ዓርብ 30 ጁን 2023

የሳሲት ወጎች ቁ. 4 ፈረንጆች የመጡ ዕለት

 የሳሲት ወጎች 

ቁ. 4

ፈረንጆች የመጡ ዕለት


ማስታወሻ - ይህን ተከታታይ ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሣሣኝ 'አፍሪካዊው ልጅ' የተባለው የካማራ ላዬ ማስታወሻ ሲሆን፤ ተወዳጅነት ካገኘ ወደ እንግሊዝኛም እተረጉመዋለሁ።)

የአንደኛ ወይም የሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ። ሁሉም ተማሪ ቁምጣ ለባሽ በነበረበት በዚያን ወቅት (1985/86) እኔም አባቴ የሰፋልኝን ባለማንገቻ ቁምጣ ለብሻለሁ። ቲሸርትና ጃኬትም አልቀሩም። ሱሪ የሚለብሱት መምህራን ነበሩ። ጫማ አይታወቅም። ሱሪ ይኮሰኩሰናል፤ ሥራ አያሰራንም ወዘተ የሚሉ ትልልቅ ሰዎችን ሰምተን ሳይሆን በአገሩ ሱሪ ሰፊ ስላልነበረ ነው። ተነፋነፍና ሳሪያን ሰፊ ግን ነበር። ቆይቶ ስድስተኛ ክፍል ሆኜ ሱሪ መልበስ ተጀምሯል። ከትምህርት ቤቱ ጎን የጋሽ ማንደፍሮ ግቢ አለ። አንድ ቀን በምላጭ ተቆርጦ እንደ ፊሽካ የሚነፋውን ሙጃ ለመንቀል ሄደን የጋሽ ማንደፍሮ ውሻ በቁምጣ ካልተሸፈነው እግሬ ገመጠችልኝ። ሐኪም ቤት ተወሰድኩ። ያው የብቻዬ በኪሷ የነበረ ኪሮሽ የወጋት ዕለት ለማስወጣት እንደሄደችው። 

"ጋሽ አድማሱ ኑ አክሙት።" ያለው ጌታቸው መሰለኝ።

"እኔ እሱ አያክመኝም።" አልኩ። በሐኪም እንጂ በዘበኛ ላለመታከም ያደረኩት ጥረት አልተሳካም። ሽማግሌው ዘበኛ አከሙኝ። ያኔ ጠዋትም ከሰዓትም ነበር የምንማረው። ማታ እቤት ሄጄ ሰው በሌለበት ቁስሉን ለማየት ስለፈለግሁ ላጥኩና አየሁት። ሁለት ቦታ ተወግቷል። ትንሽ ሸፍኜው ቆየሁና ላጥኩት። ሌላ ቀን ሁሉም ተማራ የዉሻዋን ቦታ አልፎ ይንጋጋል። ምንድነው ብዬ ለማየት ብጓጓም ለመሄድ አልፈለግሁም። አይተው ሲመለሱ ነገሩኝ። ፈረንጆችን ነበር ያዩት። ፈረንጆቹ የሥጋ ደዌ ሕክምና ለማከም የመጡ ነበሩ። ቡድናቸው ትልቅ፣ ትንሽ፣ ሴት ወንድ፣ ሕፃን ሳይቀር ሐኪሞችን የያዘ ነበር አሉ። በአጥሩ ቀዳዳ ለማየት ስጥር ረጃጅሞችና ትልልቅ ልጆች ከለሉኝ። ከፈረንጆቹም ልጆች እኛን ለማየት የሚጣጣሩ አሉ አሉ። በውልብታ ግን በጣም ቀያይና ፀጉራቸው የተለየ ሰዎችን ያየሁ መሰለኝ። ወዲያው ደወል ተደወለ። እረፍቷ አለቀች። ፈረንጆችን የማየት ህልሜ የተሳካ አልመሰለኝም። ገባሁ። ምን ነበር የፈረንጆቹንም ልጆች እኛንም ቢያገናኙንና በአስተርጓሚ ብናወራ? ቤተሰቦቻቸው ግን ሥራ በዝቶባቸው ይሆናል። ያክማሉ፤ ጫማም ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ ፈረንጅ ያየሁት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ይመስለኛል። 

እስከ ክፍል 100 ይቀጥላል ...

የሳሲት ወጎች ቁ. 3 አራጅ የመጣ ቀን

 የሳሲት ወጎች ቁ. 3

አራጅ የመጣ ቀን


ሳሲት ስናድግ እንደዛሬ ልጅ ጫማ የለንም። በክረምት ወቅትና እስከ ጥር በግ እናግዳለን። ከመስከረም እስከ ጥር ግማሽ ቀን በግ አግደን ግማሽ ቀን እንማራለን። ጉልበታችንን ለሚፈልጉት ቤተሰቦቻችን ትምህርት በፈረቃ መሆኑ ተወዷል። ነገሩ የመማሪያ ክፍል እጥረትን ለመፍታት የተዘየደ መላ ሊሆን ቢችልም። ስናድግ አስፈሪ ነገሮች አዘውትረው ይወራሉ። የሰዎች በተለያዩ መንገዶች መጎዳትና መሞት የሚታወቅ ቢሆንም አንዳንድ ትረካዎች በተለይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥሩብናል። የጭራቅ ነገር ያስፈራናል። "ዱሮ አያቶቼ ቤት መጥቶ ነበር አሉ። አራት ዓይኖች አሉት። ከኋላ ያሉትን ሁለት ዓይኖች በሻሽ ሸፍኗቸዋል። እንጀራ እንዲሰጡት ጠይቆ ሁለት እንጀራ ሲሰጡት በአንዴ ጎረሰው። ዉኃ በአቦሬ ጨምረውለት በአንዴ ጨለጣት።" ትላለች ዓለምሸት ሞሰብ እየሰፋች። እኔ ፍርሐት ይዞኛል። ይህ ትረካ የበለጠ የሚያስፈራኝ ከሰው ጋር ስሆን ሳይሆን በጨለማና ዱር ወይም ጫካ በጎች ሳግድ ነበር። በጨለማ ብፈረም መብራት በማብራት ፍርሐቴን እቀንሳለሁ። የዱሩም ትልቅ ሰው ወዳለበት በመሮጥ ለማምለጥ አስባለሁ። አንድ ቀን አይጥ ዉኃ ጋ በጎች ሳግድ አህዮች የሚነዱና አለባበሳቸው ጭራቅ የሚመስሉ ሰዎች አየሁ። ጭራቅ ባይሆኑ እንኳን አራጅ ይሆናሉ ብዬ ገመትኩ። አራጅ የሰው ደም የሚሸጥ ነው ይባላል። ወፍጮና መኪና በሱ ነው የሚሰራው ተብሎ ይታመናል። "ያለዚያማ ይህን ሁሉ እህል እንዴት ይፈጨዋል! የአጋንንት ሥራ ነው።" ይሏችኋል። አራጅም ሆኑ ጭራቅ ሰው ወዳለበት መሄድ አማራጬ ሆነና እየራቅሁ ሄድኩ። ቢያንስ አበባ የግሌ ጓሮ ባለው ጫካ አንድ ሰው ተሸፍኖ እየጮኸ እንዳስፈራራኝ ዕለት እየጮህኩ አልሮጥኩም። ገሸሽ ብዬ አሳለፍኳቸው። ምንም አልተተናኮሉኝም። በኋላ ማታ ወደ ቤት ስመጣ በሰፈራችን ባለ ቤት ደጅ አህዮቻቸው ታስረዋል። ሰዎቹም ጠላ ይጠጣሉ። ለካ ጭራቆች አይደሉም። ላሊበላዎች ናቸው አሉ። አይ ልጅነት! 

