ማክሰኞ 28 ኦገስት 2018

የኦሮምኛ ቋንቋ ገጠመኞቼ



አንደኛ፣ ቶኮፋ

አሁን አንድ መጽሐፍ እያነበብኩ ነው፡፡ መጽሐፉ <<Afan Oromo, A guide to speaking the language of the Oromo people in Ethiopia>> የሚል ሲሆን በአበበ ቡልቶ የተጻፈ ነው፡፡ የትግርኛ፣ የአማርኛና የኦሮምኛ መማሪያ መጻሕፍትን በጥሩ አቀራረብ ከቋንቋዎቹ ተናጋሪዎች ጋር እየሆነ የሚያጽፈው አሜሪካዊው ሠላም ጓድ አንድሩ ቴድሮስ ነው የመጽሐፍ ዝግጅቱ አስተባባሪና አርታኢ፡፡

ኦሮምኛን በእንግሊዝኛ እያብራራ የሚያስተምር መጽሐፍ እስካሁን ያገኘሁት በ1997 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከባሌው ተወላጅ ጓደኛዬ ከኑሪ ነበር፡፡ ኑሪ ግን አንድ ቀን ከተጠቀምኳት በኋላ ወሰደብኝ፡፡ የሂንሰኔ መኩሪያን መዝገበ ቃለት ከዩኒቨርሲቲው ቡክ ሴንተር በ199 በ30 ብር ገዝቼ ስጠቀም ቆይቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ መዝገበ ቃላት የወሰድኩትን ቃል ስናገር የቋንቋው ተናጋሪዎች ግር ይላቸዋል፡፡ ሦስት ገጽ ውስጥ ያሉ ቃላትን ከመጽሐፉ ወስጄ ታሪኩ አነጋን ምን ያህል ታውቃቸዋለህ ብዬ ጠይቄው 47 በመቶ ብቻ ነበር ያወቀው፡፡ እንግዲህ ቀበሌኛ ምንምን ይሆናል ተጽዕኖው፡፡

የአሜሪካ ሠላም ጓዶች ማሰልጠኛው ሰነድ የአማርኛው በጣም ጥሩ ነው፡፡ የኦሮምኛውንም ፈልጌ ኮፒ ሰላደርገው ቀረሁ እንጂ ጥሩ  እንደሚሆን አይጠረጠርም፡፡ የማስተማሪያ መንገዳቸው ግሩም ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ አሁን እያነበብኩ ያለሁት መጽሐፍ ዋጋው 200 ብር ነው፡፡ ከቡክ ወርልድ ነው የገዛሁት፡፡ ይህንም መጽሐፍ በማግኘቴ እድለኛ ነኝ፡፡

ከዚህ መጽሐፍ ንባቤ ከገጽ 81 መጨረሻ አንዲት ቃል ባይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ቃሏ ‹‹Anis = mee too›› ተብላ ቀርባለች፡፡ እና ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ፡፡ ሠላም ጋ ቡና የምታፈላው ልጅ ከመናገሻ ነበር የመጣችው፡፡ አማርኛ በመልመድ ላይ ስለነበረች፡፡ አንዲት ያልቻለቻት ነገር ነበረቻት፡፡ በምናብ አንድ ምልልስ ላቅርብ፡-

‹‹እንዴት ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ፡፡››

‹‹ይሄን የታደለ ገመቹን ዘፈን እወደዋለሁ፡፡ አንቺስ?››

‹‹እኔስ እወደዋለሁ፡፡››

ይህች ልጅ ገና ያልተማረች ቅጥያ ነበራት፡፡ ይህም የአማርኛው ‹-ም› ነው፡፡ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም፣ እሷም ስንል የምንጠቀመውና ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ተመሳሳይ ድርጊት ስናደርግ ወይም ተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ስንሆን የምንጠቀመው፡፡ የኦሮምኛ አቻው ‹-ስ› ነው፡፡ አኒስ፣ አቲስ፣ ኢሳኒስ እያለ የሚሄደው ማለት ነው፡፡

ልጅቱ ታዲያ የኦሮምኛውን ቅጥያ ለአማርኛ መጠቀሟ ነው የዛሬ ወጌ መነሻ፡፡ ይህንም ኦሮምኛን ለመማር ለሚፈልጉ እንደመነሻ አቀረብኩ፡፡ ይቀጥላል፡፡  

2 አስተያየቶች:

  1. ጥሩ እይታ ነው ፡፡ ሌሎች ጥናቶችንም አድረገህ የቋንቋዎችን ትስስር ብታሳየን ደስ ይለኛል

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

Z.A. They warn Oromo parents to advise their kids to avoid interacting with Amhara kids at school.

  Z.A. They warn Oromo parents to advise their kids to avoid interacting with Amhara kids at school. The Shenes said they wanted to aven...