2018 ኦገስት 22, ረቡዕ

በራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍት፣ ደብረ ብርሃን ስለተጀመረው ስልጠና



ከሥልጠናው በፊት አንድ ሃሳብ ልስጥዎት፡፡ ይኸውም እንደሚከተለው ነው፡፡ እቤትዎ ምግብ እያዘጋጁ የሚመገቡበት ሳምንታዊ የምግብ ሰንጠረዥ አለዎት? ወይንስ የለዎትም? እኛ በሥልጠናችን የምናደርገው የመጀመሪያው ነገር የምግብ ሰንጠረዥዎን አዘጋጅተው በአባላት እንዲተችልዎት ማድረግ ነው፡፡ በተቻለ መጠን የምግቡን ዓይነት ስብጥር ለማስተካከል ይሞክሩ፡፡ ቁርስ ከበድ ያለ ይሁን፡፡ ከምግብ በፊት ወይም በኋላ የሚበሉ ፍራፍሬዎችን ያካቱ፡፡ ይህ በፕሮግራም ምግብን የማዘጋጀት ነገር በህይወትዎ ሥነስርዓትን ለመልመድና የመርህ ሰው ለመሆን የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ ካሉን ቢያንስ አራት ስብዕናዎች የአንዱ፣ ማለትም የአካላዊ ማንነታችን፣ ግንባታ መሰረት ምግብ ስለሆነ የሱን ነገር መልክ ካስያዝን ሌላው ሰልፉን አሳምሮ ይከተላል፡፡
እን እኮ ሃብታም አይደለሁም!
 አይ እዚህ ቦታ ብዙም ስለማልቆይ!
 በፕሮግራም መታሰር አልሻም!
ሰበቡ፣ ሰበብ ሰበብ አለች! አንች ሰበበኛ፡፡
ሰበቡን ተወት አድርገው ይህን ዛሬ ይጀምሩትና የስኬት እርምጃዎን አንድ ይበሉ፡፡ የምግብ ሰንጠረዥዎን በኢንቦክስ ቢልኩልን ሃሳብ እንሰጥበታለን፡፡
ሌላው፡-
ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ ሲሆን፤ በደብረ ብርሃን ከተማ ያን ያህል የሚያስተማምንና ከተላላፊ በሽታ የዘለለ ምርመራና ክትትል የለም ተብለናል፡፡ እስኪ የሕክምና ሰዎች አማክሩን፡፡
መልካም ቀን
መዘምር ግርማ
የእንግሊዝኛ ሥነ-ጽሑፍ መምህር
የራስ አበበ አረጋይ ቤተመጻሕፍተ መስራችና
ሐሳብ አመንጪ
mezemir@yahoo.com

1 አስተያየት:

በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት

  በመንግሥት ወደ ወለጋ ከተወሰዱ በኋላ ዛሬ በግላቸው ደብረብርሃን የገቡት አዛውንት የዓይን ምስክርነት ረቡዕ፣ የካቲት 20፣ 2016 ዓ.ም. መዘምር ግርማ ደብረብርሃን   ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ ላምበረ...