ሐሙስ 29 ጁን 2023

የሳሲት ወጎች ቁ. 2 ሙስሊም የመጣ ቀን

የሳሲት ወጎች

ቁ. 2

ሙስሊም የመጣ ቀን


እስኪ አስቡት። ወረዳው ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሊሆን ትንሽ የቀረው ነው። ያለው መስጊድ ከአንድ አይበልጥም። ያውም የወረዳችን ጫፍ ስገሮ ቆላ። በእውነት የስገሮ ቆላን ሙስሊሞች ወግ ቅዳሜ ገበያ የሚመጡ ዘመዶቼ ሲያወሩ ነበር የሰማሁት። የአሁኑን ትውልድ ብትጠይቁት "ቀጣፊ" ሊላችሁ ይችላል። "እኛ ወረዳማ ተክርስቲያን ዉጪ የለም" እንደሚሏችሁ አትጠራጠሩ። እነዚያ ሙስሊሞች ወደ ክርስትና ተቀይረዋል ወይም እየተቀየሩ ነው የሚል ወሬ ሰምቻለሁ። ይህ ታዲያ የዛሬ 25 ዓመት የነበረ ወሬ ነው። እስልምና እንኳን አረብ አገርንና አፍሪካን አውሮፓንና አሜሪካን በአስገራሚ ፍጥነት እያዳረሰ ስላለ መሐመድም ሆነ ሠይድ የተጉለት እስልምና መጥፋት ግድ አይላቸውም። ያው በጥናትና ምርምር ሰበብ ልክ አይሁዶች ብረትና ሸክላ ሰሪ ሁሉ የኛ ነው ብለው ሰሜን ሸዋ ገብተው ውስጥ ውስጡን ወታደርና ዘመናዊ ባሪያ ምልመላውን እንደተያዙት ሁሉ አረቦችም ሊመጡላችሁ ይችላሉ። ግፋ ቢል ሙስሊም እንጂ አረብ ነኝ የሚል አማራ አይኖርም መቼም። የአረብ ቤት ባለቤት ክልስ አረቦችን አይጨምርም። ምን አለፋችሁ፣ ሳሲት ሙስሊም አይታወቅም ነበር። 1988፣ 89፣ 90 ሂዱ። በእርግጥ እንደ አሁኑ ጳድቃኔ ማርያም ታዋቂ ገዳም ሳትሆን እኛ ጋ ከሩቅ ሰዎች የሚመጡት ወፋ ነገሠን ፍለጋ ነበር። ታዋቂው ከበርቴ ባለውቃቢ የአገሩ መመኪያ ነበሩ። መኪናውም ሆነ ንግዱ በእርሳቸው ሰበብ የመጣ ነበር። እርሳቸው ጋ የሙስሊም መቃብር አለ ሲባል ሰምቻለሁ። ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያን እርሳቸው ጋር ይሄዳሉ። አያቶቼ ቤት በጃንሆይ ጊዜ ሦስት ወፋ ጋ ለመሄድ የመሸባቸው ሙስሊሞች አድረው ነበር አሉ። ስለ አሰጋገዳቸው፣ ስለ ቡና ስጦታቸው፣ ስለ ምርቃታቸው መድረስ (የልጅ ጎረቤት ይስጣችሁ)  አሁንም በፍቅር ይወራል። ስለዚህ አጋጣሚ በትዝታ ይነሳል እንጂ የእስላምና ክርስቲያን ድንበር በትክክል የተሰመረ ነው። በዚህም ሰበብ ሙስሊም እፈራ ነበር። መቼም ኢዝላሞፎቢክ የሚለኝ አይኖርም። ቢኖርም ጥረቱ በቀጣዮቹ መስመሮች ፉርሽ ይሆንበታል። ወደ ወፋ የሚወርዱ ሴቶች ሙስሊሞች "ወላሂ" ሲሉ ሰምቻለሁ። ወፋም ክርስቲያንና ሙስሊሙን ሌሊት በየተራ ሲያስተናግዱ "አማሮች ደህና እደሩ፤ የተጨነቀች የእስላም ነፍስ ትጠበቀኛለች" ይላሉ። የሳሲቱ ሙስሊም ከመምጣቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት አንድ አርበኛ እኛ ደጅ የምሽት ፀሐይ ሊሞቁ መጥተው ከሽማግሌዎች ጋር ሲያወሩ ያሉትን አስታውሰዋለሁ።

"አብዬ፣ እዚያ ደብረብርሃን የስላሙን መስጊድ አይተኸዋል?" 

"አዋድ"

"ለምንድነው እንደዚያ የረዘመው!" 

"እንዲቀርበው ነዋ ላላህ።"

"አላሁኣ ክበር የሚለውስ?" 

"እንዲበለጥግለት መሰለኝ።"

ሁለቱ ኃይማኖቶች ተከባብረዋል፤ ተዋግተዋል፤ ተቀላልደዋል። ይህም አይደንቀኝም። 

መሐመድ የመጣው አዲስ በተከፈተው ዳቦ ቤት ለመጋገር ነበር። ወጣቶችና ልጆች የመሐመድን ዳቦ በልተዋል። እኔ መሐመድ በተቀመጠበት ወንበር መቀመጥ እፈራ ነበር። ሽማግሌዎች ግን ስሙን መጥራት እንኳን ከብዷቸው ማሞ ብለው ጠሩት። ማናቸውም ወጣት ሊጠራ በሚችልበት። ባይተዋርነቱ ያልተመቸው መሐመድ የባለ ዳቦ ቤቱ ልጅ ክርስትና ስትነሣ ነተሣ። ክርስትና ስምም ወጣለት። አረብ አገር ሲሄዱ እንደሚሰልሙት። ቀጥሎ ሐኪም መሐመድ መጣ። ሰዎች በእርሱ መሮፌ ለመወጋት ማቅማማታቸውን ሰምቻለሁ። በኋላ ደግሞ ሌላ ጫት ቃሚ መምህር መሐመድ መጣ። ሳሲቶች ሙስሊም ሲያገኙ መሐመድ ብለው የሚጠሩበት ምክንያት ገባችሁ? ሴት ሙስሊም ማን ትባላለች ያለኝም አለ። ከዚያ ወጥቼ በርካታ ሙስሊም ጓደኞች ያሉኝ ሰው ነኝ።

