ቅዳሜ 28 ጁላይ 2018

ለመደሰት ስለማንበብ


ራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት

የዕለቱ መልዕክታችን 21.11.2010


የንባብ ዓላማዎች ብዙ ናቸው፡፡ አንደኛው ለመደሰት ማንበብ ይባላል፡፡ ለመደሰት ማንበብ በብዛት የልቦለድ፣ የግጥምና የተውኔት ንባብን የሚመለከት ነው፡፡ መዳረሻው መደሰት ሲሆን እግረመንገዱን የሚያሳካቸው ንዑሳን ዓላማዎችም ይኖሩታል፡፡ ለመደሰት የማንበብ ዓላማችን ሌላ ንባብን ሲገታብን ግን ለምን ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በወሳኝ ሃገራዊ ክስተቶች ወቅት የማይናወጥ ምክንያታዊ አቋም አይኖረንም፡፡  ዕውቀታችን ጎልብቶ በምንማረው የትምህርት ዘርፍ የተሳካልን ሰዎች ልንሆን አይቻለንም፡፡ በሳይንሣዊ መንገድ የተፈተሹ ምርምሮችን ማድረግም ሆነ የተዘጋጁትን በጥሩ መንገድ መረዳት ያዳግተናል፡፡ ምሁርነት፣ አርቆ አሳቢነት፣ አመዛዛኝነትም ሆነ ለወገንና ለራስ ጠቃሚነት የሚመጣው ጠጣሩን ንባብ ስናነብና በዚያም መንገድ እስከሚያስፈልገው የትግበራና የማሰላሰል ጎዳና ስንጓዝ ነው፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የትምህርት አቅጣጫ ወዴት ነው?

 የትምህርት አቅጣጫ ወዴት ነው? ትምህርት አጉል አቅጣጫ እየሄደች ይመስላል። ለዚህ ማሳያ የተወሰኑ ክስተቶችን ላንሳ። ከሰሞኑ አንዲት መምህር እያስተማረች የነበረበት ክፍል ለፈተና ተፈልጎ እንድትወጣ ስትጠየቅ በጥያቄው ተስ...