teacher said, “I make myself happy through teaching”. What shocked me is what he said on his suspension from his teaching position. He said he was asked to sign that the department of literature at AAU gets closed. “No I struggled throughout my life for its opening and wouldn’t sign for the closure. The other lecturers as well opposed the query and the administration said I was behind this” he narrates sadly. Let us try for the realization of what Mr Nema said, “We are trying to create the Ethiopian Bill Burt. In additon, our universities should criticize the books we published.” I expressed my gratitude to CODE for the English novels donated to our university. They have been very helpful in our literature class for their familiarity and simplicity. I also suggested that English novels written by Ethiopians including Ashenafi Kebede, Abe Gubegna, Sahlesilase Berhane Mariam and Daniachew worku be published since it is hard to find them in the market nowadays.

ዓርብ 12 ጁን 2015

Rediscover our cave

We have written the itinerary to the cave near Debre Birhan. Please read it and send us your feedback. I hope you and your friends will find it interesting. Thanks! You may share it. DEBRE BIRHAN AREA ITINERARY SITE NAME: Engidwasha TYPE: Natural and historical attraction LOCATION: 90 kilometers north of Debre Birhan. 40 kilometer of it is all weather gravel road which is on a good condition. It is past Tarmaber and Seladingay (Tsadkane). Only 20 kilometres from Seladingay! ABOUT THE SITE: The discovered part of this cave would be the size of a school compound. You should crawl and walk carefully to move from one part of the cave to the other. The hike to the cave takes some 30 minutes down a little steep hill. It is very quiet, tranquil, cold and interesting to be in the cave. Our local delicacies, music, dance and above all the stories the old people narrate about the cave are lively and they make your stay unforgettable. The cave served as a shelter for the whole local community when Fascist Italy invaded the area. There is an emerging story of a massacre on 400 partiots in the cave. The area was the center of the patriotic struggle in the 1930s. Traces of the ancient man, stone tools, are also discovered by an archaeologist researching the cave. Such new bits give a variety to the known sites in the northern route. WHAT YOU NEED: You should come with good shoes that can be used for steep slopes, flashlights, walking sticks and other equipments that you may need to visit this cave. Promoter: Mezemir Girma fb S
egent Ethiopia

The Moja Man’s Friday

In the afternon of Friday, June the 5th 2015, I headed to Adarash Arake, a famous liquor house, in Kebele two of Debre Birhan. Two liters of strong arake, a liquor from Ethiopia, I bought there and headed to the capital, Addis Ababa. On my way, I remembered my grandparents who walked for days all the way from Tegulet to Addis to attend the weddings of their land owner's children. These landowners included Leul Ras Imru and his sisters. After I finished the 130 kilometer journey, I went to Addis Gursha, a restaurant located next to Harmony hotel. The city I knew for the last 12 or so years looks different. I was just unable to find the places I had know easily. Most of the marks I knew were not there, so I had to ask the passers-by for help. Since I was an hour early, I had to wait for the guests and the couple to be wed there at the restaurant drinking soft drink. I had to pay 17 Birr for what cost me 1.50 in 2005 in the same town. In the mean time, guests started to come and chat about the wedding and personal business. As we were sitting in the veranda of Addis Gursha, both Amharic and English music kept flowing to our ears alternately. From PSI Ethiopia’s office located opposite where we were, in wedding dress emerge Erica and Shrunas with their bridesmaids and best men. It was me who saw them first and told the crowd with me about their coming. Soon, we started singing Amharic wedding songs. We got together with them at the main room and then headed to the veranda. The Rasta Addis Gursha owner congratulated the couple and welcomed us all. Erica’s and Shrunas’s coworkers, peace corps volunteers and other invited guests were there at the wedding. In my culture, Friday and June are not believed to be good for weddings to take place. That was why some of my friends did not believe me when I told them that I was going to a wedding. It is believed that the couple would not enjoy a happy life. However, I wish that these two enjoy life to the brim and accomplish their hearts’ wishes. The people drank what was provided and even some of them tasted my Debre Birhan liqor. I didn’t reserve a room, so I had to leave early. I left after a few hours to look for a room. A young man I met on the road showed me where to find and I found one. Again, I wish Erica and Shrunas a happy time together!