የሳሲት ወጎች ቁ. 1 ጴንጤ የመጣ ቀን


ሳሲትን በበርካታ ጽሑፎቼ ነካክቻታለሁ። አንዳንዶች ለድርሰት ማሳመሪያ በምናቤ የፈጠርኳት ቀዬ ትመስላቸዋለች። እኔ ግን እላለሁ - በእውን ያለች ገጠር ቀመስ ከተማ ነች። በፊት እንደጻፍኩላችሁ እኛ ስናድግ በሳሲት መሬት የሌለው ወይም የማያርስ ሰው አልነበረም ለማለት እደፍራለሁ - ከጥቂት የመንግስት ሰራተኞችና ከአንዳንድ ምስኪን ነዋሪዎች በስተቀር። ለመጨረሻ ጊዜ ትቻት የሄድኩት በ1992 ዓ.ም. ነበር። ይሁን እንጂ ማንነቴን ለመቅረጽ የሚያስችላትን መሰረታዊ ዕድሜ ኖሬባታለሁ። የሳሲት ወሬ ሳይደርሰኝ የቀረበት ሳምንት እምብዛም የለም። በሳምንት ባይሆን በሁለት ሳምንት ከዘመድ ወዳጅ ወይም ከእንግዳ እሰማለሁ። በለቀቅሁበት ዓመት የሰማሁት የጴንጤዎች ወደ ሳሲት መምጣት ትልቅ ወሬ ነበር። በመኪና መጡ። የበፊቱ ገበያ ላይ ጄኔሬተር አስነሱ። ፊልም ከፍተው ማሳየት፣ በየመሐሉም ማስተማር ጀማመሩ። ትምህርቱ መንፈሳዊ ቢሆንም የተለመደው የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ባለመሆኑ የተበሳጩ ሰዎች እምነታችንን ሊያስክዱን ነው ብለው የድንጋይ ናዳ አወረዱ። ሽብር ተፈጠረ። ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ የጴንጤዎቹን ሕይወት ታደገ። ያለ ምንም ጉዳት አመለጡ። በእርግጥ አስቀድሞም እየዞሩ አንዲት ትንሽ ሰማያዊ እርጉዝ መጽሐፍ ሲያድሉ ተይዘዋል አሉ። ከአዲስ አበባ የመጡ የሳሲት ተወላጆች ናቸው። ሌላ ጊዜ ባደረኩት ማጣራት በዚህ ሁኔታ የተቆጣ ካህን አልነበረም። ፖሊስ የሰዎችን ጥቆማ መሰረት አድርጎ ጴንጤዎቹን አስሮ ካህናትን በምስክርነት ጠርቶ ነበር አሉ። ካህናቱ መጽሐፉ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው ነበር ያሉት። ምናልባት ቆይቼም የጠየኳቸው ካህናት በመጽሐፏ ላይ "ዶጮ መስቀል" ከመታተሙ በቀር የእግዚአብሔር ቃል ታትሟል ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ፈጽሞ ፍላጎት ስለሌለኝ በድጋፍም በተቃውሞም ሐሳብ መስጠት አልችልም። ተራኪ ነኝ። ሳሲት ጴንጤ የሚባል ነገር ያወቅሁት አንድ አስተማሪያችን ጴንጤ መሆናቸውን በመስማቴ ነበር። በእርግጥ አንደኛና ሁለተኛ ክፍል አስተምረውን የሄዱ ሌላ ጴንጤ መምህርም ነበሩን። እኔን በተለይ ያቀርቡኛል። ይቀልዱልኛል። "መዘምር፣ እስኪ ሚስት ፈልግልኝ" ይሉኛል። እስቃለሁ። "ጡቷ አጎጠጎጤ የሆነ፣ ተረከዟ ... ፀጉሯ ... " እስቃለሁ። ሳሲትን አልፎም ገጠር ውስጥ ጴንጤ መምህር ነበሩ። ስምንተኛ ክፍል ሆነን ጴንጤ ሐኪም መጣች። የጥምቀት ዕለት ሁሉም ሰው ጥምቀት ሲሄድ ብቻዋን ቀረች። ስላሳዘነቻት የአጣዬዋ ተወላጅ ዘመዳችን ዓለምነሽ አብራት ቆየች። የጴንጤዎች ድፍረት ሲገርመኝ ይኖራል። ሁሉንም ሰው ጴንጤ ለማድረግ ይጣጣራሉ። 

ቀጣይ - ሙስሊም የመጣ ቀን

 

ረቡዕ 28 ጁን 2023

በዜሮ እንዳያባዙብኝ

 በዜሮ እንዳያባዙብኝ


ተፈራ የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን በጥሩ ውጤት ሊያጠናቅቅ ነው። የመጨረሻውን መንፈቀ-ዓመት ስድስት ኮርሶች እንደ ወትሮው ኤ ወይም ቢ ፕላስ ለማግኘትና የወደፊት ሕይወቱን የሚያሳምርለትን ጥሩ ሥራ ለማግኘት በትጋት በመስራት ላይ ይገኛል። ሰቃይ ባይሆንም ከመካከለኛ ተማሪ በላይ ነው። በዩኒቨርስቲው ረዳት ምሩቅ ሆኖ መቀጠር ባይችልም በሌሎች ተቋማት የመቀጠር ቅድሚያ ያገኛል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከሌሎቹ ቀድመው ይቀጠራሉ። ከሌሎቹ ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን ምሩቃን ቀድመው የመቀጠር ዕድል እንዳላቸው ሳይታለም የተፈታ ነው።

"ከአንደኛ ዓመት ጀምሮ ካየሁት ፈተና የዚህ ሲሚስተሩ ባሰብኝ" አለው ተፈራ ለዶርሙ ልጅ ለለሜሳ። 

"አትጨናነቅ። ቀለል አድርገው። አንተማ ልትጨርስ እኮ ነው። እኛ አለን አይደል ገና አንድ ዓመት የሚጠብቀን!" ሲል ለማጽናናት ሞከረ ለሜሳ።

"ለሚሽ እባክህ የደረሰኝ አድቫይዘር ነው እንጂ ሌሎቹ እንደሱ አይሆኑም። አንተ ባይሆን ርዕስ ስትመርጥ እሱ እንዳይደርስህ አድርገህ ምረጥ።"

"እንደሱ ይሻላል? እንዴት ከሱ የሚያርቅ ርዕስ ከየት ይገኛል?" 

"የሱ ስፔሻላይዜሽን አናሊቲካል ኬሚስትሪ ስለሆነ ሌላ ምረጥ።" ብሎት ወደ አማካሪው ቢሮ ለመሄድ ከዶርሙ ወጣ። 

ከመጀመሪያው ጀምሮ ሦስት ምዕራፍ የደረሰለትን የመመረቂያ ጽሑፍ አስተካክለህ ጻፍ ሲሉት ሁለተኛቸው ነው። በእጁ አስተካክሎ የጻፈውን ከሰጣቸው ሳምንት ስለሞላው በቀጠሮው መሰረት በማማከሪያ ሰዓታቸው ወደ ቢሯቸው ሄደ። በሩን ሲያንኳኳ በጥንቃቄ ነበር። ምን እንደሚያናድዳቸው ስለማይታወቅ እንዳይከፉ ተጠንቅቆ ነው። በጣም ይፈራቸዋል። እንዲገባ የሚጋብዝ ድምፅ ሲሰማ ገባ። ሰላምታም ሳይሰጡ ወረቀቱን ገፉለት። በርካታ እርማት አለው። 

"በዚህ መልኩ አስተካክለህ የመጨረሻውን ቻፕተር ጨምረህ አምጣ" ሲሉት በድንገት ስሜቱ ብልጭ አለበት። "እኔ ከዚህ በላይ ለሦስተኛ ጊዜ አልጠለብጥም!  ብሎ ወረቀቱን ትቶት ወጣ። 

