ዓርብ 30 ጁን 2023

የሳሲት ወጎች ቁ. 4 ፈረንጆች የመጡ ዕለት

 የሳሲት ወጎች 

ቁ. 4

ፈረንጆች የመጡ ዕለት


ማስታወሻ - ይህን ተከታታይ ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሣሣኝ 'አፍሪካዊው ልጅ' የተባለው የካማራ ላዬ ማስታወሻ ሲሆን፤ ተወዳጅነት ካገኘ ወደ እንግሊዝኛም እተረጉመዋለሁ።)

የአንደኛ ወይም የሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ። ሁሉም ተማሪ ቁምጣ ለባሽ በነበረበት በዚያን ወቅት (1985/86) እኔም አባቴ የሰፋልኝን ባለማንገቻ ቁምጣ ለብሻለሁ። ቲሸርትና ጃኬትም አልቀሩም። ሱሪ የሚለብሱት መምህራን ነበሩ። ጫማ አይታወቅም። ሱሪ ይኮሰኩሰናል፤ ሥራ አያሰራንም ወዘተ የሚሉ ትልልቅ ሰዎችን ሰምተን ሳይሆን በአገሩ ሱሪ ሰፊ ስላልነበረ ነው። ተነፋነፍና ሳሪያን ሰፊ ግን ነበር። ቆይቶ ስድስተኛ ክፍል ሆኜ ሱሪ መልበስ ተጀምሯል። ከትምህርት ቤቱ ጎን የጋሽ ማንደፍሮ ግቢ አለ። አንድ ቀን በምላጭ ተቆርጦ እንደ ፊሽካ የሚነፋውን ሙጃ ለመንቀል ሄደን የጋሽ ማንደፍሮ ውሻ በቁምጣ ካልተሸፈነው እግሬ ገመጠችልኝ። ሐኪም ቤት ተወሰድኩ። ያው የብቻዬ በኪሷ የነበረ ኪሮሽ የወጋት ዕለት ለማስወጣት እንደሄደችው። 

"ጋሽ አድማሱ ኑ አክሙት።" ያለው ጌታቸው መሰለኝ።

"እኔ እሱ አያክመኝም።" አልኩ። በሐኪም እንጂ በዘበኛ ላለመታከም ያደረኩት ጥረት አልተሳካም። ሽማግሌው ዘበኛ አከሙኝ። ያኔ ጠዋትም ከሰዓትም ነበር የምንማረው። ማታ እቤት ሄጄ ሰው በሌለበት ቁስሉን ለማየት ስለፈለግሁ ላጥኩና አየሁት። ሁለት ቦታ ተወግቷል። ትንሽ ሸፍኜው ቆየሁና ላጥኩት። ሌላ ቀን ሁሉም ተማራ የዉሻዋን ቦታ አልፎ ይንጋጋል። ምንድነው ብዬ ለማየት ብጓጓም ለመሄድ አልፈለግሁም። አይተው ሲመለሱ ነገሩኝ። ፈረንጆችን ነበር ያዩት። ፈረንጆቹ የሥጋ ደዌ ሕክምና ለማከም የመጡ ነበሩ። ቡድናቸው ትልቅ፣ ትንሽ፣ ሴት ወንድ፣ ሕፃን ሳይቀር ሐኪሞችን የያዘ ነበር አሉ። በአጥሩ ቀዳዳ ለማየት ስጥር ረጃጅሞችና ትልልቅ ልጆች ከለሉኝ። ከፈረንጆቹም ልጆች እኛን ለማየት የሚጣጣሩ አሉ አሉ። በውልብታ ግን በጣም ቀያይና ፀጉራቸው የተለየ ሰዎችን ያየሁ መሰለኝ። ወዲያው ደወል ተደወለ። እረፍቷ አለቀች። ፈረንጆችን የማየት ህልሜ የተሳካ አልመሰለኝም። ገባሁ። ምን ነበር የፈረንጆቹንም ልጆች እኛንም ቢያገናኙንና በአስተርጓሚ ብናወራ? ቤተሰቦቻቸው ግን ሥራ በዝቶባቸው ይሆናል። ያክማሉ፤ ጫማም ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ ፈረንጅ ያየሁት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ይመስለኛል። 

እስከ ክፍል 100 ይቀጥላል ...

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

Z.A. They warn Oromo parents to advise their kids to avoid interacting with Amhara kids at school.

  Z.A. They warn Oromo parents to advise their kids to avoid interacting with Amhara kids at school. The Shenes said they wanted to aven...