ሐሙስ 14 ሜይ 2015

ጥቁር እንዴት አገሬ ብሎ ይዋጋል?

አርብ ሚያዝያ 30፣ 2007 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ እጅግ ድንቅ ትምህርት ከወሰድኩባቸው መድረኮች አንዱ የነበረው በታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ፊትአውራሪነት የተዘጋጀው ትምህርታዊ መድረክ የተካሄደበት ነበር፡፡ ሰዉ ሁሉ ‹‹እንዲህ ነው ምሁራን ማለት!›› ብሎ ያደነቃቸውና እንኳን መመራመርና ማወቅ ለሚፈልግ ቀርቶ ስለ ዕውቀትና ምርምር መስማት እና ማድነቅ ለሚፈልግ ሰው አርዓያ የሆኑ ተመራማሪዎች ጥልቅ ትምህርት የሰጡበት ቀን ነበር፡፡ የዚህ መድረክ ስያሜ ‹‹የአርበኞች ቀን መታሰቢያ አውደ ጥናት›› ሲሆን ሶስት ጥናቶች ቀርበውበታል፡፡ በጥናቱ የተገኙት 90 በመቶ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሲሆኑ የተቀሩት ከባህል ጽ/ቤቶች የመጡ እንግዶች፣ የሰሜን ሸዋ አርበኞች ተወካዮች እና የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች ነበሩ፡፡ በየማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ የማስተዋወቅ ስራ ቢሰራም ይህ በየትምህርታዊ መድረኩ የሰው መታጣት ችግር ሊለቀን እንዳልቻለ ግልጽ ነው፡፡ መፍትሔ ማፈላለግ ግድ ይለናል፡፡ የመጀመሪያው አቅራቢ የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ ሲሆኑ የእርሳቸው ገለጻም ለጥቀው ለሚያቀርቡት ለኢያን ካምቤል ጥሩ ዳራ አስቀምጦላቸዋል፡፡ Mapping Collaboration and Resistance in Africa Orientale Italiana 1935-1941 የሚለውን ወረቀት ፕሮፌሰሩ ከማቅረባቸው በፊት ለአካዳሚክ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከህዝቡም ጋር ለመነጋገር ዕድል የሚከፍት በመሆኑ ደስ እንዳላቸው በመናገር ነበር የጀመሩት፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ከአውደ ጥናቱ የወሰድኩትን ማስታሻ በቅድሚያም የፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለን በአጭሩ አቀርባለሁ፡፡ አርበኝነትን ያለ ባንድነት ወይንም ለጣሊያን ከተደረገው መተባበር ውጭ ሙሉ ለሙሉ ልንረዳው አንችልም ያሉት ምሁሩ በ1928 ዓ.