"ባትገለብጥ ለኔ ብለህ ነው!" ሲሉ ዛቱበት። 

ዶርሙ ገብቶ ሲያለቅስ ዋለ። ከሰዓት በኋላ ጓደኞቹ ከዲፓርትመንቱ ፀሐፊ ጋር መክረው ፕሮፌሰርን አናገሩለትና ተጠራ። እየሳቁ የእርማት ድግግሞሹን ምክንያትና የምርምርን ሂደት አስገነዘቡት። በአስር ቀናት ወስጥ ያለቀለትን ቅጂ አስገባ። የመጨረሻው ሥራ ማቅረብ ነው። ለማቅረብ የተመደቡለት ዶክተር የተለያዩ ፀባዮች አሏቸው። አንዳንዴ ጥሩ ይሆናሉ። ሌላ ጊዜ ይናደዳሉ። የአንድ በብሔር የተደራጀ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ናቸው። ዩኒቨርስቲ የሚመጡት አልፎ አልፎ ሲሆን የፖለቲካ ተሳትፏቸው በማስተማርና የማማከር ሥራቸው ላይ ጫና ፈጥሮባቸዋል። ተፈራ አዲስ የገዛውንና የመጀመሪያው የሆነውን ግራጫ ሱፍ በነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ለብሶ ለማቅረብ ተሰይሟል። አማካሪው በዕለቱ ተገኝተውለታል። ፈታኙ ምን ዓይነት ጥያቄ እንደሚጠይቁት እያሰበ መልስ እያዘጋጀ ነው። 

ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዟል። ተፈራ በተመደበለት የ10 ደቂቃ ጊዜ አቀረበ። የጥያቄው ሰዓት ደረሰ።

"አንተን ማን ይፈራሃል!" አሉት ፈታኙ። አነጋገራቸው በንዴትና በጥላቻ ዓይን ነበር። አጠያየቃቸው ስላልገባው ተደናገረ። "ተፈራ ብሎ ስም።" እያሉ ሳቁበት። "ማንም አይፈራችሁም። እንዲያውም እናንተ ትፈራላችሁ።" ሲሉ ጨመሩለት።

ጥረቴን ሁሉ በዜሮ እንዳያባዙብኝ ሲል አሰበ። ሰጋ። የሚጥሉት መሰለው። መመረቂያ ጽሑፍ በአመዛኙ በፈታኙ እይታና ይሁንታ ላይ የሚወሰን አስተራረም ስላለው ፈታኞች ተፈታኙን ለማጥቃት ከፈለጉ ለዚያ ዓላማ ይጠቀሙበታል። የጠየቁትን ጥያቄዎች መለሰ። በብዛት ከተናገረው ነገር ተነስተው እንጂ ወረቀቱን ያነበቡት አይመስሉም። አለቀ። ሲ ሰጡት። አስተካክል የተባለውን አስተካክሎ ለማስፈረም ወደ ቢሯቸው ሲሄድ ከጓደኞቹ ጋር ነበር። ፕሮፌሰሩ ጓደኞቹን በቋንቋቸው አናገሯቸው። እሱ የነሱን ቋንቋ አይችልም። ጦጣ አደረጉኝ ሲል አሰበ። ደመነፍሱ የሆነ ስለነገር ነግሮታል። ልጆዩን ስለሱ ማንነት ጠይቀው ኖሮ ልጁ የሀዲያ ተወላጅ መሆኑን ተረዱ። ተፈራ ውጤት ሲተላለፍ ቢ መሆኑን አይቶ ተገረመ። ተጨምሮለት ሳይሆን የስራው ውጤት መሆኑን ያምናል። እንዲያውም ኤ ጠብቆ ነበር። ተፈራ እስካሁን በነገሩ በጣም ይገረማል። ኬሚስትሪ ሊያስተምሩ ተቀጥረው የማንነት ኬሚስትሪን መሰረት አድርገው የፈለጉትን የሚያጠቁና የፈለጉትን የሚጠቅሙ መምህር እያለ ይታዘባቸዋል። በቅርቡ ወደሚያስተምርበት ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ምርምር ሊያቀርቡ መጥተው ሳለ እንደ መምህርነታቸው በጥሩ ሁኔታ አስተናግዶ ሸኝቷቸዋል። እርሳቸውም ስሙን ሲነግራቸው አስታወሱት። ከዕለቱ የምርምር ጉዳዮች ዉጪ ባልተወራበት የዩኒቨርስቲው የራት ግብዣ ወቅት የተቀመጡት ጎን ለጎን ነበር። የመምህሩንና የእርሳቸውን ዓይነት ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች ድብቅና አደገኛ ስራዎች ባሰበ ቁጥር የአማሮች ነገር ያሳዝነዋል።

ሰኞ 19 ጁን 2023

The Lie School - Flash Fiction

To begin with Ameha, our younger brother, was very much trustworthy. As the little child of the house, whenever he was asked about anything, he spoke the truth. Our dad believed him even more than our mom. If anything is broken, anyone stole to eat anything not permitted, or any village child came to the house to take the kids out to play, he was the one to speak the truth. Be it punishment or reward, we would get if after he was asked.
My elder sister on the other hand sometimes seems to tell false information. This information is not regarding all the things she tells you about. And not for anyone. If you are her schoolmate or equal, she keeps pretending she were another person. She would be younger, more attractive, wanted or intelligent as per your inclination. She could tell you she were scoring more than she did or were younger than she actually were. One day, our sister told her girlfriend that two boys fought over her. "How could they be fighting over her while our father is known to have been fierce to boys who go near her?" Ameha asked me when she went out to see her friend off. I couldn't meddle in such a matter. How could I expose the 'wanted' girl as unwanted. 
I observed lying in my mom too. I know I couldn't tell if most of the pieces of information she tells people are true because most of them happened before I was born. But I have a way to know. At times, what she says to one person isn't the same as what she might tell another. I know it is rude to tell her she said quite the opposite to another person. 
At this time, I am witnessing a few lies in my younger brother's speeches. What can I do?

ቅዳሜ 17 ጁን 2023

ኢትዮጵያም እንደ ዩጋንዳ?

ኢትዮጵያም እንደ ዩጋንዳ? 

ከስር በሚጀምር እንቅስቃሴ መንግሥትን አስገድደን ሕግ እናስወጣው!


አነጋጋሪውን የዩጋንዳ ፀረ-ተመሳሳይ ፆታ ሕግ በጥብቅ እደግፈዋለሁ። ኢትዮጵያም ይህን መሰል ሕግ ማውጣት አለባት ብዬ አምናለሁ። ያው ሆዳም ባለሥልጣን ዶላሩ ያሳሳዋል እንጂ! ባህላችንን አደጋ ላይ ሳይጥል አንድ ሊባል ይገባል። ከፈረንጆች ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለመማር የማይጨነቀው ዋልጌ ሁሉ ለዚህ ወደ ኋላ አላለም። ፈረንጆቹም ይህ ነገር መጤ እንዳልሆነ ለማስረዳት ብዙ ጽፈዋል። የሐሰት ጥርቅም! ለማናቸውም በሰፊው የሚደገፈው የባህል ወረራ አደገኛነቱ እያደር ይገባናል። እስካሁን የታዘብኳቸው፦ 

