እሑድ 29 ጁላይ 2018

የዕለቱ መልዕክታችን


ራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት

ሰኞ፣ ሐምሌ 23፣ 2010

የዕለቱ መልዕክታችን

አንድ አፍታ ከባለጸጋው ጋር እናውጋ


በቅርቡ አንድ የቪዲዮ መልዕክት ያደረሱን ቢሊየነሩ ስራ ፈጣሪ ቢልጌትስ ስለ ንባብ ልማዳቸው አንዳንድ ነገሮችን ተናግረዋል፡፡ ከነዚህም አንዱ አንድን መጽሐፍ ጀምሮ መተው ያለውን ጉዳት አስመልክቶ ነው፡፡ ወደ እርሳቸው ቃላት በቀጥታ እንምጣ

1.     ‹‹የማልጨርሰውን መጽሐፍ እንድጀምር ለራሴ አልፈቅድም›› ይሉናል፡፡

ወገኖቼ፣ እስኪ ይህችን ንግግር እንመንዝራት፡፡ ስንቶቻችን የማንጨርሰውን መጽሐፍ ጀማምረን ሙሉ ሃሳቡን ሳንገነዘብ አቆምነው! ካልጨረስነው መጽሐፍ  ያገኘነውን ሃሳብ ይዘን የተምታታንና ያምታታንም አንጠፋም፡፡ ደራሲውን  ለመተቸትና ለመገምገምም የተነሳን አንጠፋም፡፡ ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ ለመሆኑ ስንት መጽሐፍ ጀምረን ሳንጨርስ ተውን?

እንደገና ወደ ቢልጌትስ ሌሎች ንግግሮች እናቅና፡-

2.     ከመጻሕፍት ጋር በሚያደርገው ቆይታ በተቻለው መጠን ብዙ ለማትረፍ ማስታወሻ ይወስዳል

‹‹በተለይ ኢ-ልቦለድ ለሆነ መጽሐፍ አትኩሮትዎን ሰብስበው እያነበቡ መሆንዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ አዲሱን ዕውቀት ካነበራችሁ ዕውቀት ጋር እያያዛችሁ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ስላለው ነገር በደንብ እያሰብኩ መሆኑን የማውቀው ማስታወሻ ስወስድ ነው፡፡››  

‹‹በሚነሱት ሃሳቦች የማልስማማ ከሆነ፤ ያው በመጽሐፉ ህዳጎች ላይ ማስታወሻ እየወሰዱ ማንበብ ብዙ ጊዜ ይወስዳል፤ እባክህ ደራሲው ሆይ! የምስማማባቸውን ነገሮች አንሳልኝና ቶሎ አንብቤ ልጨርስ እለዋለሁ በምናብ፡፡ ይህን ያንን መጽሐፍ ሳልል፣ ባለፈው ፊልሙን ቀድሜ ያየሁትን መጽሐፍ ሳይቀር፣ ጀምሬ መጨረስ አለብኝ እልሻለሁ፡፡

3.     ከሶፍትና ሃርድ ኮፒ

‹‹እያቀያየርኩ አነባለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ማታ ቁጭ ብዬ የወረቀት መጽሔት ወይም መጽሐፍ ሳነብ ከሆነ ያው ለምጄዋለሁ፡፡ ሽርሽር ምናምን ስሄድ ግን ለሸክም ከባድ ስለሆነና ያለፈበት መሆኑ ስለሚታወቅ ምን … አለ አይደል ያስጠላሻል! እንደዚህ ዓይነቱን መጽሐፍ የምታነብ ከሆነ በአንዴ ለአንድ ሰዓት ምናምን ቁጭ ማለት ግድ ይልሃል፡፡ አምስት አስር ደቂቃ አንብበህ ግን ምን ነበር ያነበብኩት ብለህ ራስህን መበጥበጥ ይሆንብሃል፡፡ አጫጭር የመጽሔት ጽሑፎች ወይም ዩቱብ ቪዲዮዎች ግን ለዚህ የአንድ አፍታ ቆይታ ነገር ሊስማሙዎ ይችላሉ፡፡ በየምሽቱ ከአንድ ሰዓት ትንሽ ተረፍ አድርጎ ማንበብ ስለለመደብኝ ለሰሞኑ የመረጥኩትን መጽሐፍ ቀብ አድርጌ ጅምሬን አስኬዳለሁ፡፡››



በመጨረሻም፡-

እርስዎስ ስለንባብ ልምድዎ ምን ይላሉ?

https://www.youtube.com/watch?v=eTFy8RnUkoU


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...