ም ጣሊያን ከኢትዮጵያ እጅግ ያየለ ዝግጅት እንዳደረገችና ኢትዮጵያም በነበራት አቅም ወረራውን እንዴት ለመቋቋም እንደቻለች በማስረዳት የወረራውን መልክ አሳይተዋል፡፡ ከ300 000 በላይ ጦር ወደ አፍሪካ ከጣሊያን ጊዜ ወዲህ ተልኮ የማያውቅ ሲሆን ጣሊያንም ይህንን ሁሉ ወታደር የላከችው አንድም የአድዋው ሽንፈት እንዳይደገም በመፍራትና ሁለትም የቀዳማዊ ኃይለስላሴን ዘመናዊነትና ዝና በመገንዘብ ነበር፡፡ እንደተገመተው የኢትዮጵያም ጦር በቀላሉ አልተሸነፈም፤ ጦርነቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ አላለቀ፡፡ 400 ታንክና 300 የጦር ጀቶች የዘመናዊው የጣሊያን ትጥቅ ማሳያዎች ነበሩ፡፡በሰሜን ለመሸነፍ ሰባት ወር፣ በምስራቅ ስምንት ወር ሲፈጅብን፣ በነገሌ ደግሞ አመት ከስድስት ወር ሳንሸነፍ ቆይተናል፡፡ ጣሊያን ደብረብርሃን ሚያዝያ 25፣ ቱሎፋ በተባለች ኮረማሽ አጠገብ ባለች ስፍራ ደግሞ በ26 ገብቶ ሚያዚያ 27 በ10 ሰዓት አዲስ አበባን ይቆጣጠራል፡፡ ይህም በጦርነቱ ተፈጥሮ ላይ የራሱ ተጽዕኖ ነበረው፡፡ የጣሊያን መንግስት በኢትዮጵያ ተብሎ መታወጁ የብዙውን ሞራል ሰብሯል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከደብረሲና እስከ አዲስ አበባ ባለው መንገድ ላይ መንገዱን የማወክ የአርበኝነት ተግባር ተጀመረ፤ ከዋና ከተማዋ ወደ አዋሽ የሚሄደውን የባቡር መስመርና የፍቼንም መንገድ የመዝጋት ስራ ተጧጧፈ፡፡ በመልሱም መስመሮቹን የማስከፈትና አርበኛውን የማባረር ስራ በጣሊያኖች ተጀመረ፡፡ አርበኝነቱ ቤተክርስቲያን የነበረችበትና ሰፊ መሰረት የነበረው ነበር፡፡ እንደማሳያም አቡነ ጴጥሮስ የነበራቸው አስተዋጽኦ ይገለጻል፡፡ እኝህ መንፈሳዊ ሰው ከደብረ ሊባኖስ ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ነበሩ፤ እዚያም ይኖሩ ነበር፡፡ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር የተጠራውንም ስብሰባ በገዳሙ መርተው ነበር፡፡ በ1928 ሃምሌ ላይ አርበኞቹ አዲስ አበባን ነጻ ለማውጣት ሞከረው የነበረ ሲሆን አቡነ ጴጥሮስም ይህ ሙከራ ከሽፎ ይገደላሉ፡፡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ የራስ እምሩ የጎሬው መንግስታቸው ፍልሚያውን ሲያካሂድ ቆይቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ራሳቸው ራስ እምሩ ተማርከው ወደ ጣሊያን ይወሰዳሉ፡፡ የጣሊያን ጦር ዋነኛ ተግባራትም የሸዋን መስመሮች ማስለቀቅ፣ የራስ ደስታን ጦር ማጥፋትና የጣሊያንን መንግስት የሚደግፉትን ማፈላለግና ግንኙነት መፍጠር ይሆናል፡፡ የራስ እምሩና የጥቁር አንበሶች መያዝ አንድ ጉልህ ሂደት ነው፡፡ በየካቲትም ወር ግራትሲያኒ መስመሮቹን ስላስለቀቀ አሸንፈናል የሚል ስሜት መጣበት፡፡ ለወራሪው የነጭ ጦር የሚደረገው ትብብር ሁለት መልክ ነበረው፡፡ ይኸውም አንድም ግለሰቦች እንደራስ ሃይሉ ራሳቸው የሚያደርጉት ትብብር ሲሆን ሌላውና ብዙ ሰዎችን የሚካትተው ግለሰቦች ማህበረሰባቸውን ይዘው የሚገቡበት ሂደት ነበር፡፡ በሁለተኛው መንገድ የሚገቡት ባላባቶች በአፋርና በሰሜን ነበሩ፡፡ ለወራሪዎቹ መተባበሩ በነዚህ ስፍራዎች ብቻ ሳይወሰን ድፍን ሸዋ፣ ጎንደር፣ ላስታ፣ ጎጃም ባንዳ ነበር አሉ፡፡ ለአገሩ የሚዋጋ በየስፍራው መኖሩ ግን መዘንጋት የለበትም፡፡ ሰፊ የማግባባት ስራ ከተሰራ በኋላ የወላይታ፣ ጅማ፣ ከምባታ እና ሃድያ ባላባቶች ለጣሊያን ሊተባበሩ ቻሉ፡፡ ለዚህም ትብብር የዳረጋቸው የጣሊያን ፖሊሲና ውትወታ ነው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ማለት አማራ የሚገዛት የአማራ አገር ናት›› እያሉ ጣሊያኖቹ ከወለጋ፣ ከኢሊባቡር እና ከፋ ደጋፊዎችን ማግኘት ችለው ነበር፡፡ ኦርቶዶክስ ነው የሚገዛችሁ በማለትም ይህንን ያገኙትን ድጋፍ አጠናክረውታል፡፡ ከሸዋ ውጭ የነበረውን አማራ ደግሞ ሸዋ ነው የሚገዛችሁ እያሉ ለመከፋፈል ቢሞክሩም አልተቻላቸውም፡፡ የሆነው ሆኖ ከየካቲት 1929 እስከ 1933 ጣሊያኖች በአንጻራዊነት በሰላም የሚያስተዳድሩባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ለኘጮቹ የተደረገውን ተብብር ስናይ ባንዳዎች የራሳቸውን ታሪክ ስላልጻፉና ባንዳነታቸውንም ከነጭራሹ ደብቀው ስለተቀመጡ የእነርሱ ታሪክ ያልተሟላ ነው፡፡ በጣሊያኖች በኩል ለተባበሯቸው ኢትዮጵያውያን በሮማ ያደረጓቸውን አቀባበሎችና በቤተመንግስት ያደረጓቸውን መስተንግዶዎች ጨምሮ በርካታ ፎቶዎችን እና ካርታዎችን ከአርኪ ገለጻ ጋር ያቀረቡት ፕሮፌሰሩ ያለምንም የጽሑፍ ማስታወሻ ንባብ የሚሰጡት ማብራሪያ አብዛኛውን እስካሁን የማውቀውን ምሁር የሚያስከነዳ ነበር፡፡ በሞሶሎኒ ቤተመንግሰት ፊት ለፊት ለጅማው ገዥ ለሱልጣን አባ ጆቢር ክብር የተደረገውን ደማቅ ሰልፍ አሳይተውናል፡፡ የአፋርና የቆላው ኢትዮጵያ ሰዎች የተደረገላቸውን አቀባበል በክብር ልብስ ሆነው በፊተኛው ረድፍ ቆመው ሲታደሙ አይተናል፡፡ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ዮሐንስም ተባባሪ ሆነው ሄደው ነበር፡፡ እንደምገምተው አቅራቢው ምሁር ያላቸው የጣሊያንኛ፣ የአረብኛና የግዕዝ ችሎታ ከተለያዩ መዛግብት ያልተዳሰሱትን እውነታዎች ለመፈልፈል ረድቷቸዋል፡፡ የአርበኝነትን እንቅስቃሴ በተመለከተ ግራትሲያኒ አጠፋዋለሁ ሲል አልሆነለትም፡፡ በውጭው ዓለም ጥቁርና ኋላ ቀር ህዝብ እንዴት ለአገሩ ይዋጋል የሚል አስተሳሰብ ነበር፡፡ አገሬ ኢትዮጵያ የሚለው ግንዛቤ ግን ለብዙ ዘመን ለሺዎች አመታት የቆየ ሲሆን ንጉስ ኢዛና ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚለውን በደብደቤው ውስጥ የተጠቀመው፡፡ መጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ግዕዝ ሲተረጎምም ኢትዮጵያ የሚል ቃል ተጠቅመዋል፡፡ ከአረብኛ ወደ ግዕዝ የተተረጎመ ገድል ላይም ኢትዮጵያ አለች፡፡ ከዚያ ዘመን ወዲህም በ13ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ይህንኑ ቃል ተጠቅመውት እናገኘዋለን፡፡ በአረብኛ አበሻ የሚለውን ወደ ግዕዝ ሲተረጉሙ ኢትዮጵያ እያሉ ነው፡፡ በግዕዝ ትርጉሙ ላይ አበሻ የሚል የለም፡፡ ስለዚህ ለመንደራቸው፣ ለቀያቸው አለያም ለዘመዶቻቸው ብቻ ሳይሆን ለሃገራቸው የሚቆሙ አርበኞች መኖራቸው ለወራሪዎች እውነታውን ከጠበቁት በላይ አድርጎባቸዋል፡፡ አርበኞችንም አግባብቶ ወደ ጣሊያን ለማስገባት እልህ አስጨራሽ ጥረቶች ይካሄዱ ነበር፡፡ እንደ ምሳሌም በሞሶሎኒ ጥያቄ አበበ አረጋይ ከኢጣሊያ መንግስት ጋር እደራደራለሁ ይላሉ፤ ይህን የሚያደርጉትም ጊዜ ለመግዛት ነው፡፡ የትምህርት ደረጃቸው ስምንተኛ ክፍል ስለደረሰ የውጭ ቋንቋና ጂኦግራፊም ጭምር ስለሚያውቁ የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት መከሰትን ይገምቱ እና ይጠባበቁ ነበር፡፡ ሞሶሎኒም ለእንደራሴዎቹ ወይ ተዋግታችሁ አሸንፉ ወይንም ለቃችሁ ውጡ ይላቸዋል፡፡ ከራስ አበበ ወገን ፊታውራሪ ወንድምነህም ለድርድር መጥተው ፎቷቸው ይታያል ፕሮፌሰሩ ባቀረቡልን ትዕይንት ላይ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በዓለም ሁኔታም መቀያየርና በነበረውም የሃይል አሰላለፍ መሰረት ሁኔታዎች ሁሉ ለጣሊያኖች ይገለባበጡባቸዋል፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ባዳ የነበረውንም ጨምሮ የመቀመጫ መርፌ ይሆኑባቸዋል፡፡ የእንግሊዞች መምጣት አስተዋጽኦ ማድረጉ አይናቅም፡፡ በእንግሊዞች እገዛ ያደረግነው የ1933ቱ ጦርነት የነጻነት ጦርነት ሳይሆን የመጫረሻው ጦርነት መባል አለበት፡፡ ምክንያቱም ከዚያም በፊት በርካታ ጦርነቶች በየጠቅላይ ግዛቱ ስለነበሩ ነው፡፡ ከጥር እስከ ሚያዚያ 1933 ጣሊያን አለቀለት፡፡ ይህም የሆነው ህዝቡና አርበኞች እንደገና ስለተነሱ ነው፡፡ ባላባቱ ሁሉ ወደ አርበኝነት ይገባ ያዘ-- በደቡብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን በሁሉም ቦታ፡፡ ቀጥሎ ምርምራቸውን ያቀረቡት ኢያን ካምቤል ሲሆኑ ምርምራቸውም የሚያጠነጥነው በደብረሊባኖስ ግድያ ላይ ነበር፡፡ በዛሬው ዕለት ታሪክ እየሰራን ነው ብለው ነበር የጀመሩት፡፡ ይህ የአሁኑ መድረክ የደብረ ሊባኖሱ ታሪክ ለህዝብ ይፋ የሆነበት የመጀመሪያው ነው፡፡ ጣሊያን ግዛት ያስፈልጋታል፤ ኢትዮጵያም መሰልጠን አለባት የሚል ነበር ጣሊያኖች እዚህ ለመግባታቸው ያቀረቡት ምክንያት፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ስለተፈጸመው ትልቁ ግድያ ብዙም የሰማነው ነገር አለመኖሩ የሚገርም ነው፡፡ ግራትሲያኒ የአዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ከሶስት ሳምንት በኋላ የኢትዮጵያ ገዥ ተብሎ ተሾመ፡፡ ግራትሲያኒ በአንደኛው የዓለም ጦርነትና በሊቢያም ተሳትፎ የነበረውና መጥፎ ታሪክ ያለው ሰው ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ስምንት ሰው የሚሰቅሉ ተንቀሳቃሽ የሰው መስቀያዎች ኢትዮጵያን በሚያስተዳድርበት ወቅት በየስፍራው ነበሩት፡፡ ግራዚያኒ ደብረሊባኖስ እና ሌሎች የኦርቶዶክስ አብያተክርስቱያናት የችግሩ ምንጭ እንደሆኑ ያምን ነበር፡፡ ስምኦን አደፍርስ፣ ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ ያቀነባበሩት የግራትሲያኒ የግድያ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቶ ህዝቡን ለማስጨፍጨፍ በቃ፡፡ የሞቱትን ከአዲስ አበባ ለማውጣት በ100 የጭነት መኪናዎች አራት ቀን ወስዶባቸዋል፡፡ ግራዚያኒ የግድያ ሙከራ ከተሞከረበት ጊዜ ትንሽ ቀደም ብሎ በዕለቱ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይ አቡነ ቄርሎስ ቀርተውበት ሲጠባበቅ የሚያሳይ ፎቶ አይተናል፡፡ እርሳቸውም አሞኛል አልመጣም ብለው ሀኪም ልኮ ጤንነታውን አረጋግጦ በግዴታ አምጥቷቸዋል፡፡ ችግር ሊኖር እንደሚችል ሰው ነግሯቸው ነበር ማለት ነው፡፡ የችግሬ ምንጭ ነው የሚለውን ገዳም የደብረሊባኖስን ለማውደም የሚያዝ ሰነድ አዘጋጅቶ የነበረው ግራትሲያኒ በገዳሙ ያሉትን ካህናትና ምዕመናን ለመግደል ዕቅድ ሲወጣ ከረመ፡፡ ግንቦት 12 ቀንም የአቡነ ተክነሃይማኖት ንግስና የሚካኤልም በዓል ቀን ስለነበር ተመረጠ፡፡ ለንግስ የመጣውንና ሁሉንም ህዝብ ቤተክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ አስገብተው ደብቀው ባስቀጧቸው መኪኖች እየጫኑ ወስደው ገደሏቸው፡፡ ግራዚየኒ 452 ሞተ ብሎም ይፋ ቢያደርግ እንኳን ከ1800- 2200 ሰው ተገድሏል፡፡ ከደብረ ሊባኖስ የተረፉትን ወደ ስምንት መቶ የሚጠጉ ሰዎችም ደብረ ብርሃን ያመጧቸዋል፡፡ ከዚያም ወደ አንኮበር መስመር እንግጫ የሚባል ስፍራ ላይ ወስደው በምስጢር ጉድጓድ አስቆፍረው ገድለው እንደቀበሯቸው የሚያስረዱ የአይን ምስክሮችን ጭምር አነጋግረዋል ተመራማሪው፡፡ ከዚያም የተረፉት እዚህ ደብረ ብርሃን ከተማ ጮሌ አካባቢ እንደተገደሉና እንደተቀበሩ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህራን የሆኑት አለባቸው በላይና ቴዎድሮስ ስዩም በዕለቱ ባቀረቡት ምርምራቸው አረጋግጠዋል፡፡ ይህን ቦታም ለመንከባከብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ የሞቱ ሰዎች ዘመዶችና እነዚያን ሰዎች የሚያውቁ ሰዎች ተጠንተው ከሰሜን ሸዋ ተሰብስበው ሶማሊያ ውስጥ ወደሚገኘው ደናኔ እስር ቤት ተወስደው የታሰሩ ሲሆን ብዙዎቹም ሞተዋል፡፡ እነዚህ በሺዎች የሚቆጠሩት ኢትዮጵያውያን የሞቱበትና የታሰሩበት ደናኔ ታሪካዊ ነው፡፡ የደናኔ የማጎሪያ ካምፕ ከ75 ዓመታት በፊት ነበር የተከፈተው እዚያ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል፡፡ ግራትሲያኒ የሰራው ግፍና በደል ተደብቆ ቆይቶ አሁን ድረስ ተመራማሪዎችም ሳይገነዘቡት መቆየታቸው ምክንያቱ አንድም እርሱ ራሱ ነገሮቹን ሁሉ እንደዚህ በድብቅ መስራቱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሰዎች ምንድነው እንደዚህ ክፉ የሚያደርጋቸው ከተባለ በማህበረሰብ ያለውን ሁሉንም ነገር ማላመድ ይቻላል፤ ሰውን መግደልንም ማለማመድ ይቻላል፡፡ ጀግናን ማወደስን ተምረንዋል፡፡ ዶሮ እንደመግደል ነው ብሎ ማስተማር፤ ልጆች የአርበኞችን የተቆረጠ ራስ እንዲይዙ ማድረግ መጥፎ ነገር ሰርተው ምንም እንደማመጣባቸውና ተጠያቂነት እንደማይኖር መንገር ነው መላው ብለዋል ኢያን ካምቤል፡፡ የእንግሊዝ መንግስት ኢትዮጵያ ጣሊያንን ወደ ፍርድ አደባባይ እንዳታወጣ ያደረገው ታሪካዊ ውሳኔ ዘርፈ ብዙ መንስኤዎች ነበሩት፡፡ በመጀመሪያም ሃገሪቱ እንድትወረር እጃቸው ስለነበረበትና በሌሎችም ስሌቶቻቸው ኢጣሊያን ማገዙን ወደውታል፡፡ በእኛ ሀገር በኩል የንጉሰ ነገስቱ መንግስት መጠነኛ እገዛ ቢደረግለትም ያ በቂ አይደለም የሚሉ እየመጡ ነው፡፡ በእንግጫ ሟቾቹን ለማስታወስ ምንም የተደረገ ነገር የለም፡፡ በደብረ ሊባኖስ ግን የሞቱትን ለማሰብ የተጻፈ የጽሑፍ መግለጫ አለ፡፡ የሚታወሱበትን አይነተኛ ነገር መፈለግ ግድ ይለናል፡፡ አሁን በሰሜን ሸዋ አርበኞችና በዩኒቨርሲቲያችን የታሪክ ምሁራን እየተሰራበት ያለው የደብረ ብርሃኑ መታሰቢያ ከዳር ቢደርስ ቀጣይ የሸዋ አርበኞችን ማፍራት እንደሚቻል እምነቴ ነው፡፡ በአውደ ጥናቱ ዕለት ከሸዋ አርበኞች ማህበር የመጡት አራት ሃላፊዎች በመርሃ ግብሩ የታደሙ ሲሆን ገና ወደ አዳራሹ ሲገቡ ተማሪውና ታዳሚው ተነስቶ በጭብጨባ እና በደስታ ነበር የተቀበላቸው፡፡ ባላምባራስ በየነ አደለኝም በወታደራዊ ሰላምታ ህዝቡን አመሰገኑ፡፡ የዚህ ዘመን ወጣቶች ታሪካቸውን ለማጥናት ባላቸው ትጋት እጅግ እንደተደሰቱ ተናግረው በ93 ዓመታቸው ይህን በማየታቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የታሪክ ትምህርት በየመድረኩ የሚሰጥበት ዕድል ቢመቻች ሁላችንም ስለማንነታችን እንድናውቅና የአሁኑንም ሆነ የወደፊቱን ህይወታችንን በተሻለ ሁኔታ እንድንመራ ስለሚያስችለን እንደዚህ ዓይነት መድረኮች ቢጠናከሩ ጥሩ ይሆናል በሚል እርስዎንም ስለሰጡኝ ጊዜ እያመሰገንኩ ልሰናበት፡፡

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...