1. የአዲስ አበባ ጉዶች መጽሐፍ ላይ መሰለኝ በአዲስ አበባ ያለው አሳሳቢ ሁኔታ ተጽፏል።

2. ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የተባለ በትግርኛ ሳይሆን በአማርኛ ብቻ ለመጻፍና ባህልን ለማጥፋት የተላከ ብዬ የማስበው ግለሰብም ተመሳሳይ ፆታን በረቂቅ ዘዴ ለማስተዋወቅ ሞክሯል። ተልዕኮውን ትውልድ ተመራምሮ ይድረስበት።

3. የልማት ድጋፍ ለማድረግም ሆነ ለማናቸውም ዓላማ የሚመጡ አሜሪካውያንን እስኪ ጠይቋቸው። እኤአ በ2014 ሦስት አሜሪካውያን ሴቶች በደብረብርሃን በአንድ ካፌ ስለ በጎፈቃድ ሥራ ስናወራ በምስጢር ቃላት "አዞዎች" እያሉ ስለ ጉዳዩ ሲያወሩ ምስጢሩ ምን እንደሆነ ጠይቄ ሳይወዱ በግድ አውጣጥቼ ነገሩኝ። ግልጽ ተቃውሞዬን ተናግሬ እዚህ ለማስፋፋት እንዳይሞክሩ አስጠነቀቅኋቸው። ከሐይቅ የመጣችው አሜሪካዊት አንዱን የተመሳሳይ ፆታ አራማጅ ከሐይቅ እስከ ደሴ በመኪና ጎተቱት አለች። በግልጽ ለመከራከር ሲፈሩኝ ሌላ አሜሪካዊ በፌስቡክ ሜሴጅ የጥናት ወረቀት ተብዬዎችን እንዲልክልኝ አደረጉ። ይህን መሐልሜዳ ይሰራ የነበረ ፈረንጅ ልክ ልኩን ነግሬ አሰናበትኩ። ሌላ ቀን አንደኛዋ አሜሪካዊት ከሌላ ወንድ አሜሪካዊ ጋር ስትዳር ለሰርግ አዲስ አበባ ተጠራሁ። በግብዣው መሐል ያንን የመሐል ሜዳ አሜሪካዊ አየሁት። ለምን እንደሆነ በማላውቀው ምክንያት ሰውነቴ ተቀያየረ፤ ተናደድኩ። ከዚያ ወደሱ እየሄድኩ "Never in this country!" ማለትም "በዚህች አገር ፈጽሞ አይሆንላችሁም!" እያልኩ ስጠጋው የቤቱ ማለትም የ"አዲስ ጉርሻ" ባለቤት የሆነው ጃማይካዊ "ሰክረሃል መሰለኝ" ብሎ አስቆመኝ። ባያስቆመኝ በቤቱ በብዛት ሐበሾች ስለነበሩ ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል እገምታለሁ። አንዷ ጥቁር አሜሪካዊት ስለምትቆረቆርልን መሰለኝ "ነገሩ የለም ትላላችሁ እንጂ ወንዶቹ አሜሪካውያን እዚህ (ኢትዮጵያ) ብዙ ኢትዮጵያውያን ወንዶች የፍቅር ጓደኞች አሏቸው" ብላኛለች።

4. ውብሸት ወርቃለማሁ ከአሜሪካና ከዉጪ ዲፕሎማት ወንዶች ጋር ያለውን ምስጢር አላውቅም። ልጁ ግን በግልጽ የወጣ ግብረሰዶማዊ ነው። ይህን ላውቅ የቻልኩት ሙያዬ የእንግሊዝኛ ሥነጽሑፍ ስለሆነ የሱን ምርምሮች አግኝቼ ሳነብ ነው። ጉዳዩ አገርበቀል ነው ባይ ነው።

5. በቅርቡ ከአንዲት ሐኪም ጋር ሳወራ ብዙ ነገር ነገረችኝ። ወጣት ወንዶች በሚያጋጥማቸው ችግር እሷ ሐኪም ቤት እንደሚመጡ ነገረችኝ። ወንድአዳሪ እንደሆኑ ነግኛለች። ሌላ በሃያዎቹ አጋማሽ ያለች ወጣት ሴት ልጅ መውለድ እንደምትፈልግና ከዚህ ነገር እንዴት መውጣት እንደምትችል ለማማከር መምጣቷን ነግራኛለች።

5. አንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ አሜሪካ ሁለት ወንዶች ልጆች አሉት። አንዱ ገንዘብ ይልክላቸዋል። ሌላው አይልክም። "ትልቁ ሲረዳን አንተ ምነው ረሳኸን!" እያሉ ይጨቀጭቁታል። ተምሬ ሰርቼ እልክላችኋለሁ ቢል አስቸገሩት። ምስጢሩን ዘረገፈው። "እሱ እኮ ወንድ አዳሪ ሆኖ ከወንዶች ጋር ግንኑነት እየፈጸመ ከሚያገኘው ነው የሚልክላችሁ" ሲላቸው "ታዲያ አንተስ የለህም እንዴ!" አሉት። እሴት እየጠፋ ነው።

6. ትናይት ለአንዲት አዝማማያዋ ላላማረኝ ወጣት በፌስቡክ መልዕክት "ያልሆነ ነገር ውስጥ እንዳትገቢ። ህሊናሽን ንፁህ እንደሆነ አቆዪው" ብዬ መልዕክት ልኬላት "እሺ" ብላ መለሰችልኝ። ይሳካልኝ ይሆን? ሱፍ እየለበሰ በመዞር ኃይማኖት ከመስበክ እንደመለስኩት ወዳጄ በተሳካልኝ።

7. ባለፈው በሬዲዮ የሰማነውስ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ዉጪ አገር ከሴት ጋር ስትጋባ ሰርግ ላይ ወላጆቿን ጠርታ እናቷ ስትሄድ አባቷ የቀረው?

ወገኖቼ፣ ዝምታው ያብቃ! ልጅ ወልዶ ማዕረግ ማየት እንዳማራችሁ እንዳይቀር።

ዓርብ 16 ጁን 2023

የተጉለት ህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ እናግዝ

 ከጠጠር ዋሻ አማኑኤል እስከ ወንፈስ ቆላ አማኑኤል የመንገድ ፕሮጀክት

በአማራ ብሔራዊ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ሞጃና ወደራ ወረዳ፣ እንግድዋሻ ቀበሌ ከጠጠር ዋሻ አማኑኤል እስከ ወንፈስ ቆላ አማኑኤል የመንገድ ፕሮጀክት ከሁለት ዓመት በፊት ተጀምሮ ተቋርጦ የነበረ ቢሆነም ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ ጠቀሜታ እንደሚከተለው ይገለጻል፡-

አካባቢው መንገድ ስለሌለው እናቶች በልምድ አዋላጅ እየወለዱ ሕይወታቸው ማለፉና ጤና ማጣታቸው አሳሳቢ ችግር ላይ ሲሆኑ፤ መንገዱ ከተሰራ ግን ይህ ችግር ይስተካከላል፡፡

ዕቃ አጓጉዞ የመጠጥ ዉኃ መገንባት ባለመቻሉ ማህበረሰቡ በዚህ ዘመን ንጹህ የመጠጥ ዉኃ ያለማግኘቱ እየተቸገረ ይገኛል፡፡ መንገዱ ከተሰራ ግን የዉኃ ችግር ይወገዳል፡፡

