2018 ኦገስት 12, እሑድ

ጊዜን ፍለጋ! ጊዜ፣ የገባቸው የሚተጉለት፣ አብዛኞች የሚዘነጉት ሐብት … ካለፈው የቀጠለ


ደራሲ - ሊዮን ሆ

ተርጓሚ - መዘምር ግርማ



ክፍል 1፡ ተመራጭ የአሠራር መንገዶችና ጊዜ 

ግለሰቦች አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ጊዜና ሐብታቸውን ምን ያህል በአግባቡ ይጠቀማሉ?  ቡድኖች ወይንም ድርጅቶችስ ትልልቅ ግቦችን ለመቀዳጀት የሚጠቅሟቸውን ጥሬ ዕቃ፣ የሰው ኃይል፣ ክህሎት፣ ገንዘብ ወይም የአስተዳደር አቅሞቻቸውን እንዴት ይፈጥራሉ ወይም ያሻሽላሉ? እንግዲህ አሁን እኔና እርስዎ የምርታማነት ጨዋታ አንዳንድ ማለት ጀምረናል፡፡ በዚህ ክፍል ብዙ ስራዎችን በፍጥነትና በጥራት ለመስራት የሚጠቅሙዎትን ሁሉንም ጠቃሚ ብልሃቶች አቀርብልዎታለሁ፡፡   



ስለማለዳ ሥራ ልምድዎ ድብቅ ጉልበት ምን ያህል ያውቃሉ?

አስተማማኝ የማለዳ የሥራ ልምድ መኖር ምርታማነትዎን ለመጨመርና አጠቃላይ ሕይወትዎን ለማሻሻል ከሚጠቅሙዎት ሁነኛ መንገዶች አንዱ ነው፡፡

የኔን (የሊዎን ሆን) የማለዳ የሥራ ልማድ ያየን እንደሆነ ጠንካራ ማሻሻያ ማድረግ ግድ የሚለው ነበር፡፡ እንዴት መሰለዎ? ጠዋት ከእንቅልፌ እንደነቃሁ ዝም ብዬ እየተገላበጥኩ ስልኬን መጎርጎር ብቻ ነበር ስራዬ፡፡ ጥሎብኝ በቃ እንቅልፍ ወስዶኝ ሳለ እንዲያው  ምን አምልጦኝ ይሆን እያልኩ ስፈልግ አረፍድላችኋለሁ፡፡ የእርስዎም እኮ እንደኔ እንደዱሮው ይሆንና ያርፈዋል ማሬ፡፡  ብዙዎቻችን ቀኖቻችንን የምንጀምረው ኢሜልና ማሕበራዊ ሚዲያችንን በማየት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጥሩ ልማድ ላይሆን ይችላል፡፡



ባልተtገባ መንገድ ማለዳችንን መጀመር ምርታማነታችንን ሊያነጥፈው ይችላል፡፡ በአንድ ቀን የተለመደው የሥራ ቆይታችን ስምንት ሠዓት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኃይላችን ከሠዓት ሠዓት ከፍ ዝቅ ማለቱን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ቀንዎን ተፍለቅልቀውና በጥሩ አቅም ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ቀኑ እየገፋ ሲሄድ ትንሽ እንቅልፍ ሊያሰኝዎት ይችላል፡፡ ደህና ጉልበት ባለዎት ሠዓት ውጤታማ ስራ መስራት ግድ ይልዎታል፡፡

አእምሮዎ ስል በሆነበት ጊዜ መስራትን ይልመዱ፡፡

‹‹የማለዳ ስራዎ በሳምንት ከሃያ በላይ ሰዓት ያተርፍልዎታል›› የሚለው የቤንጃሚን ሃርዲ መጽሐፍ ጊዜያችንን በአግባቡ ተጠቅመን ስለምናተርፍባቸው ሁነኛ ዘዴዎች ጠቃሚ ነጥቦችን ያቀርባል፡፡

 ዋነኛው ምክንያት በጠዋት ከምን ጊዜውም በላይ ንቁና ዝግጁ መሆንዎት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን የምርታማነት መስኮት በደንብ አልተጠቀሙበትም፡፡

ምን ያህል ስራ ሰሩ የሚለው በእርግጥ ምንም ዋጋ የለውም፡፡  የሰሩት ምንድነው የሚለው ነው ቁልፉ ጉዳይ፡፡

አነስተኛ ጥቅም ያላቸውን ጥቃቅን ስራዎች እየሰሩ እሰራዋለሁ ካሉት ዝርዝር ላይ እያንዳንዷን ዝርዝር ጫር እያደረጉ እያጠፉ ስራዎን መጀመር የሚፈታተንዎት ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ችግሩ ግን ራስዎን ከተጫነብዎት የትንንሽ ስራዎች ተራራ ጥግ እንደምንም ብለው ቆፍረው ባወጡ ጊዜ ድክምክም ብለው ጉልበትዎን የጨረሱበት ጊዜ ይሆናል፡፡ ይህም ትልልቆቹንና በዝርዝርዎት ላይ የበለጠ ጠቀሜታ አላቸው ብለው ያስቀመጧቸውን ስራዎችዎን መስራትን የበለጠ አዳጋች ሊያደርግብዎት ይችላል፡፡

ለአብነት አንድ መቶ የኢሜል መልዕክቶችን ስላዩ ምርታማ የሆኑ ሊመስልዎት ይችላል፡፡ ግን አባተሉዎት ነው መባል ያለበት፡፡ በማለዳ መጀመሪያ አንድ ትልቅ ዋጋ ያለውን ስራ ለመስራት ይቁረጡና ኢሜሉን ለኋላ ያዘግዩት፡፡

ይቀጥላል፡፡

እስከዚያው የእርስዎን ልምድ ያጋሩን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት

  በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት ረቡዕ፣ የካቲት 20፣ 2016 ዓ.ም. መዘምር ግርማ ደብረብርሃን   ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ ላምበረ...