ወንፈስ ቆላ አማኑኤል ትምህርት ቤት ቢኖርም የተሻለ በጎአድራጊዎች መርዳት ቢችሉና ቢገኝ እንኳን በመንገድ ምክንያት ሳይረዳ በመቅረቱ ወይም የተሻለ ግንባታ ባለመኖሩ ትምህርት ላልደረሳቸው ማድረስ አልተቻለም፡፡ መንገድ ካለ ግን ይህ ችግር ይስተካከላል፡፡
በወንፈስ የሚገኘው ገልብጥ አማኑኤል ታሪክ ያለውና የተመሰረተው በአጼ ናዖድ ዘመን ሲሆን የስም ትርጓሜውም ሁለት ወንድማማቾች ተካክደው በሀሰት ሊምሉ መጥተው በሀሰት ምለው ሲመለሱ መንገድ ላይ በመሞታቸው የተሰየመ ነው ይባላል፡፡ ሌላው የቤተክርስቲያኑን ቅርስ የሰረቀ ሰው ከነእቃው ተገልብጦ ሞቶ በመገኘቱ ነው የሚባልም አለ፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ አብያተክርስቲያናትን እየዞረ ሲያቃጥል ያልተቃጠለ ብቸኛ በመሆኑ ታሪካዊነት ስላለው ጎብኝዎች ቢያዩት የሚለው አንዱ ዓላማ ነው፡፡ የገልብጥ አማኑኤል ፀበል ፈዋሽ በመሆኑ በፀበሉ መጠቀም የሚፈልግ ብዙ ማህበረሰብ ቢኖርም በመንገድ ምክንያት ሳይጠቀሙ መቅረታቸው ይታወቃል፡፡ መንገዱ ከተሰራ ግን ይህ ችግር ይስተካከላል፡፡

እንግድዋሻ የተባለው ታሪካዊና አርበኞች ከጣሊያን ወራሪዎች ጋር ሲፋለሙ በመኖሪያነትና ህዝቡን ከእልቂት በማትረፊያነት ይጠቀሙበት የነበረው ዋሻ ወንፈስ ስለሚገኝ ለመጎብኘት መንገዱ ወሳኝነት አለው፡፡ ይህም የቱሪስት መስህቡን በማስጎብኘትና የማህበረሰብ ሎጅ ለመገንባት ለአካባቢው ህዝብ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

የመንገዱን ስራ የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተከታታለው ይገኛል፡፡ ህብረተሰቡም ለመንገድ ስራ ጥሩ ግንዛቤ ያለው በመሆኑ ግብር በሚክፍሉበት ወቅት በአባወራ 1000 ብር በነፍስ ወከፍ ከፍለው በተዋጣው መዋጮ ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ 9 ኪሜ ርዝመት ያለው መንገድ ቆረጣ በ ኤክስካቫተርና ሎደር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ክረምቱ እስከሚገባ ስራው የሚቀጥል ሲሆን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ስራው እንዳይስተጓጎል ታግዙንና ላልሰሙም ታሰሙልን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡

ስራው እስካሁን ከተጠቀምነው 1.6 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በትንሹ 2.5 ሚሊዮን ብር ይጠይቃል፡፡ ይኸውም

የቆረጣ 100 ሰዓት 8300 ብር በሰዓት ድምር 830 000 ብር፣ ኤክስካቫተር 100 ሰዓት በሰዓት 4580 ብር ድምር 458000 ብር፣ አፈር መድፋት 450 ድፌት በዳምፕ 2000 ብር ድምር 900000 ብር፣ ሎደር 312000 ብር ስራን የሚያካትት ነው፡፡

የመንገድ ስራው ኮሚቴ አባላት - ከበደ ኃይሉ፣ አባተ ተድላ፣ ጌታነህ በላቸው፣ አውላቸው ገብረጻድቅ፣ ተገሽ ደግነገር፣ ደመረ ተክለጻድቅና ሸዋፈራ ከበደ ናቸው፡፡ የፕሮጀክቱ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከጠጠር ዋሻ አማኑኤል እስከ ወንፈስ ቆላ አማኑኤል የመንገድ ፕሮጀክት 1000531335938 ነው፡፡

 






ረቡዕ 7 ጁን 2023

Donkey Language (A humorous story)

 This happened a few years ago and it is a true story. A group of friends made a trip from Debre Birhan to Debre Sina. It was a chilly but enjoyable morning. The chills scratched deep into our flesh, but that alone gave us a certain feeling. As we made the hour-long trip crossing valleys and mountains, we were talking about different issues including the historical importance of the place we were heading to. Even geographically it is a place worth noting. The mountain chain we follow is said to march from Shewa to Tigray. To the left of the mountain, the chilly highlands are sleeping, whereas to the right lowlands neighboring the Afar desert get hotter and hotter like furnace as the day progresses. After about 50 minutes-drive we stopped at the Menelik window, a cliff where one can see the lowland areas through. This was near Tarmaber town. We saw what was said part of the Awash valley across the mist and headed to Tarmaber. At Tarmaber, we saw the small shops, restaurants and houses, and bought food items form the people who came inside the bus. Then, off to Debre Sina. Past Tarmaber, we entered the eerie tunnel. How this tunnel fills you with awe and heaviness as you think a big mountain is reining just above it! Just past the last of the three tunnels made by the Italians during the five year war, we got out of the car and started taking in the brisk air. Everyone was talking about the serenity and beauty of that place which was sometimes cloudy and other times sunny. We took group photos and tasted every moment of our stay. Afterwards, we started our half-an-hour walk down towards the small town. A friend spotted a donkey coming towards us and invited us to bet. The quest was a strange one that everyone kept laughing. The guy was promising to make the donkey’s penis erect only using words. He started saying, “kullll kulll kulll kul kul kul” each time his voice getting louder and saying the sounds longer than before. We saw the donkey act to this immediately. Isn’t it amazing how the young man knew donkey language! The jack started to look for a jennet in every side but there was none. Its penis started to erect. Not only this, it ejaculated. Its semen dropped on the asphalted road. Everyone of us was laughing. Deep inside I felt pity to the donkey.  This is the one thing I remember from that trip. Let me add one more. There was an Indian teacher with us. He was sending voice messages to his wife about our stay at the town, not this donkey one though. Then, the wife was happy for us since she knew us before she went back to India to give birth. Whenever he told her that he saw old people asking for alms, she told him to give them money and he did. They are the most kindly Indians I knew. How kind was our friend! His kindness was unparalleled by anyone I know. The other Indians didn’t befriend or enjoy with locals. 

The End.        

እሑድ 4 ጁን 2023

የየግል መርሃችንን ለማስተካከል በጽሑፍ መመለስ ያለብን አስር ጥያቄዎች (ይሞክሩት)

ራሳችንንና በዙሪያችን ያለውን ዓለም በምናይበት መሰረታዊ የሕይወት መመሪያ ወይም አመለካከታችን ላይ መስራት ከፍተኛ የሆነ ጠቃሚ ለውጥ ያመጣልናል፡፡ ይህ የሕይወት መመሪያችን የአመለካከታችን፣ የባሕሪያችንና ከሌሎች ጋር ያሉን ግንኙነቶች መነሻ እንደመሆኑ፤ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ስለሆነም እርሱ ላይ ለመሥራት የሚጠቅሙ አስር ጥያቄዎችን ቀጥሎ እናቀርባለን፡፡ ለጥያቄዎቹ ለእያንዳንዳቸው ከአራት እስከ አስር መስመር የሚሆን ምላሽ ይጻፉ፡፡ በመጨረሻም ራስዎን ለመመልከት ዕድሉን ያገኛሉ፡፡ ምላሽዎ ምስጢራዊ ካልሆነ እሱን፤ ከሆነ ደግሞ አጠቃላይ አስተያየትዎን ይላኩልኝ፡፡  

1.       በተሳሳተ ግምት ምክንያት ወደ ውሳኔ በፍጥነት የሄዱበት የሕይወት አጋጣሚ አለዎት? እስኪ ያንን ሁኔታ ይግለጹት፡፡

2.       ያ የተሳሳተ ግምት ምን ነበር?

3.       ስለ ሌሎች ሰዎች የነበሩዎትን የተሳሳቱ ግምቶችንም ያስቡ፡፡ ከነዚያ ግምቶች በዚህ ሳምንት አንደኛውን ለማስተካከል ምን ማድረግ ይችላሉ?

4.       ከአገርዎ ውጪ ወይም በአገርዎ ውስጥ ወደ ሌላ የአገርዎ ክፍል ሄደው ያውቃሉ? እዚያ ምን የተለየ ነገር ተመለከቱ?

5.       የሰዎች ሁኔታና አድራጎት እንደጠበቁት ነበር? እርስዎስ ስለ ድርጊቶቻቸው ምን አሰቡ?

6.       የጉዞ ገጠመኝዎን አሁን መለስ ብለው ሲመለከቱት ሰዎች ስለ እርስዎ ምን ያሰቡ ይመስልዎታል? እነርሱ ስለ እርስዎ የነበሯቸው ሃሳቦች እርስዎ ስለእነርሱ ካነበሩዎት ጋር ይመሳሰሉ ይመስልዎታል?

7.       በጉዞዎ ሰዎችን ለመተዋወቅ ችለው ከነበረ ያ አጋጣሚ ስለነእርሱ የነበሩዎትን አስተሳሰቦች እንዴት ቀየራቸው?

8.       ወደ ቤትዎ ወይም ወደ ስራ ቦታዎ ሊወስዱዎ የሚችሉ የተለያዩ መንገዶችን ያስቡ፡፡ የተወሰኑት መንገዶች ከሌሎቹ በበለጠ ውስብስብ ናቸው? አንዱ መንገድ ከሌሎቹ በተለየ አመቺ ነው? ለምን ሆነ? ወይስ ለምን አልሆነም?

9.       ወደ ቤትዎ የሚወስድ እስካሁን የማያውቁት መንገድ አግኝተው ያውቃሉ? በተለያዩ መንገዶች መሄድ ያመጣብዎት ያልተጠበቁ ስሜቶች ምንድን ነበሩ?

10.   አሁን ከሰዎች ጋር የሚግባቡበትንና የሚኖሩበትን መንገድ ያስቡ፡፡ የተለያዩ ሰዎችን የመቅረቢያ መንገዶች ያሉ ይመስልዎታል? ምን ዓይነት አዳዲስ መንገዶችን ሊሞክሩ የሚችሉ ይመስልዎታል?   

ዓርብ 28 ኤፕሪል 2023

ጠባሴ ላይ እንደ አሜሪካ መስራት አትችልም

 ጠባሴ ላይ እንደ አሜሪካ መስራት አትችልም።


ትናንት ምሽት ወደ ቤት የገባሁት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሳይሞላ ነበር። በዕለቱ የነበሩኝን ሥራዎች የሠራሁበትን ሁኔታ ለማጤንና ለተመስጦ የተወሰኑ ደቂቃዎች ወስጄ ነበር። በእርግጥ ሁለት ክፍለጊዜ ከማስተማር በዘለለ የግል ሥራዬን ነበር የሠራራሁት። ሐሙስ እንደመሆኑ መጠነኛ የቤተመጻሕፍት ውይይትም ነበረች። ከተመስጦ በፊት ከሞባይሌና ከወረቀቶች ማስታወሻዎቼን ካየሁ በኋላ ወደ ኮምፒውተሬ ገለበጥኳቸው። ካደረ ስለሚዘነጋና የሐሳቡም መዘግየት ለተግባር ስለማያበቃው ነበር ይቺን በመልክ በመልኩ የማስቀመጥ ተግባር ያከናወንኩት። የመሰብሰብ ሥራ በየሚያስፈልገው ቦታ ተቀምጦ ለመደራጀትና ለመተግበር ካልበቃ ዋጋ የለውም ይል የለ ዴቪድ አለን። በእርግጥ በቀን ከሁለት ያላነሱ ገፆችን ወደ ኮምፒውተሬ አሰፍራለሁ። ይህን አሰልቺ የአሰራር አመል ምናልባት ቁራጭ ወረቀትና እስኪርቢቶ ከማይለየው አንድ ዘመዴ የወሰድኩት ይመስለኛል። ወደፊት እርግፍ አድርጌ ለመተው አስባለሁ። 

"ይህን ሁሉ የሐሳብ ክምር አንድ መላ ካልዘየድኩለት አስጨንቆ ሊገድለኝ ነው።" 

"ምን መላ አለው ብለህ ነው? ካልሞትክ አይተውህም!" 

"ሆሆይ! የስንት መጽሐፍ፣ ገጠመኝና ምልከታ ውጤት እኮ ነው። በቀላሉ መች እተወዋለሁ።"

"ትተወዋለህ። ያቺ ትንሿ ኮምፒውተር ስትበላሽ ይዛ እንደጠፋችው ፋይል።"

"ኧረ ተወኝ። አሁን ከዚያ ተምሬ ጉግል ድራይቭ ላይ አድርጌ የለም ወይ?" 

ሁለታችን ስንጨቃጨቅ ቆይተን የፌስቡክ አመል ውል አለችኝና ገባ ብዬ የዕለቱን ወሬ ቃርሜ ወጣሁ። 

ተመስጦ ለማድረግ በዚህ ዓመት መቸገሬን ባውቅም ገባሁበት። በቪዲዮ የተመራ እንዳላደርግ ኢንተርኔቱ ማታ ደካማ ነው። የአስር ደቂቃዋ ሰላሳ ደቂቃ ትወስዳለች። በዚያ ላይ የዩቱብ በየደቂቃው ማስታወቂያ መልቀቅ አሰልችቶኛል። ስለዚህ በራሴ የተወሰነ የትንፋሽና የማስታወስ ሥራ ሰርቼ በአንድ አፍታ ጨረስኩ።

ቤቱ በአጭር ዓመታት ማርጀቱ የለውጥን አስፈላጊነት አስታወሰኝ። ይህንና በርካታ የኑሮ ዘይቤ ለውጦችን ሳይቀር ነው በማስታወሻዬ የማሰፍረው። እንደገባሁ የሌሊት ልብስ ስለብስ ነበር ብርዱ የጀመረኝ። ስቶቭ ለኩሼ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እሳት መሞቅ ጀመርኩ። ሁልቀን ትዝ የሚለኝ የኢዮብ መኮንን "ተርቦ እሳት ይሞቃል" የሚለው ዘፈን ትዝ አለኝ። በፈቃዴ ያደረኩት መራብ አእምሮዬን ያሰላዋል። የፍላጎቶች መገደብ የሚያመጣውን ሁሉ እፈልገዋለሁ። ሰዓቴን ሳይ የክለብሐውስ የኦንላይን ቡክ ክለብ ውይይታችን መድረሱ ታወሰኝ። እዚያው እሳቱ ጋ ሆኜ መሳተፍን ፈለግሁ። በእርግጥ ማስታወሻ የያዝኩት በኮምፒውተሬ ነው። ኮምፒውተሩንም ኩሽና አምጥቼ ከፈትኩ። ኢርፎኔን ሞባይሌ ላይ ሰክቼ ውይይቱን ስከታተል አንድ ቅር የሚለኝ ነገር አለ። ይኸውም ተኩስ ቢሰማ አያሰማኝም የሚል ነው። "ቢሰማህስ ምን ልትሆን!" ይለኛል

አእምሮዬ። "ለጠቅላላ ዕውቀት ነው።" 

የዛሬው ውይይት ሰማኒያ በመቶ ሴቶች ያሉበት ነው። በእርግጥ ወደ ሴቶች የመጽሐፍ ውይይት ክበቦች እየተጋበዝኩ መግባት ጀማምሬያለሁ። ያው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ትዳር ስለማይገኝባቸው 12 መንገዶች ከፃፍኩ በኋላ ምከረኝ ባዩ በዝቷል። ለምክር ነው እንጂ እንደኔው ዕድሜ የተላለፋቸውን ሴቶች ለትዳር አልፈልጋቸውም። ምን አለፋችሁ! ውይይቱ ቀለጠ። መወያያው የፒተር ቲል "ዚሮ ቱ ዋን" ነበር። ከዚህ መጽሐፍ አንድ ሰው አዲስ ነገር መፍጠር ስለሚችልበት ሁኔታ ደራሲው ከኖረው ልምድ ለመገንዘብ ችለናል። የተለያዩ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን የመሰረተውና ባለ አክስዮን የሆነው ቲል የራሱ ሰራተኞች ከሱ በቀሰሙት ትምህርት ቢሊየነር የሆኑለት ነው። 

አወያይዋ በጽሑፍ እንዳወራ ጋበዘችና ፈቃደኛነቴን ስለገለጽኩላት ገባሁ። ሃሳቤም እንደሚከተለው ነበር። "እኔ ይህን መጽሐፍ ያነበብኩት እንደ አንድ ሥራ ፈጣሪና ነገን እየሠራ እንዳለ ሰው ነው። ከአስር ዓመቴ ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን የሰራሁ ሲሆን አንድን እንግዳ ነገር ለመሞከር ወደኋላ አልልም። ፒተር ቲልም ሌሎች ካንተ ጋር የማይስማሙበትን ነገር ለይ ይለናል። ሰው ምን ይላል ብዬ ሳይሆን ይህን ሥራ ብሰራው ያስደስተኛል ወይ ከሚለው አንፃር ነው የማየው። የኔን ሕይወትና ገጠመኝ ሌላ ማንም ሰው ስላልኖረው የምሠራው ሥራ ማንም ከሚያስበው ዉጪ መሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ። እስኪ እኔ ወሬ እንዳላበዛ አንድ ጥያቄ መልሱልኝ። የምዕራባውያን የስኬት መጻሕፍት ለእኛ አገር ይሰራሉ ብላችሁ ታስባላችሁ?"

አንደኛዋ ዉጪ ያለች ልጅ ስፔን መሰለኝ መናገር ጀመረኝ። የአማርኛዋ ሁኔታ ትግሬ ወይም ኤርትራዊ እንደሆነች ያስታውቃል። በእርግጥ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሙስሊም፣ የተለያዩ እንዳሉ ታዘሰቤያለሁ። "አርፍደህ ስለገባህ ነው እንጂ መጀመሪያ ላይ አዘጋጇን ሰላማን እየጠየቅናት ነበር። በኋላ ደግማ ልትነግርህ ትችላለች። የስኬት መጽሐፍ የማንበብ ፍላጎት ያለውም የሌለውም አለ። በተለይ ኢትዮጵያ ሆኖ ካለው አሠራርና የግንዛቤ ደረጃም አንፃር የምዕራቡን ሐሳብ እንዳለ ለመውሰድ ይከብዳል። የተለያዩ ሁኔታዎች ናቸው ያሉት። ለምሳሌ ባህሉ፣ ኢኮኖሚው፣ ቢሮክራሲው አንድን ሐሳብ ወደ መሬት ላውርድ ስትል ተስፋ ሊያሰቆርጥህ ይችላል። ሌሎች እንደ ጽናት፣ ግብ ማውጣት፣ ጥረት የመሳሰሉት ሁሉም ጋ አሉ። በአካባቢህ ያለው የሥራ ባህል አለመኖር ለሥራ ላያነሳሳህ ስለሚችል እነዚህ መጻሕፍት የማነቃቃት ሥራ ይሰሩልሃል። ብቻ አመጣጥነህ መሄድ አለብህ።" በሐሳቧ ላይ ደጋፊም ነቃፊም ሐሳቦችን ሰምተን ለኔ የማሳረጊያ ዕድል ተሰጠኝ። ሥራን ለመፍጠር ፈጽሞ አዲስ ሥራ የሚለውን በተለይ ለቴክኖሎጂ የሚሆነውን እንደወደድኩት፣ ሌሎች የወሰዱትን ኮፒ የማድረጉን የቻይናን ዓይነቱን ተግባርም እንደየሁኔታው ልሞክረው እንደሚችል ገለጽኩ። አንድ ቦታ ጀምሬ ቀስበቀስ ማስፋፋትን፣ ጠቅልሎ የመያዝንና ብዙኃኑን በዚያ መጥቀሙን መውደዴን ተናገርኩ። ስለመጽሐፉ ስላየኋቸው ዳሰሳ ቪዲዮዎችና ጽሑፎችም አሳወቅሁ። ስላሉኝ ዕቅዶች አቅጣጫ ስናገር ሌሎቹም አብረው የመሥራት ፍላጎታቸውን ገለጹልኝ። ምህንድስና የተማረች ልጅ ከጀመረችው አዲስ ድርጅት ፈጠራ፣ የአእምሮ ንብረት ምዝገባ፣ የገንዘብና ኢንቬስተር አለመኖርን ከሲሊከን ቫሊ ጋር እያነፃፀረች አወጋች። ከተወያዮች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት የሆነ አዲስ ነገር የሚሞካክሩ መሆናቸው ውይይቱን አድምቆታል። የተለያዩ ድረገፆችንና ጠቃሚ አድራሻዎችን አየተላላክን ነው። ቡድናችን በመጽሐፍ፣ በንባብና በውይይት ላይ አንድ ድርጅት ቢመሰርት ጥሩ ነው በማለት ላነሣ ስል ዋይፋዩ ተቀበረጠና ከውይይቱ አስወጣኝ። ዛሬ ስለቀረው ውይይት ነግረውኛል። ስለሐሳቤም እያወራን ነው።

የጃዋር መሐመድ 'አልፀፀትም' እንደ ባራክ ኦባማ 'The Audacity of Hope'?

'አልፀፀትም' የተባለው የጃዋር መሐመድ መጽሐፍ ወደ መደምደሚያው ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ለማምጣትና አገረመንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ ይጠቅማሉ የሚላቸውን ሐሳቦች ይጠቁማል። ይህን ግን ደጋግሞና በስፋት ካቀረበው...